ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, April 22, 2020

የኤልሳቤጥ ከበደ ታፋ በሐረር ፖሊስ ከአዲስ አበባ ታፍና መወሰዷ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ብቻ ሳይሆን በሴቶች ላይ የተፈፀመ ወንጀልም ነው።


Ethiopian Elizabeth Kebede Tafa (attorney) is illegally imprisoned by Harar Regional police in Ethiopia for over two weeks.The sole reason for her imprisonment was her comment on social media regarding the illegal status of the Harar Regional administration in Ethiopia. Human Right Organizations are expected to speak out loudly about her right of expression.

ኤልሳቤጥ ከበደ የሕግ ባለሙያ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ከአንድ ሳምንት በፊት በሐረር ያለውን አስተዳደር የሕግ ክፍተት በተመለከተ በማኅበራዊ ሚድያ አስተያየት ሰጠች።በእዚህ አስተያየቷ በቪድዮ በተደገፈ ማብራርያዋ የሐረር ምክር ቤትም ሆነ ተግባርና ኃላፊነት በተመለከተ ከሙያዋ አንፃር ማብራርያ ሰጥታለች።ሆኖም ግን ማብራርያውን ከሰጠች በኃላ የሐረር ክልል ፖሊሶች እንደሆኑ የተናገሩ ሰዎች ከአዲስ አበባ በግድ ይዘዋት ሄደው በሐረር እስር ቤት እንድትገባ ሆናለች።ጉዳዩን አስመልክተው የተቃወሙ  በጣት የሚቆጠሩ አክትቪስቶች ቢኖሩም የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንም ሆነ ማዕከላዊ መንግስት ጉዳዩን በቸልታ ተመልክቶታል።ይህ ደግሞ ወደፊት ክልሎች በክልላቸው ላይ ለሚፈፀሙ ኢሰብአዊ  መብት ተግባራት ሁሉ በቸልታ እንዲመለክቱ የሚያደርግ አደገኛ አካሄድ ነው።

በኢትዮጵያ ካሉት ክልሎች ውስጥ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ፍትሃዊ ያልሆነ የስልጣን ክፍፍልም ሆነ የነዋሪውን ቁጥር ያላማከለ የፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ እና ማኅበራዊ ግልጋሎቶች ያሉበት ይሄውም አካሄድ በተደጋጋሚ ለተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት የሆነበት  መሆኑ እየታወቀ፣ይህንኑ ፀሐይ የሞቀውን ጉዳይ ከሕግ አንፃር የተናገረችውን ኤልሳቤትን ያውም ከአዲስ አበባ ድረስ ታፍና ስትወሰድ በዝምታ ማለፍ ለማዕከላዊ መንግስትም ሆነ ለሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከፍተኛ ክስረት ነው። ኤልሳቤጥ ሐረር ፍርድ ቤት ብትቀርብም የዋስ መብቷ ተነፍጎ እንደገና ቀጠሮ ተሰቶባታል።ይህ ሁሉ የሆነው ደግሞ ሃሳብን መግለጥ እንደወንጀል ተቆጥሮባት ነው። 

ባጠቃላይ በኤልሳቤጥ  ላይ የተፈፀመው ሕግ የጣሰ ድርጊት መታረም አለበት።ድርጊቱ የመናገር እና ሃሳብን የመግለጥ መብትን ብቻ የሚጋፋ ሳይሆን የሐረር ክልል አስተዳደር ለሴቶች ያለውን የተሳሳተ እና ዝቅ አድርጎ የማየት ደካማ አስተያየትም የሚያመላክት ነው።በአሁኑ ጊዜ መንግስት ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ በርካታ ወንጀለኞች እንዲለቀቁ በሚያደርገበት ጊዜ የሐረር ክልል አስተዳደር ሃሳቧን ገለጠች ብሎ ወደ እስር የወሰዳት የሕግ ባለሙያ ኤልሳቤጥ ከበደ የዋስ መብት እንድታጣ የተደረገበት አካሄድ ተራ የማሸበር እና ነገ ሌሎች በክልሉ የሚፈፀሙትን በርካታ ወንጀሎች ተድበስብሰው  እንዲያልፉ ለማድረግ የሚሞከር የማስፈራርያ ተግባር አካል ነው።
አሁንም ኤልሳቤጥ እንድትፈታ መንግስትም ሆነ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ድርጅት እንዲሁም ሌሎች ድምፃቸውን ሊያሰሙ ይገባል።የሐረር ክልልም እየሄድበት ያለው ሕገወጥ አካሄድ ሊታረም እና አጠቃላይ ክልሉ ከለውጡ ወዲህ እየሄደባቸው ያሉት መንገዶች ሁሉ ውስጥ  የውጪ አካላት አማካሪዎች ላለመኖራቸው የማጣራቱ ሥራ  የመንግስት ተግባር እና ኃላፊነት ይሆናል።ኤልሳቤጥ ግን ሃሳቧን ከመግለጥ ሙሉ መብቷ ጋር በፍጥነት መፈታት አለባት።
  

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...