ጄኔራል ኃይሌ መለስ
ጄኔራል ኃይሌ መለስ የጎንደር ሕዝብን መግለጫ
ምንጭ = ሳተናው
የጎንደር ህዝብ ወንድሙን አሳልፎ የመስጠት ባህል የለውም። እኔ ከወረታ እስከ ባህርዳር በተደረገው ጦርነት በ1983ዓ.ም ሰባት ጊዜ ሰባት ቦታ ላይ ቆስዬ አዲስ አበባ ሄጀ ልታከም የሚል አጋጣሚ ሊኖረኝ ይችል ነበር፤ነበረኝም።ሂዶ መታከም እችል ነበር ያኔ ደርግ ጨርሶ አልፈረሰም ነበርና። ግን የነገሩን ማለቅ ስለተረዳሁት በቀጥታ በታንኳ ተሻግሬ ዘጌ አርፌ እንደገና ሌላ ታንኳ ይዤ እብናት ነው የገባሁት። እብናት ገብቼም ህዝቡ ትጥቁን እንዳይፈታ መጥቸልሃለሁ ትጥቅህን አትፍታ ነው ያልኩት ህዝቤን እና ብዙ ሽምቅ ተዋጊዎችን አደራጅቼ እየተዋጋሁ ለ5 ዓመታት ያክል ስዋጋ ቆይቻለሁ።
በዚያን ሰዓት በኔ በግል በደረሰብኝ ችግር፤ ቤተሰቦቼ ላይ በደረሰ ሰቆቃ፤ ወያኔ እኔን አሳልፈው እንዲሰጡ እንዲሁም አብረው በሚታገሉ ወገኖቸም ዘንድ የደረሰው ግፍ ይሄ ነው ተብሎ ሊገለፅ የሚችል አይደለም። ይሄ ሁሉ ችግር እያለብኝ ግን እጄን ለጠላቴ ለወያኔ አንስቼ ልሰጥ ፈፅሞ አልዳዳኝም። ወጣሁ ቆርጨው በአዲስ አበባ አቋርጨ ቀጥታ በኬንያ ነው የወጣሁት! ከኬኒያ እንደገና ሱዳን ገብቼ ነው ውጊያ የጀመርኩት። ያገሬ ህዝብ ጎንደር እኔን አሳልፈህ እንዳልሰጠህ እንዲያውም የኔን ሞት እንደሞትክ ሁሉ የጀግናው ወንድማችንና ልጃችን የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ህይወትም ማትረፍ መቻል አለብህ እና አምኖ አድነኝ ብሎሃል፤ወንድምህ ነው አድነው፤ ተዋደቅለት። ሌላም ልጨምር! የምችለው ነገር ብኖር ሁሉም ሸዋ፣ወሎና ጎጃም እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይሄ ሁሉ ግፍና ሰቆቃ በአማራው ላይ የሚሆነው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ስለሆነ አማራው ብቻ ሳይሆን መነሳት ያለበት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተነስተህ ይሄ ያገር ጠንቅ የሆነውን ወያኔ ንቀል፤ጊዜው አሁን ነው ተጀምሯል፤ከአሁን በኋላ ይሄ ነገር መክሸፍ የለበትም።
ከዚህ በፊት ብዙ አጋጣሚዎች አምልጠውናል፤ይሄ ግን ሊያመልጠን አይገባም። በድጋሜ ይሄንን የመሰለው ወርቃማ ጊዜ ሊያመልጠን አይገባም እና ተነስ የኢትዮጵያ ህዝብ። ይህ የመጨረሻ ጥሪዬ ነው የማቀርብልህ። በተለይ በተለይ የደቡብ ጎንደር ህዝብ ባለፈው ጊዜ ብዙ እንዳስቸገርኩህ አውቃለሁ።አሁን የማስቸግርህ ለመጨረሻ ጊዜ ነው፤ተነስ! ተነስ! ተነስ! ይህንንም ደግሞ ላንተው መዳን ሲባል ነው፤አንተ ህይወትህ እንዲቀጥል ነው የምለምንህ። እና እስከዛሬ እንዳላሳፈርከኝ ሁሉ ዛሬም እንደማታሳፍረኝ ፅኑ ዕምነቴ ነው።
በመጨረሻም የጎንደር ህዝብ ማድረግ የሚገባህን ተጋድሎ ሁሉ ማድረግ አለብህ። በምንም ታዓምር ወያኔን አሳፍረኸዋል፤ አሁንም ደግመህ ደጋግመህ አሳፍረው።ሌላውም ህዝብ ይሄንን የጎንደርን ህዝብ ማገዝ መቻል አለብህ። በምንም ተዓምር ወያኔ ሁልጊዜ አሸናፊ እየሆነ መውጣት የለበትም፤ይሄ የመጨረሻው መሆን አለበት። እያታለለ አንድ ጊዜ ኦሮሞውን፣ ሌላ ጊዜ አማራውን፣ሌላ ሰሞን ደሞ አኙዋኩን እንዲሁም ሱማሌውን እየደበደበና እርስበርስ እያባላ የሚነግድበት ካርድ ለመጨረሻ ጊዜ ማቃጠልና ማስቆም አለብህ።
ይሄንን መሰሪ ቡድን ማጥፋትና ነፃነትህን ማገኘት መቻል አለብህ።
ጀኔራል ሃይሌ መለስ።
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ መግለጫ
ምንጭ - ዘሐበሻ
ሐምሌ 15, 2008 ኖርዌይ !!
ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ከተቋቋመበትመሰረታዊ ዓላማዎች አንዱና ዋነኛው በሃገራችን ኢትዮጵያ ያለውን ኢፍትሃዊና የአንድ ዘር የበላይነት አገዛዝ የሰፈነበትን አምባገነን ሥርዓት በማውገዝ እንዲሁም በመታገል ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ማለትም የዜጎችን እኩልነትየተረጋገጠባት፣ ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት ፣ የዜጎች ሰብዓዊናዲሞክራሲያዊ መብቶች የተከበረባትና የተረጋገጠባት ፣ የሕግ የበላይነትየሰፈነባት፣ እንዲሁም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በኩል አይን የሚታይባትዴሞክራሲያዊት ኢትዮጲያን ለመገንባት የሚደረገውን ህዝባዊ ትግል መደገፍናብሎም በአጋርነት መቆም ነው፡፡
እኛ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት አባላት የወያኔ መንግስትበመላው አገሪቱ ዜጎችን በማናለብኝነት ከትውልድ ቦታቸውና ከመኖሪያአካባቢያቸው ማፈናቀልም ሆነ ይዞታቸውን በጠመንጃ አፈሙዝ መንጠቅ አንድንአገር አስተዳድራለሁ ያለን መንግስት ለሕዝብ ያለውን ንቀት ያሳያል። ወያኔ ስልጣንበጠመንጃ ከያዘ ጀምሮ በመላው አማራ በጉራ ፈርዳ ፣ በጋምቤላ ፣ በኦሮሚያ ክልል በማስትር ፕላን ሰበብ፣ እንዲሁም አዲስ አበባዜጎችን የመኖሪያ ቤታቸውን ከሀና ማርያም፣አቃቂ ቃሊቲ፣ላፍቶ ክፍለ ከተማና ሌሎችም አካባቢዎች ህዝብን ከይዞታቸው ማፈናቀል አሁንደግም በጎንደር ወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄን በጠመንጃ አፈሙዝ ለማፈን የሚደረገውን ትግል በማናለብኘነትና በአምባገነንነትየተወሰደና ሕገ ወጥ እርምጃ ነው ።
በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በጎንደር ከተማ ከወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄን ተንተርሶ በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ ላለፉት ሃያአምስት ዓመታት የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ቀደም ሲል በቤጌምድር በኋላም በሰሜን ጎንደር በአማራነቱ ተከብሮ የኖረ ሕዝብ ስለሆነ ወደትግራይ ክልል መካለሉን በመቃወም ጥያቄዉን በአግባቡ ያቀረበ ቢሆንም ይህን በሰላማዊ መንገድ ላቀረበዉ ጥያቄ አንባገነኑ የወያኔጉጀሌ ቡድን የሕዝቡን ጥያቄ በሃይል ለማፈን የኮሚቴ አባላቱን ማሰርና ማፈን የቀጠለ ሲሆን ኮረኔል ደመቀ ዘዉዴ ለማሰር የሞከረዉንሙከራ ተንተርሶ ሕዝብዊ ማዕበል/ቁጣ ተነስቷል። የሕዝብን ጥያቄ በሃይል ለማፈን እንደማይቻል ትላንት በኦሮሚያ የታየዉን ሕዝባዊአመጽ ዛሬ በታሪካዊቷ ጎንደር ተደግሟል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለፉት25 ዓመታት በአሸባሪውና በፋሽስቱ ወያኔ ቁጥጥር ሥር ከወድቀበትጌዘ አስቶ የፍዳ ዓመታትን እያሳለፈ ሲሆን በእነዚህ ረጅም የመከራ ዓመታት አንድም ቀን ወያኔን ከመታገል የተቆጠበበት ጊዜ ግን አልነበረም:: ወያኔ የማህበረሰቡን እሴትበቁጥጥር ስር ለማስገባት በአካሄደው አረመኔያዊ ድርጊት አሉ የሚባሉትን ማህበራዊ እሴቶቻችንን በሙሉ ተራ በተራ ያፈራረሳቸዉና በራሱ አሻንጉልቶች በመተካት ፀረ ማህበረሰብ ዘመቻውን በሰፊው ገፍቶበታል። ይህ አንባገነን ሥርዓት ኢትዮጵያ እንደሃገር ሕዝቧምእንደ ሕዝብ ቀድሞ በነበረዉ ሃገራዊ ትስስር እንዳይቀጥል ለእኩይ ዓላማዉ ሲል ብቻ የሃገሪቷን ሕዝቦች በዘርና በቋንቋ በመከፋፈልየሃገሪቷን ሕዝቦችን ሲያጣላና እርስ በርሳቸዉ እንዳይተማመኑ በከፍተኛ ጥንቃቄ የሰራና በሃገሪቷ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰቦችወይም ብሄረሰቦች ከራሳቸው ዘር ውጭ ሌላውን ማመን የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ እየገቡ ለመሆናቸው በቅርቡ እየተፈፀሙ ያለውድርጊት ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው። በጋራ ሁላችንም በሰውነታችን ብቻ ልንቀበላቸው የሚገቡ፣ ዘርን፤ ቋንቋንና ባህልን ተሻግረውሊያስተሳስሩን የሚገቡ ጉዳዮቻችንን እያፈራረሳቸዉ ይገኛል።
የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት በህዝብ ያልተወከለ አገሪቱን የግዛት አንድነት ያላስጠበቀ፤ የሃገሪቷን አኩሪ የነፃነትና የአንድነትን ታሪክ ገድልየካደና የናደ እኩይ ቡድን ስለሆነ ይህ ቡድን ከህዝብ ጫንቃ ላይ ማስወገዱ አማራጭ የሌለዉ ወቅታዊና ሃገራዊ ግዴታ መሆኑንዲሞክራሲያዊ ለዉጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት በጽኑ ያምናል። በወልቃይት ጠገዴ መሪዎች ላይ ይህ አንባገነን ታጣቂዎችንከትግራይ ወደ ጎንደር በመላክ የኮሚቴ አባል የሆኑትን ኮለኔል ደመቀንና ሌሎችንም ለማፈን እንዲሁም ላለፉት ዓመታቶች በወልቃይትጠገዴ ማንነት ጥያቄ አቅራቢዎች ላይ የጦር ሀይል፤ ደህንነትና ፖሊሶችን በማዝመት ጥያቄዉን ለማኮላሸት ቢሞክርም የወልቃይትጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ጥያቄዉን እንዲያቀርቡለት የመረጣቸዉ የኮሚቴዉ አባላቶች ለሚደርስባቸዉ ወከባና እንግልት ሳይበገሩየተጣለባቸውን አደራ ያለማወላወል በመጠበቅ ባካሄዱት አኩሪ የትግል ገድል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ታሪኩን በወርቅ ቀለም ፅፏል።ዘረኛው ወያኔንና ተባባሪዎቹ የማይገባቸውና እስከ ዛሬ ያልተረዱት የሕዝብ ፍላጎት ብሎም ቁጣንውን አሻፈረኝ አልገዛም ብሎ ማመጽወቅቱ ጠብቆ የሚመጣ ክስተት ነው። የወያኔ መንግስት ይሄንን ሕዝባዊ መነቃቃት ለማጥፈት በሌሎችም ላይ እንደሚያደርገው ሁሉየተለያዮ ዘዴዎችን በመጠቀም ያላሰለሰ የሞት ሽረት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።አሁንም በተግባር እየፈፀመ ነው።
ዴሞክራሲያዊ ውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አምባገነኑ ህውሃት(ኢህአዴግ) በሰላማዊና በንፁሃን ዜጐች ላይ የወሰደውንኃላፊነት የጐደለው እርምጃ አጥብቀን እያወገዝን የኢትዮጵያ ሕዝብ ልዩነቱን ወደ ጐን በመተው ይህንን ዘረኛ ና አምባገነን ስርዓትለማስወገድ ከመቸውም ጊዜ በላይ ተባብሮ እንዲነሳ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። እንዲሁም በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ሊያሰሙበወጡ ዜጎች ላይ የወሰደውን አረመኔያዊ እርምጃ በጥብቅ እያወገዘን የጎንደር ሕዝብ እያደረገ ያለውን ፍትሃዊ ትግል ሙሉ በሙሉእንደግፋለን።ለተጀመረው የነጻነት ትግል ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አጋርነቱን ይገልጻል።
ወያኔ በማስወገድ የሃገራችንን አንድነትና ዳር ድንበር እናስከብር!!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!!
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ !!!!
ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment