ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, December 25, 2020

207 አስከሬን በግሬደር ጠርጎ በጅምላ መቅበር ፋሺሽታዊ ተግባር ብቻ ሳይሆን ድርጊቱ የስነልቦና ጦርነትም በህዝቡ ላይ ለመክፈት ያለመ ይመስላል።




  • ድርጊቱን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣የእስልምና እና ሌሎች ቤተ እምነቶች  አጥብቀው ማውገዝ አለባቸው።
  • የአስከሬን አቀባበር ስህተቱን  ለማረም አሁንም  መንግስት ሶስት የመፍትሄ አማራጮች አሉት።
በቤንሻንጉል፣መተከል  በቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ ከትናንት በስቲያ ማንነትን መሰረት ባደረገ በአራት አቅጣጫ በታጠቁ ኃይሎች በደረሰ ጥቃት እስከዛሬ ምሽት ድረስ ከቀይ መስቀል ምንጮች በተገኘው መረጃ  መሰረት 222 ኢትዮጵያውያን ከዓማራ፣ሽናሻ፣አገው እና ኦሮሞ ተወላጆች በአሰቃቂ ደረጃ ህይወታቸውን አጥተዋል።ግድያው በክልሉ ልዩ ኃይል ጭምር መከናወኑን የአይን ምስክሮች ገልጠዋል።በግድያው ላይ አንድ አባት ዘጠኝ ልጆቻቸውን ካጡት ጀምሮ በአንድ ቤተሰብ እስከ 12 የሚደርሱ የቤተሰብ አባላት ተገድለዋል።

ግድያው ከተፈፀመ በኃላም አሁን ውጥረቱ እንዳለ መሆኑ እየተነገረ ሲሆን በመንግስት በኩል ክልሉን ተከትሎ የተወሰደ እርምጃ ገና አልተሰማም። በዛሬው ዕለት በሌ/ጄኔራል አስራት ድኒሮ የሚመራ ከፍተኛ የመከላከያ ባለስልጣን የተመራ ልዑክ ወደ መተከል ተጉዞ በዝግ ስብሰባ የወንጀሉ ተባባሪ እንደሆኑ ከሚታሙት ከክልሉ ፕሬዝዳንት እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ስብሰባ ተቀምጠው እንደነበር  ተነግሯል።

ይህ በእንዲህ እያለ በግፍ የተገደሉት ኢትዮጵያውያንን አስከሬን ክልሉ ለጅምላ መቃብር በተቆፈረ መቃብር እና በግሬደር ከአፈር ጋር እየለወሰ እንዲቀበሩ ሲያደርግ የሚያሳዩ ፎቶዎች በማኅበራዊ ሚድያ ሲዘዋወር ታይቷል።ድርጊቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከፍተኛ ባለሙያ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን አዲስ አበባ ዜና እወጃ ላይ ቀርበው የተሰራው ከሰብዓዊ መብት ጥሰት በላይ መሆኑን ገልጠዋል።በእዚህ የጅምላ ቀብር 207 ኢትዮጵያን በአንድ ላይ በግሬደር እየተጠረጉ መቀበራቸውን በመቃብራቸው ላይ እንደዋዛ በብጣሽ ወረቀት የተፃፈው ፅሁፍ ያሳያል (ከላይ የምትመለከቱት ፎቶ በመቃብራቸው ላይ የተፃፈው ጽሁፍ ነው)።የጅምላ አቀባበሩ በራሱ ከኢትዮጵያዊነት ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስርዓት የወጣ ከመሆኑም በላይ የቤተሰቦችን እርማቸውን አውጥተው የመቅበር  መብት የተጋፋ፣ጥላቻ እና ዘረኝነት የተንፀባረቀበት እና በፋሺዝም ዘመን የነበረውን ድርጊት የሚያስታውስ ነው።ይህንን የፈፀሙ የክልሉ ባለስልጣናት ላይም ሆነ አስፈፃሚዎቹ ሊመረመሩ ይገባል።

የጅምላ መቃብሩ ሌላው የሚያሳየው ጉዳይ ሆን ብሎ ከግድያው በተጨማሪ የስነ ልቦና ተፅኖ በሟች ቤተሰቦች እና ኢትዮጵያውያን ላይ ለመፍጠር የታሰበ ይመስላል።የግድያው ሃዘን በራሱ የሚፈጥረው የስነ ልቦና ተፅዕኖ እንዳለ ሆኖ፣በግሬደር አስከሬን እየገፉ በጅምላ መቅበር ይህንንም በፎቶ አንስቶ ማሰራጨት ሌላው የስነ ልቦና ጦርነት በሕዝቡ ላይ የመክፈት ዓላማ ያዘለ ይመስላል።ስለሆነም ከድርጊቱ ጀርባ ከክልሉ ባለስልጣናት ሌላ እነማን አሉ? ለምን ለቤተሰብ አስከሬን እንዲሰጥ አልተደርገም? በጅምላ ቢቀበሩስ ለምን ስርዓት በያዘ መልክ ቢያንስ የቤተሰብ ወኪል እንዲገኝ እና እንደ እየእምነታቸው እንዲቀበሩ ለምን አልተደረገም? ቀብር የኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ ጉዳይ አንዱ እና ዋናው ክንውኖች ውስጥ ነው።ይህ ማለት ሁሉም የሚተባበርበት ጉዳይ ነው።ስለሆነም ለምን በተቻለ መጠን ህዝቡ ተረባርቦ እንዲቀብር አልተደረገም?

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣የእስልምና እምነት እና ሌሎች የዕምነት አካላት ሁሉ ግድያውን ከማውገዝ በላይ የጅምላ አቀባበሩ ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ሰውኛ መልክ የሌለው በመሆኑ ድርጊቱን አውግዘው መግለጫ መስጠት እና ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈፀም ማሳሰቢያ መስጠት አለባቸው።አሁንም የተፈፀመውን ስህተት ለማረም መንግስት  ሶስት አማራጭ መንገዶች ሊኖሩት ይችላሉ። እነርሱም -

1) ኬሚካል እረጭቶ እንደገያ የቀብር ስርዓቱን የሚያስተካክልበት መንገድ ካለ ማስተካከል እና በየቤተ ዕምነታቸው አስከሬናቸው ተልኮ ቤተሰብ እንዲቀብር ማድረግ፣

2) ይህ ካልተቻለ በተቀበሩበት ቦታ ላይ ቤተ ዕምነት መትከል እና ቦታውን አጥሮ ማክበር በቦታው ላይ ቤተሰብ እርም የሚያወጣበት የሃይማኖት አባቶች ተገኝተው በፀሎት የሚሳተፉበት መርሃግብር በቶሎ ማዘጋጀት ወይንም 

3) እነኝህ ሁሉ ካልሆኑ ግን የቀብር ቦታው አሁንም በሥርዓት ታጥሮ እና ልዩ የማስታወሻ የቀብር ምልክት ከተደረገ በኃላ የክልሉ መንግስት በቀጥታ ስርጭት ስለ ድርጊቱ ስህተቱን አምኖ ሕዝብን ይቅርታ እንዲጠይቅ ማድረግ ያስፈልጋል።
ይህንን ሁሉ የማድረግ ፍላጎት ከሌለ ግን በኢትዮጵያ ሕግ ለአስከሬን የሚሰጠው ክብር አንፃር አቃቢ ሕግ ከገዳዮቹ ጋር ከሚከፈተው የክስ ቻርጅ ጋር ክስ መመስረት አለበት።

==============================///============
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ የሚችሉበት አዲስ ቴክኖሎጂ ጉዳያችን ማስተዋወቅ ጀምራለች።
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...