ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, April 7, 2020

ከዓለም ጤና ድርጅት ፕሬዝዳንት ከዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጎን እንቆማለን!

  • ዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ ጣታቸው የሚቀስሩት አንዳንድ የምዕራብ ሚድያዎች ዋና ምክንያት ምንድነው?
  • በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር በዶ/ር ቴዎድሮስ አንፃር የሚፅፉት ትውቴር ያሉበትን ቦታ አይመጥንም 
==============
ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant

ሰሞኑን አንዳንድ ሰዎች ከምዕራብ አገሮች ጭምር በዓለማችን ላይ ለተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት የአመራር ድክመት እንዳለበት ለመናገር ሲሞክሩ ይሰማሉ።የዓለም ጤና ድርጅት ግን የሚጠበቅበትን ስራዎች በሚገባ እየተወጣ ነው።ከድርጅቱ የሚጠበቁት ሁለት መሰረታዊ ተግባራት ማለትም በወቅቱ የበሽታውን መከሰት ለመላው ዓለም ማስታወቅ፣በየወቅቱ ያለበትን ሁኔታ መንገር፣ አስፈላጊውን የባለሙያ ምክር እና የማስተባበር ሥራ መስራት ነው።በእዚህ መልክ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በሽታው ከመከሰት አንስቶ ወደ ወረርሽኝ ደረጃ ሲቀየር የዓለም አገሮች ከምር የሆነ ርምጃ እንዲወስዱ አምርረው  በማስታወቃቸው  አገሮች ጉዳዩን ከምር እንዲመለከቱ አድርገዋል።ከእዚህ በተረፈ እንደ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያሉ መሪዎች በራሳቸው የዝግጅት መዘግየት ምክንያት መወቀሳቸው የዓለም ጤና ድርጅትን አይመለከትም።

በአሁኑ ጊዜ በዓለም የጤና ድርጅት ፕሬዝዳንት ላይ በትዊተር ሳይቀር የስም ማጥፋት ዘመቻ ላይ የተሰማሩት በጃፓን የኤርትራው አምባሳደር እስጢፋኖስ  ናቸው።የዓለም አቀፍ ድርጅት ፕሬዝዳንት ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ከለላ ያለው በሌላ በዲፕሎማት ደረጃ ያለ ሰው በትዊተር የሚፅፉቸው ጉዳዮችም ውስብስብ ትርጉም እንዳለው ይታወቃል።

አምባሳደሩ የድርጅት ቁርሾን ወደ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ መድረክ ባይወስዱት ጥሩ ነው።አምባሳደሩም ሆኑ ዶ/ር ቴዎድሮስ ያሉበት የአሁኑ ቦታ ከድርጅት ቁርሾ ያለፈ ትልቅ አፍሪካዊ ብሎም ዓለም አቀፋዊ ቦታ መሆኑን አምባሳደሩ ሊገነዘቡት ይገባል።







በዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ላይ የተከፈተው የአንዳንድ የምዕራብ አገሮች ዘመቻ መነሾ ምንድነው?

የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተ በኃላ ዶ/ር ቴዎድሮስ ተከታታይ መግለጫዎች ከሰጡበት ውስጥ ሁለቱ መግለጫዎች አንዳንድ የምዕራብ ባለስልጣናትን አላስደሰተም።ይሄውም የቻይና እና የሰሜን ኮርያ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ በሽታውን በተሻለ መንገድ ለመከላከል እየረዳ መሆኑ መግለጣቸው ነው።እርሳቸው የገለጡት ሂደቱን ነው።ሂደት ደግሞ ተለክቶ ተሰፍሮ የሚቀመጥ ምክንያታዊ  ጉዳይ ነው።እንዳሉትም የሂደቱ ውጤት ደግሞ አሁንም እየታየ ነው።ሁለቱ አገሮች ብቻ ሳይሆኑ ሲንጋፖርም በጥሩ ሂደት እንዳለች እና ውጤቷም የተሻለ እንደሆነ ተመዝግቧል።መልካም የሰሩ አገሮችን ማመስገን በአንዳንድ የምዕራብ ሚድያዎች አንፃር እንደወንጀል እየተቆጠረ ይመስላል።በሌላ በኩል ወረርሽኙን በቻይና አሜሪካ የነበረ የምጣኔ ሃብት ቁርሾ አንፃር ለመጠቀም ዶ/ር ቴዎድሮስ ያልተመቿቸው አንዳንድ የምዕራብ ሚድያዎች አሉ።


የእዚህ ጽሁፍ አቅራቢ እንደናሙና የሁለት የቢቢሲ ዓለም አቀፍ ዘገባዎችን ተመልክቷል።የመጀመርያው ዶ/ር ቴዎድሮስ የኮርያ እርምጃ መልካም መሆኑን የገለጡበት መግለጫ እንደተላለፈ የቢቢሲ ዘጋቢ የዶ/ር ቴዎድሮስ መግለጫ ''non diplomatic'' (ዲፕሎማሲያዊ ያልሆነ መግለጫ) ስትል አዳምጧል።ዲፕሎማሲያዊ ያልሆነ ያስባለው በወቅቱ የምዕራቡ ዓለም በተለይ አሜሪካ ከሰሜን ኮርያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት አላገናዘበም ለማለት እንደሆነ መረዳት ይቻላል።የምዕራቡ ዓለም በተለይ አሜሪካ  ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደማዋጣቷ ተፅኖ ማሳረፍ ካላስቻላት ገንዘቡ ይቆጫታል።ይህንን ደግሞ በዩኔስኮ መረዳት ይቻላል።አሜሪካ ከዩኔስኮ ለቃ የወጣችው ድርጅቱ የአሜሪካንን ፍላጎት የሚያሟላ አንቀፅ ባለማፅደቁ ነው። ዩኔስኮ አገራት በዘረፋም ሆነ በማናቸውም መንገድ ከሌሎች አገሮች የዘረፉት ቅርስ መመለስ እንዳለባቸው ያምናል። በእዚህ የዓለም ጤና ድርጅት አንፃርም ኮርያን ማመስገን ያስወቅሳል። ሌላው ዶ/ር ቴዎድሮስ ቻይናን በሰበብ አስባቡ አለመውቀሳቸውም የምዕራቡን ዓለም ያስከፋ ሌላው ጉዳይ እንደሚሆን መገመት ይቻላል።ይልቁንም በመጀመርያ አካባቢ ቻይና በሽታውን በተመለከተ እየወሰደች ላለው እርምጃ ማመስገናቸው ለአንዳንድ የምዕራቡ ባለስልጣናት ሌላው ራስ ምታት ነበር።

የዓለም ጤና ድርጅት ባለስልጣን እና የቢቢሲው ጋዜጠኛ 


ከአራት ሳምንታት በፊትም የእዚህ ጽሁፍ ፀሐፊ  ከአንድ የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣን ጋር የተደረገውን  የቢቢሲ ''ሃርድ ቶክ'' ቃለ መጠይቅ ተከታትሏል።እዚህ ላይም በዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ ምክንያት ፍለጋ ቁፋሮ እንዳለ መመልከት ይቻላል።

ጋዜጠኛው = የዓለም ጤና ድርጅት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም  ፖለቲከኛ ናቸው።ቀደም ብሎ የህዝባዊ አርነት ትግራይ ድርጅት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ ፖለቲከኛ ናቸው፣ድርጅቱን የሚመሩትም በፖለቲካ ነው ይባላል .....

የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ መልስ = እንዴ! እራሱ የዓለም ጤና ድርጅት የምን ውጤት ነው? የፖለቲካ ውጤት አይደለም ወይ? ከፖለቲካ ውጪ የሆነ ዓለም አቀፋዊ ድርጅት የቱ ነው? ደግሞስ ድርጅቱን መምራት እና ፖለቲካ ምን አገናኛቸው።የዓለም ጤና ድርጅት በትክክል ስራውን እየሰራ ነው።አመራሩም ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው።ስለሆነም ይህ አቀራረብ መሰረተ ቢስ ነው። በማለት መልስ ሰጥተዋል።

ባጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳብያ አሜሪካ ተገቢ ሚና መጫወት ሲገባት በትራምፕ ቸልተኝነት እና ጉዳዩን አቅልለው በማየታቸው ለዓለም ከመትረፍ ይልቅ ራሷ አሜሪካ ችግሩን ለመቆጣጠር ፈተና ላይ ነች።ይህ ደግሞ በርካታ የአሜሪካንን ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች አበሳጭቷል። አሜሪካ በዓለም ላይ በተከሰቱ ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳይ ሁሉ የመሪነት ሚና ስትጫወት ቆይታለች።በኮሮና ወረርሽኝ ግን ለዓለም ከመትረፍ ይልቅ እራሷ ከፍተኛ ፈተና ላይ ነች።ለእዚህ ተጠያቂው የትራምፕ አመራር እንደሆነ ብዙዎች አሜሪካውያን ይናገራሉ።ስለሆነም  ለእዚህ ውስጣዊ ችግር አዲስ ምክንያት ለመፍጠር ''መሬት የመጫር'' ዓይነት ሙከራ ይታያል።ለእዚህ ማምለጫ ደግሞ ዶ/ር  ቴዎድሮስን በመውቀስ ለማሳበብ ይፈለጋል።ጉዳዩ የአንዳንድ ዘረኞች ደካማ አስተሳሰብም ሰለባ ነው።ስለሆነም ኢትዮጵያውያን ከዶ/ር ቴዎድሮስ ጎን  መቆም ይገባቸዋል።ይህ በእንዲህ እያለ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሰሞኑን የኮሮና ቫይረስ ክትባት በአፍሪካውያን ላይ ለመሞከር እንደሚያስቡ የተናገሩትን የፈረንሳይ የሐኪሞች ቡድን ትናንት በሰጡት መግለጫ ወቅሰዋል።ይህ ዓይነት የክትባት ሙከራ በድርጅቱ መርህ መሰረት የሚከናወን እንጂ የተለየ አካባቢ ለይቶ የሚደረግ ሙከራ የለም።ይህ ጉዳይ ከዘረኝነት እና ከቅኝ ገዢ አስተሳሰብ የሚመነጭ ክፉ ሃሳብ ነው ካሉ በኃላ በአፍሪካ ፈፅሞ ሊሆን አይችልም ብለዋል።በእዚሁ ጉዳይ ላይ የሰጡትን መግለጫ ከእዚህ በታች ካለው ቪድዮ ላይ ይመለከቱ።

video source = Daily Nation



ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...