ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, December 21, 2020

ኢትዮጵያ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል አግኝታለች! በእዚህም የተሸረበባት ትልቅ ተንኮል ከሽፏል።ተንኮሉ ምን ነበር?ጉዳያችን/Gudayachn

ኢትዮጵያ በህወሓት ፅንፈኛ ቡድን ላይ የወሰደችው የሕግ ማስከበር እርምጃ ተከትሎ በኢትዮጵያ ላይ የሐሰት ዜና ከማሰራጨት ጀምሮ እስከ የውጭ ባለስልጣናት ጉትጎታ ድረስ የፅንፍ ኃይሎች ከውጭ ሀገር ተወላጆች ጋር በመጣመር ዘመቻ ሲያደረጉ ሰንብተዋል።ዘመቻው ከትዊተር እስከ ፔቲሽን ማስፈረም ሲቀጥል ዋና ዓላማው የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በተለይ የምዕራቡ ዓለም እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በዋናነት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ እንዲገባ የተደረገ ቅስቀሳን ሁሉ ያካተተ ነበር።

የተባበሩት መንግሥታትም ሁለት ጊዜ ''መደበኛ ያልሆነ'' የተባለ ንግግር አደረገ የሚል ዜናም ተለቆ ነበር።በእነኝህ የተባበሩት መንግሥታት መደበኛ ያልሆኑ ስብሰባዎች በተመለከተ የአፍሪካ ዲፕሎማቶችም ሆኑ የራሱ የድርጅቱ የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሙያዎች የተባበሩት መንግሥታት አካሄድ ትክክል አለመሆኑን ተናግረዋል።ይሄውም የአንድ ሀገር ጉዳይ ወደ ተባበሩት መንግሥታት አጀንዳነት ከመሄዱ በፊት በአህጉራዊ ድርጅት ችግሩ መፍትሄ ለማግኘት ጥረት ተደርጎ ካልተሳካ መሆን አለበት የሚለው ሃሳብ ነው።በእዚህ መሰረት የተባበሩት መንግስታትን መቆምያ እና መቀመጫ አሳጥተው የነበሩ መንግሥታት አይናቸውን ወደ አፍሪካ ሕብረት እና ኢጋድ ላይ ጥለው በተስፋ ሲጠብቁ ቆዩ።

ይህ በእንዲህ እያለ የኢትዮጵያ ጦር ኃይል የሰላም ማስከበር ስራውን አጠናቆ ቀንደኞቹን ማደን ላይ አተኮረ።ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ደግሞ የአፍሪካ ሕብረት ''ኢትዮጵያ በትግራይ የወሰደችው የሕግ ማስከበር ተግባር ሕጋዊ ነው'' ማለቱ እና በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በጅቡቲ የአፍሪካ ቀንድ በየነመንግሥታት ሀገሮች (ኢጋድ) ስብሰባ ላይ ከተገኙ በኃላ የኢጋድ ሀገሮች የኢትዮጵያን ሕግ ማስከበር ሂደት መረዳታቸው እና መደገፋቸውን ያመሰገኑበት መልዕክት እና ኢጋድም በራሱ የሕግ ማስከበር ሂደቱን መደገፉ የተባበሩት መንግስታትን ሲጎተጉቱ የነበሩትን ሁሉ ከመንገድ ያጨናገፈ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል ያስመዘገበ ነው።
====================

ማስታወቂያ 

============

በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ የሚችሉበት አዲስ ቴክኖሎጂ ጉዳያችን ማስተዋወቅ ጀምራለች።

አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

https://www.fetantopup.com/#gudayachn No comments: