ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, December 12, 2014

ኢትዮጵያን መውደድ ሕይወትን ከመስጠት ያነሰ እሳቤ እንደሌለው በተግባር ያሳዩት አንዳርጋቸው ፅጌ ዛሬ ታህሳስ 3 ከየመን ከተጠለፉ 172ኛ ቀናቸው ከ172 ቀናት በኃላስ ኢትዮጵያ የት ነች?ኢትዮጵያን መውደድ ሕይወትን  ከመስጠት ያነሰ እሳቤ እንደሌለው በተግባር ያሳዩት በዘመናችን የምንጠቅሳቸው ጀግና አንዳርጋቸው ፅጌ ዛሬ ታህሳስ 3 ከየመን ከተጠለፉ 142ኛ ቀናቸው።
ከ172 ቀናት በኃላስ ኢትዮጵያ የት ነች? በእነኝህ 172 ቀናት ውስጥ ምን ደረሰብን?

- ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እስር ቤት ገባ፣

- የዞን 9 ጦማርያን በእስር ቤት ግርፋት ተፈፀመባቸው፣

- ተማሪዎች በሙሉ ''የኢትዮጵያ ስጋት'' ተብለው በኢህአዲግ ሰነድ ላይ ሰፈሩ፣

- አሸባሪ የሚለው ቃል ''ተመንድጎ'' የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን አገልጋዮች እና ማኅበራትን ሁሉ የመፈረጃ ቃል ሆነ፣

- ከደርዘን በላይ ጋዜጠኞች ከሀገር ተሰደዱ፣ከተሰደዱት ውስጥ አንዱ ህይወቱ ኬንያ ላይ አለፈ፣

- አዲስ ጉዳይ መፅሔትን ጨምሮ ፍትህ እና ሌሎች ጋዜጦች ተዘጉ፣የቆዩ የግል ጋዜጦች ማንበብ ይሻላል ብሎ ህዝቡ የቆዩትን መግዛት ጀመረ፣

- በአዲስ አበባ ዙርያ እና አምቦ ላይ ከመሬት መቀራመት ጋር በተያያዘ በርካታ የኦሮምኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን በጥይት ተመቱ የቀሩት ለእስር ተጋዙ፣

- ኢትዮጵያዊ ትውልድ ያላት ሱዳናዊቷ ማርያም  ክርስቲያን በመሆኗ የሞት ፍርድ ሲፈረድባት መላው ዓለም ድምፁን ሲያሰማ የኢህአዲግ/ወያኔ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ሆነ ስርዓቱ በገዛ ዜጋው ላይ የተወሰነውን ጉዳይ በዝምታ አለፈው።ማርያ ተፈታ ስትሄድ ጣልያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን እስከ አይሮፕላን ጣብያ ድረስ ሄደው ተቀበሏት፣

- የኢትዮጵያ የከፍተኛ ተቋማት ፕሬዝዳንቶች ዋና ተግባራቸው ለኢህአዲግ መስራት እና ምርጫ እንዲመረጥ ማድረግ መሆኑ እና የምመዘኑትም ከእዚህ አንፃር ብቻ  እንደሆነ በሰነድ ተደግፎ ተነገራቸው፣

- ከ70 በላይ ኢትዮጵያውያን በቀይ ባህር ውስጥ መስጠማቸውን ዓለም በሃዘን እየተቀባበለ ዘገበው፣የአሜሪካ አምባሳደር በአዲስ አበባ የሃዘን መግለጫ ለኢትዮጵያ ላኩ፣ኢህአዲግ/ወያኔ እያጣራሁ ነው ብሎ ጉዳዩን ችላ አለው፣

- ኢትዮጵያ የብድር መጠኗ ተመነደገ ያም አልበቃ ተብሎ ኢትዮጵያን ለበለጠ ዕዳ የሚዳርግ ''ሶቨሪን ቦንድ'' ፍለጋ አውሮፓ ተዞረ፣

- ከሳውዲ ባለፈው ዓመት ተባረው የተመለሱ ወገኖቻችን እያዘኑ ተመልሰው ውደ ሳውዲ መሄዳቸውን አዲስ ጥናት አዲስ አበባ ላይ በCRDA  ተገለፀ፣

- አዲስ አበባ ላይ ግን 1 ሚልዮን የሚበልጥ ሕዝብ ውሃ እንደሌለው እራሳቸው አቶ ኃይለማርያም ለጋዜጠኞች በገለፁ በወራት ውስጥ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ተብሎ አሶሳ ላይ በ300 ሚልዮን ብር ድግስ ተበላ፣

- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዘክር (ወመዘክር) ጥንታዊ የኢትዮጵያ ታሪኮች ያሉባቸው በተለያዩ የአውሮፓ ቋንቋዎች የተፃፉ መፃህፍት፣ የነገስታት ደብዳቤዎች፣የጥናት ፅሁፎችን ቦታ ጠበበኝ ብሎ በኪሎ ሸጣቸው፣

172 ቀናት ውስጥ ኢትዮጵያ እንዲህ ከረመች።ለእዚህ ነው ኢትዮጵያን መውደድ ሕይወትን  ከመስጠት ያነሰ እሳቤ እንደሌለው በተግባር ያሳዩት በዘመናችን የምንጠቅሳቸው ጀግና አንዳርጋቸው ፅጌን የምናደንቀው።

ጉዳያችን
ታህሳስ 3/2007 ዓም (ደሴምበር 12/2014)

No comments: