ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, January 11, 2014

የአውሮፓውያን እና የእኛ የገና በዓል አከባበር ለምን ተለያየ? የእኛ ትክክል ለመሆኑ ማስረጃዎች (አጭር ማስታወሻ)


ዛሬ  እዚህ ኦስሎ ውስጥ በተገኘሁበት የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ የገና በዓል መታሰብያ ላይ አንዳንዶች ስለበዓሉ ቀን መለያየት ጥያቄ ሲያነሱ ነበር።ከእዚህ በታች ያለው ፅሁፍም መርሃግብሩ  ላይ ካነበብኩት እረዘም ያለ ፅሁፍ ጥቂቱን እና ስለበዓሉ የተመለከተውን ብቻ ነው።ፅሁፉ በተለያዩ ጋዜጦች እና ድህረ ገፆች ላይም  ወጥቷል።

ከጥንት ጀምሮ ሮማውያን እውነተኛ ፀሐይ የተወለደበት ቀን እያሉ ታኅሣሥ 16 ቀንን ያከሩ ነበር ምክንያቱም በሮማውያን ግዛት የረጅሙ የክረምት ወቅት አብቅቶ በመጀመሪያ ጊዜ የፀሐዩን ብርሃን የሚያዩት በዚህች ቀን ነው፡፡ ሮማውያን በተለምዶ ከዚያ ከሚያኮራምት የክረምት ወቅት በማለፍ ብርሃንና ሙቀትን ስለሚያገኙ ለተክሎቻቸው ልማት ለከብቶቻቸውም የፍንደቃ ወቅት ስለሆነ ለዚህ ብርሃን በየዓመቱ የምስጋና መስዋእትን በመያዝ ሁሉም ወደ ተራራ ጫፍ ላይ በመውጣት መስዋዕትን ያቀርቡ ነበር፡፡

 ክርስትና  እስከ አራተኛ ክፍለ ዘመን ድረስ በስደት ላይ ባልተረጋጋ ሕይወት ውስጥ ስለነበረ   በዓለም ላይ በሰፊው ያልታወቀበት ዘመን ስለነበር  አውሮፓውያን ስለ ጌታችን ልደት ብዙም ትኩረት አይሰጡም ነበር፡፡እንደሚታወቀው ከአራተኛው ክፍለ ዘመን በፊት ክርስትያኖች በሮማውያን ነገስታት ተሳደዋል፣ተገርፈዋል ለአውሬ ተሰጥተዋል።ቤተክርስቲያን እረፍት ያገኘችው በእሌኒ ንግስት ልጅ ንጉስ ቆስጠንጢኖስ ሲነግስ ነበር።

ስለዚህ  ክርስትና በአግባቡ በሕዝቡ ውስጥ እስኪሰርፅ እና የመንግስት ሃይማኖት እስኪሆን ድረስ ሁሉ የፀሐይ አምላክ እንደማንኛውም ሮማዊ በአባቶቻቸው የወረሱትን አምልኮ ነውና መስዋዕትን ይሰዉለት ነበር፡፡ ከ  320ዓም በኃላ  ለመጀመሪያ ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች የሚኖሩ ክርስትያኖች የጌታችን ልደት በታኅሣሥ 29 ማክበር ጀመሩ፡፡

በ354 ዓ.ም. ግን ሮማዊው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊብሮስ ክርስቲያኖች ‹‹ሳትሩን›› እየተባለ በሚጠራው የፀሐይ አምላክ ፈንታ መንፈሳዊ የፍትህ ፀሐይ ክርስቶስ የተወለደበት የደስታና የነፃነት አብሳሪ ልደት በዲሴምበር 25 (ታኅሳስ 16) ቀን እንዲከበር ለዓለም ሁሉ አዋጅ አስተላለፋ፡፡ በወቅቱ ብዙ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት የሊብሮስ አዋጅ አልተዋጠላቸውም ነበር፡፡

 ከዚህ በኋላ አብዛኛዎቹ አብያተ ክርስቲያናት ታኅሣሥ 25 (እ አ አቆጣጠር) እንደ ጌታ ልደት ቀን ተቀበሉ፡፡  የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ግን እስከ ዛሬ ታኅሣሥ 29 የጌታን ልደት ብላ ታከብራለች፡፡ ይህ እለት በመፅሐፍ ቅዱስ እንደተጠቀሰው መጥምቁ ዮሐንስ ጌታችንን በስድስት ወራት ይቀድመዋል(መጥምቁ ዮሐንስ  ልደት ሰኔ 30 ነው) እመቤታችን በመጋቢት 29 በቅዱስ ገብርኤል ብስራት እግዚአብሔር ወልድ ከሥጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በተዋህዶ ሰው ሆኖ ካለ አባት በመንፈስ ቅዱስ ግብር ተፀነሰ።ከ 9 ወር ከ 5 ቀን በኃላ በታህሳስ 29 ተወለደ። ታህሳስ 29 ቀን ትክክለኛ የክርስቶስ የልደት ቀን ነው።አጉስጦስ ቄሳር ሕዝቡን ለቆጠራ በሰበሰበበት ወር ከቆጠራ ሲመለሱ በከብቶች ግርግም እመቤታችን ጌታችንን እንደወለደችውቅዱስ መፅሐፍ ይነግረናል።
////////////////////////////////።።።።።።።።።።።።።።/////////////////////።።።።።።።።።።።።////////////////////።።።።።።።።።///////

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...