ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, October 3, 2017

ሀገር ወዳዷ ድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ ስትታወስ

ጉዳያችን /Gudayachn
መስከረም 23/2010 ዓም (ኦክቶበር 3/2017)

የፊቱን እየተረተርን የቀደመውን እየረሳን መሄድ አንዱ ክፉ ልማዳችን ነው። በኢትዮጵያ ሴት ድምፃውያን ውስጥ ከፈር ቀዳጆቹ ተርታ የምትመደበው ብዙነሽ በቀለየቀደመው ትውልድ ኮከብ ሆና አልፋለች። ብዙነሽ የኢትዮጵያን ጦር ሰራዊት በሰሜን በነበረው የሀገር አንድነት የማስከበር የግዳጅ ግንባር ሰራዊቱን ለማበረታታት በርካታ ጉዞዎች አድርጋለች።ለሕይወቷ ማለፍ አንዱ ምክንያትም ሰራዊቱን ለማበረታታት የሙዚቃ ስራዋን ከሌሎች አርቲስቶች ጋር አቅርባ ስትመለስ ሻብያ አርቲስቶቹን ለመግደል መንገድ ላይ ባጠመደው ፈንጅ በደረሰው አደጋ ብዙነሽ በጆሮዋ ላይ በደረሰባት ጉዳት ሳቢያ ነበር።

ብዙነሽ በአደጋው ምክንያት የደረሰባትን የጆሮ ህመም ለማዳን ለሕክምና በኢትዮጵያ ሕዝብ እና በወቅቱ በነበረው የደርግ መንግስት እንዲሁም የሙያ አጋሮቿ ጥረት ሕክምና በአሜሪካ እና ሩስያ ሕክምና አግኝታ ነበር። ሆኖም ግን ሕክምና ካገኘች በኃላም በፈንጅ አደጋው ሳብያ የደረሰባት ህመም ለሕይወቷ ማለፍ አንዱ ምክንያት መሆኑ ይታወቃል። በእዚሁም ሳብያ ብዙነሽ በ54 ዓመቷ ሰኔ 16/ 1982 ዓም ከእዚህ ዓለም በሞት ተለየች።
ስለ ብዙነሽ በቀለ የእኔ ትውልድ ብዙ የሚያውቀው ነገር የለም። ብቃት ያላቸው መርሃ ግብሮች በራድዮ እና ቴሌቭዥን ሲቀርቡ አይታዩም።ብዙነሽ ግን ሀገር ወዳድ ብቻ ሳትሆን በእርሷ ትውልድ የነበሩትን ሴቶች ድፍረትን እና ሙያቸውን ካለምንም መሸማቀቅ እንዲያቀርቡ ፈር ከቀደዱት ውስጥ ነች።ይች ለሀገሯ አንድነት ስትለፋ በደረሰባት የጤና ጉዳት ለሞት የተዳረገች ጀግና ትውልድ ወደፊትም እንዳይዘነጋ ማድረግ ተገቢ ነው።እኛ መቸም ጀግኖቻችንን ማክበር አለመደብንም።በፈር ቀዳጆቻችን ስም ሙዜም መገንባት ወይንም የሚታወሱበት እና መጪው ትውልድ ከእነርሱ ተምሮ ለበለጠ ሃገራዊ ተግባር እንዲተጋ የማድረግ ሥራ ላይ ገና ብዙ ይቀረናል።የብዙነሽ ጉዳይም የተረሳ እንዳይሆን ነው ''ድረ ገፅ እና ወረቀት የያዘውን አይለቅምና'' ለመጪው ትውልድም ሆነ ለአሁኑ ማሳሰቢያ ይሆን ዘንድ ጉዳያችን ይችን ትንሽ  ማስታወሻ ስለ ብዙነሽ ለማስቀመጥ ወደደች።

ስለ ብዙነሽ በቀለ አጭር ጥናታዊ ፊልም  


ብዙነሽ ከእዚህ ዓለም ከመለየቷ አንድ ወር በፊት ከስራዎቿ ውስጥ ለመጨረሻ ጊዜ መድረክ ላይ የታየችበት ዜማ  (ከስር)



የእናት ወለታዋን (ከስር)


ጉዳያችን /Gudayachn
 www.gudayachn.com

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...