ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, October 28, 2017

ኦስሎ ኖርዌይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የምትጫረተው ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ሀገር ቤት ያሉት ገዳማት የነገ ጥሪት ነው







  • ነገ የቤተ ክርስቲያን አንድነት ተመልሶ አባቶቻችን በአንድነት ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተዳድሩ የቤተ ክርስቲያናችን እያንዳንዱ በውጭ ያፈራቸው ሀብት በማዕከል ይተዳደራል።
  • ሁሉ ነገር በድረ ገፅ አይፃፍም።የመገንዘብ አቅማችንን ተጠቅመን ጉዳዩን እንረዳው። 
  • በተለይ በአሜሪካ እና ሌላው ዓለም ያላችሁ እየተለመናችሁ ያላችሁት ለማክዶናልድ ከምታወጡት 20 እና 30 ዶላር ነው።
  • በእዚህ ቤተ ክርስቲያን ግዥ ሳቢያ ቤተ ክርስቲያን በውጭ ማዕከሏ የምታደርገው ሐዋርያዊ ጉዞ ያድጋል፣ የኢትዮጵያ ተሰሚነት ይጨምራል።
  • በሁሉም መልክ ተፅኖ ፈጣሪነት ያሳድጋል።ይህ እንግዲህ ከመንፈሳዊው ጥቅም በዋናነት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። 
  • እኛም ማሰብ ያለብን የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚሰራ ስልታዊ ሥራ ላይ ነው። 
  • ከስልታዊ ስራዎች ውስጥ አንዱ በውጭ ሃገራት እንደዚህ ቁልፍ የሆኑ ቦታዎች እና ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ንብረት እንዲሆን መስራት ነው። 
  • ቤተ ክርስቲያን የከፈተችው ጎፈንድ ሊንክ ከእዚህ በታች ተያይዟል። አነሰ የሚባል የለም።የእኔ የሻይ ምን ሊሰራ ነው ማለት ግን ከብዛት ለውጥ እንደሚያመጣ አለማሰብ ነው።



ኦስሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃያማኖት ቤተ ክርስቲያን ከሶስት ቀናት በኃላ በኦስሎ ለሽያጭ የቀረበ በ1900 ዓም እ ኤ አ የተመሰረተ ቤተ ክርስቲያን ለመጫረት በዝግጅት ላይ ነች።የቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመናን በግላቸው ከመበደር አንስቶ ባላቸው አቅም እየተረባረቡ ነው።የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ይህንን ቤተ ክርስቲያን በጨረታ ማሸነፍ ማለት ብዙ ነገር ማለት ነው።

በመጀመርያ ደረጃ አሁን ላለው ምእመን በእርጋታ አምልኮት የምፈፅምበት እና አሁን በአብነት ትምህርት ላይ ያሉትን ጨምሮ የበለጠ ልጆችን ማፍራት የመቻሉ ጉዳይ አንዱ እና የቅርብ ጥቅሙ ነው። ክዚህ ባለፈ ግን በሰሜን አውሮፓ ወደፊት ቤተ ክርስቲያን ለምታደርገው ሐዋርያዊ አገልግሎት ቁልፍ ሥራ ነው።አሁን እዚህ ሀገር ተወልደው የሀገሩን ባህል እና ልማድ ሁሉ ጠንቅቀው የሚያውቁ ልጆች የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርት ከአባቶቻቸው እግር ስር መማራቸው ነገ ለሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲነሱ እና ለአውሮፓ የተረፈ ሥራ ለመስራት እንደሚችሉ ምንም ጥርጥር የለውም።አውሮፓ በሃይማኖት የሚያድነው የሚፈልግበት ሰዓት ነው። የእዚህ ትውልድ ሥራ ነገ ህፃናቱ አድገው ለሚሰርቱ ሥራ ቁልፍ የሆነውን ህንፃ አዘጋጅቶ መጠበቅ ነው።
በሌላ በኩል አንዳንድ ምእመናን ይህ ቤተ ክርስቲያን ሀገር ቤት ላሉት ገዳማት የሚፈይደው ነገር እንደሌለ ይገምታሉ።ይህ ፈፅሞ አላዋቂነት ነው።ነገ የቤተ ክርስቲያን አንድነት ተመልሶ አባቶቻችን በአንድነት ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተዳድሩ የቤተ ክርስቲያናችን እያንዳንዱ በውጭ ያፈራቸው ሀብት በማዕከል ይተዳደራል።ያን ጊዜ አሁን የገዛነው ህንፃ ዋጋው ይጨምራል።ቤተ ክርስቲያን በውጭ ማዕከሏ የምታደርገው ሐዋርያዊ ጉዞ ያድጋል፣ የኢትዮጵያ ተሰሚነት ይጨምራል።በሁሉም መልክ ተፅኖ ፈጣሪነት ያሳድጋል።ይህ እንግዲህ ከመንፈሳዊው ጥቅም በዋናነት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። 

አባቶቻችን በኢየሩሳሌም ገዳማትን ያላቸውን ጥሪት እየያዙ ስገዙልን እና ለትውልድ ሲያስተላልፉ የኖሩት ለመጪው ትውልድ ነው። እኛም ማሰብ ያለብን የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚሰራ ስልታዊ ሥራ ላይ ነው። ከስልታዊ ስራዎች ውስጥ አንዱ በውጭ ሃገራት እንደዚህ ቁልፍ የሆኑ ቦታዎች እና ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ንብረት እንዲሆን መስራት ነው። 
የኦስሎ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የመጫረት አቅሟ ከፍ እንዲል በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲያግዙ እና ትኩረት እንዲሰጡት ይህ በአሜሪካ እና ሌላው ዓለም እንዳለው ያለ ጉዳይ አይደለም ቁልፍ የቤተ ክርስቲያኗ ጉዳይ ነው።

ሁሉ ነገር በድረ ገፅ አይፃፍም።የመገንዘብ አቅማችንን ተጠቅመን ጉዳዩን እንረዳው። በተለይ በአሜሪካ እና ሌላው ዓለም ያላችሁ እየተለመናችሁ ያላችሁት ለማክዶናልድ ከምታወጡት 20 እና 30 ዶላር ነው።ሁላችሁም የእኔ ትንሽ ነው ሳትሉ ማድረግ ከቻላችሁ የቤተ ክርስቲያን የመወዳደሯ አቅም ከፍ ይላል። በአጥብያችሁ ብዙ ቀዳዳ ይኖር ይሆናል።ለሀገር ቤት ገዳሞቻችን ሁሉም እኩል የመርዳት አቅም የላቸውም። የኦስሎው በተለየ መልክ ተመልከቱት።አሁን ለጨረታ የተለያዩ አካሎች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ለመፎካከር እየመጡ ነው። ጉዳዩን ትኩረት ሰጥታችሁ አሁን ባሉት ሶስት ቀናት ውስጥ የአቅማቹን ብታደርጉ ለውጥ እናመጣለን። ቤተ ክርስቲያን የከፈተችው ጎፈንድ ሊንክ ከእዚህ በታች ተያይዟል። አነሰ የሚባል የለም።የእኔ የሻይ ምን ሊሰራ ነው ማለት ግን ከብዛት ለውጥ እንደሚያመጣ አለማሰብ ነው።ይህንን ጨረታ አስመልክቶ ይህ የመጨረሻ ፅሁፍ ነው።መቼም በድረ ገፅ የማይፃፉ ብዙ ነገሮች አሉ (ይህ ማለት ለቤተ ክርስቲያን ያለው ጥቅም አንፃር ከእዚህ ሀገር ሕግ አንፃር   ቤተክርስቲያኒቱን ለመፎካከር እየመጡ ያሉትን ማለት ነው) እና እባካችሁ ለቤተ ክርስቲያናችሁ ስልታዊ ሥራ ስሩ ይህንን ጨረታ አግዙ ከማለት ሌላ ምን አይነት ንግግር መናገር ይቻላል። እግዚአብሔር ምስጢሩን ይግለጥልን  እንጂ።
የጎፈንድ አካውንቱ ሊንክ http://www.eotcnor.no/በመላው-ዓለም-ለምትኖሩ-ኢትዮጵያውያን-አ/

የቤተ ክርስቲያኒቱ ድረ-ገፅ http://www.eotcnor.no

ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

No comments:

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...