ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, August 2, 2014

በመጪው ሰኞ ሐምሌ 28/2006 (ኦገስት 4/2014) ዓም ዋሽግተን ዲ ሲ ምናልባትም በኢትዮጵያውያን ዘንድ በታሪክ ያልታየ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ታስተናግዳለች። የኢህአዲግ/ወያኔ አስተዳደር ለእዚህ ጉባኤ የሚመጥን ውክልና ይዟል ወይ? የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ


በመጪው ሰኞ ሐምሌ 28/2006 (ኦገስት 4/2014) ዓም ዋሽግተን ዲ ሲ ምናልባትም በኢትዮጵያውያን ዘንድ  በታሪክ ያልታየ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ታስተናግዳለች።

የኦባማ አስተዳደር እ አ አቆጣጠር ከነሐሴ 4 እስከ 6/2014 ዓም በዋሽግተን ዲሲ ''የአሜሪካ - አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ'' ጠርቷል።ጉባኤው ከሃምሳ በላይ የአፍካ መሪዎች እና ተወካዮች የሚገኙበት እና በአሜሪካ ታሪክ የመጀመርያው ግዙፉ የአፍሪካ እና የአሜሪካ የጋራ ጉባኤ መሆኑ ተነግሮለታል።ስብሰባው ባለፈው ዓመት ፕሬዝዳንት ኦባማ ወደ አፍሪካ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት የተነሱ የአፍሪካ እና የአሜሪካ ግንኙነቶች ላይ የሚያተኩር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።እንደ ዋይት ሃውስ መግለጫ መሰረት የጉባኤው መሪ ቃል ''በመጪው ትውልድ ላይ መስራት'' (Investing in the Next Generation)  የሚል መሆኑን ይጠቅሳል።

ስለጉባኤው ይህንን ያህል ካልን የኢትዮጵያ የኢህአዲግ/ወያኔ አስተዳደር ለእዚህ ጉባኤ የሚመጥን ውክልና ይዟል ወይ? ብለን መጠየቅ አለብን።መልሱ አይመጥንም የሚል ይሆናል።ለእዚህ ቀላል ማስረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል። ለምሳሌ ከጉባኤው መሪ ቃል ''በመጪው ትውልድ ላይ እንስራ'' የሚለውን ብቻ ብንመለከት ኢህአዲግ/ወያኔ የመጪውን ትውልድ በማሳደድ እና ፍላጎቱን በኃይል በመጨፍለቅ የታወቀ እንጂ መጪውን ትውልድ ለአፍታም ቢሆን ሲያዳምጥ አልተስተዋለም።እዚህ ላይ መጪው ትውልድ ብዬ የምጠራው አሁን ያለውን ወጣት ትውልድን ነው።ነገ ሀገር ተረካቢው እርሱ ነዋ!  

ለአብነት ያህል ኢህአዲግ/ወይኔ በያዝነው ዓመት ብቻ የመጪው ትውልድ አካላትን ያጠቃበት እኩይ ተግባራት ብንመለከት ምን ያህል ለጉባኤው አለመመጠኑ እና ከጉባኤው መሪ ቃል ጋር ተግባሩ እንደተጣላ እንረዳለን።ከታሰሩ አንድ መቶኛ ቀናቸውን የያዙት  የዞን 9 ጦማርያን ለእስር የተዳረጉት፣በርካታ ወጣት ጋዜጠኞች ወደ ወህኒ የተወረወሩት ምንም አይነት ወንጀል ተገኝቶባቸው ሳይሆን ሃሳባቸውን በነፃ ለመግለፅ ስለሞከሩ ከሁሉም በተሻለ ደግሞ መጪውን አማትረው በመመልከት ለሀገራቸው ይበጃል ያሉትን ሃሳብ በመሰንዘራቸው ብቻ ነው። ይህን ያደረገ መንግስት ተወካዮች ናቸው እንግዲህ ''አይናቸውን በጨው አጥበው'' በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ የሚዘጋጁት።

ሁለተኛ አብነት ልጥቀስ በያዝነው ዓመት አሜሪካ የዓለማችን ''የአዲሱ ትውልድ አዲስ ሃሳብ አመንጪዎች እና መሪዎች'' ብላ ባዘጋጀችው ጉባኤ ላይ የሰማያዊ ፓርቲ መሪ ኢንጅነር ይልቃል አንዱ ተመራጭ እና ተጋባዥ እንደነበሩ ይታወቃል።ኢህአዲግ/ወያኔ ግን ምን ነበር ምላሹ? ኢንጅነር ይልቃል የጉዞ ሰነዳቸውን አዘጋጅተው  አየር መንገድ እስኪቀርቡ ድረስ ጠብቆ ከፓስፖርታቸው አንዱን ገፅ ቀዶ እንዳይሄዱ ከለከላቸው።የመጪው ትውልድን እግር በእግር እየተከታተለ የማምከን እኩይ ስራውን ቀጠለበት። ይህንን ትዕዛዝ የሰጡት ባለስልጣናት ናቸው እንግዲህ በመጪው ሰኞ ምንም እንዳላደረጉ ሁሉ ከአፍካ መሪዎች ጋር አብረው ዋንጫ ሊያነሱ የተዘጋጁት።ይህ ለአሜሪካም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ውርደት ነው።ለእዚህም ነው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከየቦታው ተጠራርቶ በአይነቱ ግዙፍ የተባለ ሰልፍ ለማድረግ በመጪው ሰኞ ዋሽግተን ዲሲ ላይ የሚከትመው።ሰኞ መንግዶች ሁሉ ስቴት ዲፓርትመንት አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ ያመራሉ።

የሰልፉን ማስታወቂያ ከእዚህ በታች ይመልከቱ -

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...