ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, January 4, 2016

ሰበር ዜና - በሳውዲ አረብያ እና በኢራን መሃከል ውጥረቱ ተባብሷል፣የዲፕሎማቲክ ግንኙነት እና በረራ ቆሟል።ሱዳን ከሳውዲ ጎን መሰለፏ እየተነገረ ነው (የጉዳያችን አጭር ጥንቅር)



በሳውዲ አረብያ እና በኢራን መሃከል ያለው ውጥረት ጨምሯል።የዲፕሎማሲ ግንኙነት አቁመዋል።
ሱዳን እና ባህሬን ከሳውዲ ጎን ቆመዋል።ጉዳዩ ከየመኑ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የአካባቢውን አገራት ሊያነካካ ይችል ይሆን? የሚል ጥያቄ አስነስቷል።ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ የማነካካቱ ጉዳይ ለብዙዎች ጥያቄ አይደለም።ነገር ግን ጥያቄው በምን ያህል ደረጃ የሚለው ነው።ኢራን የሚገኘው የሳውዲ ኢምባሲ ጥቃት ደርሶበታል።ይህንን ተከትሎ የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቆሟል።

ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 25/2008 ዓም ደግሞ በሁለቱ አገራት መሃከል የነበረው የአየር በረራ መቆሙ ተሰምቷል።ብዙውን ጊዜ የአየር በረራ በሁለት አገራት መሃከል የሚቆመው በተለይ ከዲፕሎማቲክ መቆም ቀጥሎ ሲከተል መጪው  ወታደራዊ ግጭት ሲሆን ማየት በአለማችን በርካታ የግጭት ሂደቶች የተለመደ ሁኔታ ነው።ሲ ኤን ኤን ዛሬ ታህሳስ 25/2008 ዓም የሳውዲውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአገራቸው እና በኢራን መሃከል ያለው የበረራ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን የቆመው ዜጎቻቸውም ፈፅሞ አንዳቸው ወደ አንዳቸው አገር እንዳይሄድ እቀባ መጣሉን ገልፀዋል።ለጉዳዩ በፍጥነት መባባስ አንዱ ምክንያት የተባለው የኢራን ሰልፈኞች የሳውዲን ኤምባሲ ማጥቃታቸው ነው። የኢራን ወጣት ደግሞ ኤምባሲ መውረር ከቀደሙት አባቶቹ የወረሰው ልማድ ሆኖ ዘመናትን ተሻግሯል።ከእዚህ በፊት በቀቃዛው ጦርነት ወቅት ቴራን የሚገኘው  የአሜሪካ ኢምባሲ መወረሩ ይታወሳል።

ኢራን ባብዛኛው የሺአ እስልምና ተከታይ ሲበዛባት ሳውዲአረብያ የሱኒ ሙስሊም ተከታዮች ይበዙባታል።ዩናይትድ አረብ ኢምረት፣ባህሬን እና ሱዳን ከሳውዲ አረብያ ጎን እንደቆሙ የታወቀ ሲሆን።ሁኔታው የመካከለኛው ምሥራቅን ባጠቃላይ ሊያበጣብጥ ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አለ።በሌላ በኩል የቀድሞው የእንግሊዝ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚስተር ጃክ ስትሮው ለሲኤንኤን ቀርበው ሲናገሩ ግጭቱ ለአይ ኤስ ኤስ ሽብርተኛ ቡድን መስፋፋት ምክንያት እንዳይሆን የሚል ስጋታቸውን ገልጠዋል።

በመጨረሻም የኢራን እና የሳውዲ ግጭት የመካከለኛውን ምስራቅ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድም የራሱ የሆነ አንድ አይነት ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ጥላ ይዞ እንደሚመጣ ለማወቅ ይቻላል።ኤርትራ የመንን በአየር ለሚደበድበው የሳውዲ ቡድን ድጋፍ መስጠቷ ይታወሳል።የሳውዲ እና የኢራን ውጥረት ለሌሎች የነዳጅ ሻጭ አገሮች ደግሞ ሰርግና ምላሽ ነው።ምክንያቱም የነዳጅ ዋጋ ከአሁኑ የዋጋ መጨመር ማሳየት ጀምሯል።በነገራችን ላይ የሁለቱ አገሮች የቃላት ጦርነት ከአሁኑ እየተሟሟቀ ነው።የሳውዲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ ሰኞ ሲ ኤን ኤን ቀርበው ቆጣ ባለ እና በአረብኛ ቃና በተቃኘ እንግሊዝኛ ''ኢራን የሳውዲን ኃይል ንቃው ከሆነ በጣም ተሳስታለች'' ሲሉ ታይተዋል።


ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
ታህሳስ 26/2008 ዓም (December 5/2016)

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...