ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, January 19, 2016

ኢህአዴግ/ህወሓት ለኢትዮጵያ ድንበር በሞቱት አባቶቻችን ደም ውስጥ እጁን ነከረ! በገንዘብ፣በጎጥ እና በደም ጥማት የሚንቀለቀል ልቦና የተሸከሙት የአራት ኪሎ ባለስልጣናት አፄ ቴዎድሮስ ከነገሱበት እስከ አፄ ዮሐንስ የተሰዉበትን መሬት ለሱዳን ለመሸጥ ተስማምተዋል።የሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ትርጉም ይዘናል።ኢህአዴግ/ህወሓት ለኢትዮጵያ ድንበር በሞቱት አባቶቻችን ደም ውስጥ እጁን ነከረ! አፄ ቴዎድሮስ ከነገሱበት እስከ አፄ ዮሐንስ የተሰዉበትን መሬት ለሱዳን ለመሸጥ ተስማምቷል። ኢትዮጵያ የተዳከመች ሲመስላቸው ጠላቶቿ ስነሱባት መስማት አዲስ ነገር አይደለም። አዲስ ነገር የሚሆነው በቤተ መንግስቷ በኢትዮጵያ ስም መንግስት ነኝ የሚሉ ስብስቦች የኢትዮጵያን ጥቅም ከባዕዳን ጋር ሲዶልቱ፣ሲሸጡ እና ሲያስማሙ መመልከት ነው።በገንዘብ፣በጎጥ እና በደም ጥማት የሚንቀለቀል ልቦና የተሸከሙት የአራት ኪሎ ባለስልጣናት አፄ ቴዎድሮስ ከነገሱበት እስከ አፄ ዮሐንስ የተሰዉበትን መሬት ለሱዳን ለመሸጥ ተስማምተዋል።ይህ ሕሊናን የሚያደማ ብቻ ሳይሆን የመኖር እና ያለመኖር ህልውና ጉዳይ ነው።''ዳሩ ሲነካ መሃሉ ዳር ይሆናል'' የሚለው አባባል እዚህ ላይ ማሰቡ ተገቢ ነው።ይህ ሥራ በመንግሥትነት እራሳቸውን የሾሙ ስብስቦች ኢትዮጵያን የማፈራረስ ልክ የት ድረስ እንደሚሄድ ብቻ ሳይሆን የከሃዲነት ደረጃቸው እና ህዝብን የመናቃቸው መጠን ምን ያክል እንደሆነ ማሳያ ነው።

አቶ ኃይለማርያም በድንበሩ አካባቢ የሚያርሱ ገበሬ ኢትዮጵያውያንን የህዝብ ተወካይ ነኝ ባሉ ምክር ቤት ስም ''ሽፍቶች'' እያሉ የተሳደቡትን ስድብ የሱዳኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እብራሂም ጋንዱር ለአልጀዝራ በሰጡት መግለጫ ላይም ደግመውታል።ኢትዮጵያውያንን እርሳቸው ብቻ ሳይሆኑ በስልጣን ላይ የተቀመጠው የኢትዮጵያ መንግስትም እንደሚገልላቸው ሲገልጡ ''ኢትዮጵያ እና ሱዳን በሱዳን ግዛት ላይ የሰፈሩትን ሽፍቶች  (gangs) በመግታት የድንበር ማካለሉን ሥራ በአንድነት እየሰሩ ነው'' ነበር ያሉት።አሁን የንግግር እና የወሬ ጊዜ አይደለም።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል በሙሉ መለየት አለበት።ኢትዮጵያን ከሸጡ ጋር ነህ ወይንስ አይደለህም? ጥያቄው ይህ ነው።ኢትዮጵያን የከዳ በሙሉ ተገቢውን ቅጣት ማግኘት አለበት።

ኢህአዴግ/ህወሓት ለኢትዮጵያ ድንበር በሞቱት አባቶቻችን ደም ውስጥ እጁን ነክሯል።የኢትዮጵያ የቀደሙት መሪዎች ማናቸውም የኢትዮጵያን ድንበር ጉዳይ ላይ ሲደራደሩ አልታዩም።አፄ ዮሐንስ ከደርቡሽ ጋር ተዋግተው መተማ ላይ አንገታቸው የተቀላው ለአገራቸው ክብር ነው።አፄ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ እራሳቸውን የገደሉት ለኢትዮጵያ ክብር ነው።ዛሬ ሚልዮኖች ያፈሰሱትን ደም እረግጦ የኢትዮጵያን መሬት ለባዕዳን አሳልፎ ለመስጠት የተነሳው የህወሓት ቡድን የሕዝብ ፍርድ ያስፈልገዋል።

ወቅቱ እያንዳንዱ ሰው ለድንበሩ ዘብ የሚቆምበት ጊዜ ነው።ባዕዳን ዳር ድንበሩን ሲፈልጉ ከመሃል በጎሳ እንድንቧደን እና እንድንጋጭ በማድረግ ጭምር ነው።ለእዚህም የሚረዳቸው የአራት ኪሎ መንግስት አለ።ሱዳን የኢትዮጵያን መሬት ስትወስድ ብቻዋን አትሆንም ኢትዮጵያን ለዘመናት ለማዳከም የሚማስኑ የአረብ ሊግ አባላት እና የሩቅ መሰሪዎችንም ይዘው ነው።ጉዳዩ የተቀናበረ ነው።ለኢትዮጵያውያን ቀዳሚውን ሥራ ለመግለፅ የሚያጠቃልለው ሁነኛ አባባል ''ጠላትማ ምን ጊዜም ጠላት ነው።አስቀድሞ መምታት አሾክሿኪውን ነው'' የሚለው ነው።ቀዳሚው ጠላት እኛነታችንን የሸጠን ለ24 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተንሰራፋው ስርዓት ነው።ቅድምያ ስልጣኑን መልቀቅ ያለበት ህወሓት ነው።የሱዳኑ ጉዳይ 'እዳው ገብስ ነው'። 

ከእዚህ በታች የሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ እኤአ ጥር 17/2016 ዓም ድንበሩ በእዚህ ዓመት እንደሚሰጥ የገለጠበትን ዘገባ ትርጉም ያንብቡ።(ትርጉም ጉዳያችን)

ሱዳን እና ኢትዮጵያ የድንበር ማካለል ስራቸውን በእዚህ ዓመት ያጠናቅቃሉ

ጥር 17/2016 (ካርቱም)
በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል የድንበር ማካለሉን ሥራ ኃላፊነት የወሰደው የቴክኒክ ኮሚቴ በመሬት ላይ ድንበሩን የማካለሉን ሥራ በእዚህ ዓመት እንደሚያጠናቅቅ ገልጧል።ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኃላ ቆሞ የነበረው የድንበር ማካለሉ ሥራ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም እና የሱዳኑ ፕሬዝዳንት  አልበሽር ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው በሰጡት መመርያ መሰረት ስራውን በህዳር ወር 2014 ዓም ቀጥሏል።የቴክኒክ ኮሚቴው ሰብሳቢ አብደላ አል-ሳዲግ ለሱዳን ሚድያ ሴንተር (SMC) እንደገለጡት ኮሚቴው እዚህ ግባ የሚባል ምንም ችግር በስራው አልገጠመውም ነበር።
አብደላ አል-ሳዲግ አክለው እንደገለጡት በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ያለው  የሚካለለው የድንበር ርዝመት 725ኪሜ በሁለቱ አገሮች መካከል ያሉ ገበሬዎች በባለቤትነት ግጭት የተፈጠረበት አል-ፋሻጋ አካባቢ እና ደቡብ ምስራቅ ግዛት ገዳረፍን ያጠቃልላል።

አል-ፋሻጋ 250 ስኩኤር ኪሎ ሜትር እና 600 ሺህ ጋሻ ለም መሬት ይዟል።ከእዚህ በተጨማሪ ቦታው በወንዝ የበለፀገ ሲሆን አትባራ፣ሰቲት እና ባስላም የተባሉ ወንዞች ይገኙበታል።ባሳለፍነው ቅዳሜ እና ዕሁድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢብራህም ጋንዱር መቀመጫውን ኩአታር ላደረገው አልጀዚራ ቴሌቭዥን እንደገለፁት ''ኢትዮጵያ እና ሱዳን በሱዳን ግዛት ላይ የሰፈሩትን ሽፍቶች  (gangs) በመግታት የድንበር ማካለሉን ሥራ በአንድነት እየሰሩ ነው'' ከማለታቸውም በላይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በመቀጠል አፅንኦት ሰጥተው እንደተናገሩት ''አል-ፋሻጋ የሱዳን ግዛት ነው።የሱዳን መንግስት የኢትዮጵያ ገበሬዎች እንዲያርሱት ፈቃድ የሰጠውም በሁለቱ አገራት መካከል ባለው ትብብር ሳብያ ነው።ኢትዮጵያም አልፋሻጋ የሱዳን ግዛት መሆኑን አምናለች'' ብለዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋንዱር በሁለቱ አገራት መካከል በፕሬዝዳንት ደረጃ በድንበሩ ጉዳይ ውይይት መደረጉን ጠቁመው ውይይቱ በሱዳን ጋዳርፍ እና ብሉ ናይል ግዛት እና በኢትዮጵያ በአማራ ክልል ደረጃም መደረጉን ገልጠዋል።በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል የተሰመረው በእንግሊዝ እና ጣልያን ቅኝ ግዛት ወቅት በ1908 ዓም ነው።ሁለቱ መንግሥታት ድንበሩን እንደገና በማካለል የአካባቢው ሕዝብ መጥቀሙ ላይ ተስማምተዋል።ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ገዢውን ፓርቲ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፎ በመስጠቱ ይከሱታል።

 ====የሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ትርጉም መጨረሻ===

Sudan, Ethiopia to complete border demarcation this year

January 17, 2016 (KHARTOUM) - The technical committee tasked with redrawing the border between Sudan and Ethiopia said it would complete its work on the ground during this year.
JPEG - 45.1 kb
A road leading to Ethiopia-Sudan border (Photo Jamminglobal.com)
In November 2014, Ethiopia’s Prime Minister Hailemariam Desalegn and Sudan’s President Omer al-Bashir instructed their foreign ministers to set up a date for resuming borders demarcation after it had stopped following the death of Ethiopia’s former Prime Minister, Meles Zenawi.
The head of the technical committee Abdalla al-Sadig told the semi-official Sudan Media Center (SMC) that the border demarcation between Sudan and Ethiopia doesn’t face any problems.
He pointed out that the length of the border with Ethiopia is about 725 km, saying the process of demarcation is proceeding properly.
Farmers from two sides of the border between Sudan and Ethiopia used to dispute the ownership of land in the Al-Fashaga area located in the south-eastern part of Sudan’s eastern state of Gedaref.
Al-Fashaga covers an area of about 250 square kilometers and it has about 600.000 acres of fertile lands. Also there are river systems flowing across the area including Atbara, Setait and Baslam rivers.
On Saturday, Sudan’s foreign minister Ibrahim Ghandour told the Qatar-based Aljazeera TV that Sudan and Ethiopia are working together to curb the activities of Ethiopian gangs inside Sudanese territory.
He stressed that Al-Fashaga is a Sudanese territory, saying the government allowed Ethiopia farmers to cultivate its land as part of the cooperation between the two countries.
“However, Ethiopia is committed and acknowledges that [Al-Fashaga] is a Sudanese territory,” he said.
Ghandour pointed to joint meetings between the two countries at the level of the presidency to discuss borders issues.
Sudan’s Gadarif and Blue Nile states border Ethiopia’s Amhara region. The borders between Sudan and Ethiopia were drawn by the British and Italian colonisers in 1908.
The two governments have agreed in the past to redraw the borders, and to promote joint projects between people from both sides for the benefit of local population.
However, the Ethiopian opposition accuses the ruling party of abandoning Ethiopian territory to Sudan.

ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
ጥር 10/2008 ዓም (ጃኗሪ 19/2016)

No comments:

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...