ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, July 12, 2016

ጎንደር ኮ/ል ደመቀ ከበባውን ሰብረው ከሕዝቡ ጋር ተቀላቅለው እራሳቸውን እየተከላከሉ ነው


ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ 

¨ጎንደር ጦርነት አለ!" ጋዜጠኛ ተፈራ አስማረ 1984 ዓም ¨

ህወሓት ከ25 ዓመታት በፊት ሶስተኛ አብዮታዊ ሰራዊትን ሽሬ እንዳስላሴ ላይ ካጠቃ በኃላ ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመው ጎንደር ላይ ነበር።ጎንደር ከተማ እና ደብረ ታቦር ከተማን ልክ በአምቦ እንደሆነው ሁሉ ሁለት ጊዜ ገብቶ በሕዝቡ ተባሮ ወጥቷል።በእዚሁ ሳብያም በርካታ ወጣቶች በግፍ ተገድለዋል፣በግዞት ወደ እስር ቤት ተግዘዋል የቀሩት ለስደት ተዳርገዋል።ለህወሓት የጎንደር ጉዳይ ሲነሳ ልቡ የሚመታው ካለነገር አይደለም።የህዝቡን የስነ ልቦና ደረጃ እና ቁርጠኝነት ላይ በቂ ልምድ አለው። ለእዚህም ነው በ1984 ዓም ጋዜጠኛ ተፈራ አስማረ በወቅቱ በሚታተመው የግል ጋዜጣው ላይ በፊት ገፁ ላይ ¨ ጎንደር ጦርነት አለ!¨ በሚል ርዕስ ባወጣው ዜና አማካይነት ህወሓት በከባድ ወንጀል ከሶት የነበረው። በወቅቱ ተፈራ ¨ጦርነት ለመኖሩ የቪድዮ ማስረጃም አለኝ ¨ ማለቱ እና ህወሓት ግን ከዜና ሁሉ አጥብቆ የሚፈራው ዜና ¨ጎንደር ጦርነት አለ¨ የሚለው መሆኑ የታወቀው ከ24 አመታት በፊት ነበር።

¨ገበያችን ጎንደር ነው አታጣሉን¨ የትግራይ ገበሬ 1980 ዓም


ህወሓት ኃላፊነት በማይሰማቸው፣ቤተሰባዊ መሰረት የሌላቸው እና ለሀብት ንብረት በሚስገበገቡ መሪዎች መመራቱ ክፉኛ ጎድቶታል።በትጥቅ ትግሉ ወቅት የህወሓት ካድሬዎች በህወሓት አመራሮች ከሚሰጣቸው መመርያ ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው  የአማራውን ሕዝብ ነፍጠኛ የሚል ታቤላ ለጥፎ የትግራይን ሕዝብ ከአማራ ማሕበረሰብ ጋር ለማጣላት ብዙ ደክሟል።በሽሬ የተገኘ አንድ የህወሓት ካድሬ የትግራይ ገበሬ ሰብስቦ የለመደውን የአማራ ሕዝብ የሚያጥላላ ንግግር ሲያደርግ አንድ ገበሬ ይነሱ እና ¨ አንተ የተላክበትን አራግፈህ ትሄዳለህ ለእኛ ትግራዮች ግን ቅዳሜ ገበያችን ደባርቅ ጎንደር ነው አታጣላን¨ አሉት። ተመሳሳይ ንግግር ለአቶ ታምራት ላይኔ መነገሩን በወቅቱ በክርክሮቹ ወቅት የነበሩ በተለያዩ መፅሄቶች ላይ ስያወሱት የነበረ ጉዳይ ነው። ዛሬም ህወሓት አፉ እንዳመጣ በመናገር ለስልጣን መጠበቅያው በህብረት ለዘመናት የኖረውን የአማራ እና የትግራይ ማሕበረሰብ ለማጣላት የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም።ስለሆነም ይህንን እኩይ ተግባር ለማክሸፍ የትግራይ ሕዝብ ለመጪው ዘመን ሲል ከፍትህ ጋር መቆም እና ህወሃትን ከቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር መቃወም የቀረበለት ብቸኛ መንገድ ነው።

ጎንደር ጦርነት አለ


ሐምሌ 4 ለ 5/2008 ዓም ከለሊቱ 10 ሰዓት የወልቃይት ጉዳይ ከሚከታተሉት የኮሚቴ አባላት አንዱ ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ ቤታቸው ይቆረቆራል። ፊታቸውን ጭንብል ያጠለቁ የፌድራል ፖሊስ መሆናቸውን የሚናገሩ እና እውነታው ግን ከትግራይ በሚስጥር ወደ ጎንደር የተላኩ ግለሰቦች ነበሩ።ኮ/ል ደመቀ ከመንግስት ከመጡ ሲነጋ እንደሚያናግራቸው እና አሁን ግን ሌሊት ስለሆነ  ከበሩ ላይ እንዲሄዱ ይነግራቸዋል። ሆኖም የህወሓት ታጣቂዎች ፈቃደኛ አልነበሩም። በመቀጠል  ታጣቂዎቹ በኃይል ለመግባት ሲሞክሩ ተኩስ ይከፈታል።ሁለቱ ታጣቂዎች ይወድቃሉ።ይህ ዜና ለጎንደር ብሎም እስከ አርማጮ ድረስ ይሰማል። የጎንደር ሕዝብ ኮ/ል ደመቀን አናስነካም ብሎ የከበቡትን ፈድራሎች መልሶ ይከባል።ቀኑን ሙሉ እስከ ቀትር በኃላ ድረስ ይታኮሳል።የህወሓት ንብረት ናቸው ያላቸውን የሰላም ባስ አውቶብስ፣ኮ/ል ደመቀን ወደ ትግራይ ለመውሰድ የመጣው መኪና እና ሌላ የፖሊስ መኪና ጨምሮ ይቃጠላል።የጎንደር ዩንቨርስቲ ተማሪ፣ ከአርማጮ የመጡ ታጣቂዎች በስድስት አውቶብስ እና የከተማው ነዋሪ ከሌሎች የገጠር ቀበሌዎች ጭምር ወደ ጎንደር ከተማ ይገባሉ። ከምሽቱ በፊት ኮ/ል ደመቀን ለማባባል የህወሓት ሰዎች የገዛ ዘመዶቹን አግባብተው እጁን እንዲሰጥ ይልካሉ። የተላኩት የኮለኔሉ ዘመዶች ግን ኮ/ል ደመቀን እንዳገኙ ያገኙትን መሳርያ ይዘው አፈሙዛቸውን ወደ ህወሓት ነፍሰ ገዳዮች አዞሩ። የዕለቱ ጀንበር ሳትጠልቅ ኮ/ል ደመቀ ከሕዝቡ ጋር ሆኖ ከበባውን ሰብሮ አመለጠ።በአሁኑ ሰዓት ከሕዝቡ ጋር ሆኖ ከህወሓት ታጣቂዎች ጋር ሆኖ  እየተዋጋ መሆኑን ኢሳት በምሽቱ የራድዮ ዘገባ ከስፍራው ያናገራቸውን የአይን እማኞች ቃል  አስደምጧል።

ባጠቃላይ ከ24 አመታት በፊት ህወሓት የፈራው እና ጋዜጠኛ ተፈራ አስማረን መቀጣጫ ያደረገበት ¨ ጎንደር ጦርነት አለ¨ የሚለው ዜና ገዝፎ እና አድጎ በሩ ላይ መጥቷል።ህወሓት አገሩን ሁሉ እየገዛ ትግራይን ከሌላው ኢትዮጵያ ለመለየት ባለው ሕልም  ምክንያት የትግራይን ሕዝብ ለማስደነበር እና ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ለመለየት የሚያደርገው ጥረት  መልሶ እራሱኑ እንደሚፈጀው ቢረዳ ጥሩ ነበር።የአባይ ወልዱ እና ወዳጆቻቸው የአስተሳሰብ ችሎታ ጥግ  ከአፍ እስከ አፍንጫ ድረስ ባይሆን እና የዛሬን ሳይሆን አሻግረው መጪው ትውልድ ሕልውናው እንዳየበጠበጥ ማሰብ ቢጀምሩ ጥሩ ነበር።አሁን እንደሚታየው ግን ፈፅሞ ለአቅመ መጪውን ማሰብ ደረጃ እንዳልበቁ እና ጎንደርን በደም ለመንከር ተጨማሪ ሰራዊት እያስገቡ መሆኑ ተሰምቷል። የጎንደር እና አርማጮ ህዝብም እራሱን የመከላከል ሥራ ሴቶች ከበርበሬ እስከ ክላሽ ይዘው የወጡበት ፍልምያ መሆኑን እየገለፁ ነው። እስከ ሰኔ 30 ድረስ መንግስት ምላሽ እንዲሰጠው የጠየቀው የወልቃይት ግፉአን ማኅበርም ባወጣው መግለጫ የህወሓት እብሪት አደብ እንዲገዛ ሁሉም ኢትዮጵያዊ  እንዲነሳ ጥሪ አቅርቧል። 


ጉዳያችን GUDAYACHN 
www.gudayachn.com

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...