ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, January 21, 2014

በኢትዮጵያ አብዮት በየካቲት ወር 1966 ዓም ከፈነዳ በመጪው የካቲት/2006 ዓም ሙሉ አርባ አመት ይሞላዋል (እነሆ የወደፊቱን ለማሰብያ ኦድዮ ክላሲካል ሙዚቃ)

በኢትዮጵያ አብዮት በየካቲት ወር 1966 ዓም ከፈነዳ እነሆ በመጪው የካቲት/2006 ዓም ሙሉ አርባ አመት ይሞላዋል።በእነኝህ አርባ አመታት ውስጥ የሶቭየት ህብረት ርዕዮት እና ወታደራዊ የአምባገነን ስርዓት ለ 17 አመታት መንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ ለ 23 አመታት አስተናግደናል።ዛሬ ላይ ሆነን ያለፈው አርባ አመትን ስንተነትነው ብንውል ብዙም የሚፈይድ ነገር አይኖረውም።በመጪው አመታት ግን እንዳለፉት አርባ አመታት መቀጠል አለብን ወይ? ትልቁ ጥያቄ ነው።ጥያቄው የሁላችንም ነው።

ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ፍልስፍናችን የት ነው? በዘርፉ የሰለጠኑ ምሁራን ብዙ ሊሉበት የሚገባ አጋጣሚ ላይ ነን።የት ነበርን? አሁን የት ላይ ነን? ወደፊትስ ወዴት እና እንዴት መሄድ አለብን? የአንድነት ኃይሎች ከበታኝ ኃይሎች ጋር ምን ያክል እርቀት መሄድ ይችላሉ? ኢትዮጵያዊነት የፖለቲካ ፍልስፍና ጠርቶ መውጣት የለበትም ወይ? ብዙ ጥያቄዎች አሉ።እነሆ የወደፊቱን ለማሰብያ (ኦድዮ) ክላሲካል ሙዚቃ። ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር!

የበለጠ ለማንበብ ሊንኩን ይክፈቱ

የኢትዮጵያ የተቃውሞ የፖለቲካ መድረክ ኢትዮጵያን በተመለከተ ግልፅ የፖለቲካ አቅጣጫ መያዝ የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሷል (ከጉዳያችን ጡመራ) 

No comments:

የምዕራቡ ዓለም በተለይ አሜሪካ ለዩጎዝላቭያ መፍረስ ምን አድርጋ እንደነበር የሚያሳይ ጥናታዊ ፊልም ከህወሓት ደጋፊ እስከ የፅንፍ የኦሮሞ ብሔርተኝነት አራማጆች፣ከአማራ አክራሪ ብሔርተኝነት እስከ ኢትዮጵያዊነት ይቅደም የምንል ሁሉ በትዕግስት እንመልከተው።

ፊልሙን ከተመለከትኩ በኃላ እነኝህ ነጥቦችን ያስታውሱ - ኢትዮጵያ ውስጣዊ የፖለቲካ ግጭቶቿ ታሪካዊ ዳራ እና ስነልቦናው ከዩጎዝላቭያ ጋር አይመሳሰልም።ይህ ማለት ግን ለኢትዮጵያ ካልሰራን አደጋ የለብንም ማለት አይደለም:: ...