ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, November 28, 2020

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሕዝብ ታሪክ ሰርተዋል! አሁን ርዝራዥ ህወሓት ማኅበራዊ ሚድያው ላይ ሊያስነሳቸው የሚችላቸውን ሶስት ቀዳዳዎች ቀድመን እንወቅ!

ዛሬ ህዳር 19/2013 ዓም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከ600 ኪሎሜትር በላይ በእግሩ ተጉዞ የመቀሌ ከተማ እና የትግራይ ክልልን ከህወሓት ነፃ አውጥቷል።ይህ ድል የትግራይ ሕዝብ ህወሓት እንደሚለው ሳይሆን ለዲሞክራሲ፣ለፍትሕ እና ለእኩልነት ያለውን ፅኑ ፍላጎት የመከላከያ ሰራዊቱን በማክበር አሳይቷል።በእዚህም የትግራይ ሕዝብ ባለፉት 25 የዘመቻ ቀናት ውስጥ ድምፁን ከፍ አድርጎ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አሰምቷል።ከሁሉም ደግሞ ነፃነቱ  በነፃ አውጪ የመጣ ሳይሆን የሁሉም የጋራ በሆነው በመከላከያ ኃይል መምጣቱ እንደሀገር ትልቅ ቁም ነገር አለው።በእርግጥ በእዚህ ዘመቻ ላይ የዓማራ እና የአፋር ልዩ ኃይሎች ቢካፈሉም በዋናነት የመከላከያ ሰራዊት የመራው እና ያጠናቀቀው መሆኑ እንደ ሀገር ትልቅ መልዕክት አለው።ይህንን ለመዘርዘር ብዙ ማለት ይችላል።አሁን ጊዜ ስለሌለ አልፈዋለሁ።

አሁን ርዝራዥ ህወሓት ማኅበራዊ ሚድያው ላይ ሊያስነሳቸው የሚችላቸውን ሶስት ቀዳዳዎች ቀድመን እንወቅ! እነርሱም 

1ኛ) በዓማራ ስም የማኅበራዊ ሚድያ በመክፈት ዓማራ አሸነፈ በሚል የሚፎክሩ ድምፆች በማብዛት የትግራይን ሕዝብ ለማበሳጨት መሞከር፣

2ኛ) በኦሮሞ ስም በተከፈቱ ማኅበራዊ ሚድያዎች ስም በዓማራ ላይ የሚፎክሩ ድምፆች ማብዛት እና 

3ኛ) በመንግስት ባለስልጣናት በተለይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ከቀድሞ የበለጠ ዘመቻ ማካሄድ የሚሉት ናቸው።

ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ሁሉም ጥንቃቄ ከማድረግ ባለፈ መሬት ላይ መሰራት ያለባቸው፣የሕዝብ ስሜት፣ሃዘን፣መቃቃርን የሚያርቁ ስራዎች ላይ በቶሎ መሰማራት አስፈላጊ ነው።

ይህ በእንዲህ እያለ  ለኢትዮጵያ ብዙ የመሰከሩ፣የተሰደዱ እና የተሰዉላት ምስጋና እንደሚገባቸው ሳንረሳ፣ዛሬ  ኢትዮጵያ ባለችበት ፈታኝ ጊዜ ለሰጡት ብቃት ላለው አመራር ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ታላቅ ምስጋና ይገባቸዋል። 

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ 







No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...