ጉዳያችን/ Gudayachn
ታኅሳስ 28/2011 ዓም (ጃንዋሪ 6/2011 ዓም)
================
ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የነበረው አገዛዝ ግልጥ የሆነ ብሔራዊ ጭቆና በልማት ስራዎች ላይ ሲያሳርፍ ታይቷል።ከደብረ ብርሃን አዲስ አበባ ያለውን የአስፋልት መንገድ ለመስራት ከአስር ዓመት በላይ ያውም መንገዱ ከተቆፋፈረ በኃላ ፕሮጀክቱ ሲጎተት እንደነበር የአደባባይ ምስጢር ነው።ይህ ሕዝብ የሚያወራው እና 'ፀሐይ የሞቀው' በደል ነው።ስለቱሪዝም በሚወራባት ሀገር በርካታ ቅርሶች ያላት አንኮበር ከተማን ከደብረ ብርሃን ለማገናኘት አንድም ሥራ ሳይሰራ መኖሩ ብዙዎችን ብዙ አስብሏል።የቀደሙት ገዢዎቻችን በቢልዮን የሚቆጠር ዶላር ሕፃን ልጅ እንደፈረፈረው ደረቅ ዳቦ ሲጫወቱበት ሕዝብ በአቧራ መንገድ እየሄደ ለአይን ትራኮማ በሽታ ይዳረግ ነበር። በሀገራዊ ሀብት እኩል ተጠቃሚነት የሚለው አነጋገር ለቅንጡ የቀደሙት የህወሓት ገዢዎች በቀላሉ አይገባቸውም።የተገፋው ሕዝብ ግን ያውቀዋል።
የደብረ ብርሃን አንኮበር መንገድ በአቧራ ተሸፍኖም በርካታ ቱሪስቶች አስቸጋሪውን መንገድ እየሄዱ ቦታውን ለመጎብኘት ጥረት አድርገዋል።አሁን በዶ/ር አብይ ዘመን የመንገዱ ሥራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን አሳይቷል። ቪድዮውን ከስር ይመልከቱ።
ቪድዮ = ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ታኅሳስ 28/2011 ዓም
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

No comments:
Post a Comment