ታላቁ የኢትዮጵያ አርበኛ ጀነራል ጃጋማኬሎ
ጉዳያችን/Gudayachn
መስከረም 21/2011 ዓም (ኦክቶበር 2/2019ዓም)
=========================
ትናንት ማክሰኞ መስከረም 20/2011 ዓም ወደ 14 የሚጠጉ ድርጅቶች በጋራ ለመስራት መፈራረማቸውን ለአምስተኛ ጊዜ በመፈራረም አሳይተዋል።የፊርማው ድባብ በራሱ የሚነግረን ነገር ግን የተለየ ነው።
ለመሆኑ የተፈራረሙት ማን ከማን ጋር ነው ብለን ብንጠይቅ መልሱ ቀላል ነው።ለሃያ ሰባት ዓመታት ኦህደድ የኦነግ ድርጅቶችን ሸኮና እየሰበረ አላስገባ ካላቸው ኃይል ጋር ነው።ይህ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው የኦህዴድ (የአሁኑ ኦዴፓ) የኦነጎችን ፕሮፋይል ደካማና ጠንካራ ጎን ሲያጠና ነው የኖረው።በእርግጥ የኦነግ አንጃዎች እና ኦዴፓ በአንድ ነገር ላይ ይስማማሉ።ይሄውም ኢትዮጵያዊ ቅኝትን ማጥፋት፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ተሰሚነት ማደብዘዝ፣ያለፈውን ታሪክ በአዲስ የእረቻዊ የታሪክ ትርክት መፃፍ እና ሌሎች ላይ አብረው የሚያልሙት ጉዳይ ነው። ይህ ግን ሁሉም ኦዴፓ ውስጥ ያለ ሃሳብ አይደለም።ሃሳቡ ቢኖርም እንደማያዋጣ ጠንቅቀው የሚያውቁ ብዙ ናቸው።ስለሆነም ግቡ ላይ ቢስማሙም አካሄድ ስልት ላይ ግን ይለያያሉ።
በአካሄድ ከሚለያዩት ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ይጠቀሳሉ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልችት ያላቸው ጉዳይ አሁንም የኦነግ እንደአንዳንዶች አባባል የማይጠራ የበግ ሽንፍላ የማጠብ ያህል ማለቂያ የሌለው ያረጁ እና የጃጁ ጥያቄዎች እራሱ ኦነግ ቤተ መንግስት ቢገባም ያማይመልሳቸው ጥያቄዎች ናቸው።እነኝህ ጥያቄዎች የ21ኛው ክ/ዘመንን የማይመጥኑ ብቻ ሳይሆኑ ያለፈው እና የድሮው ስራቶችንም ያማይመጥን ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ አይነት ጥያቄ ያለው ግን ግቡ እና ዓላማው ኢትዮጵያዊነትን በፅንፍ የእስልምና ሃሳብ የመተካት ነው። ከኦነግ አንጃዎች ውስጥ ብዙዎቹ የኦኤምኤን ባለቤት ሃጅ ጀዋርን ጨምሮ የሚያገናኛቸው ይሄው ኢትዮጵያን ወደ ፅንፍ የእስልምና አብዮት መምራት ነው።ሁሉም ለኦሮሞ ሕዝብ እንደ ሰብዓዊ ጋሻ ከመጠቀም ያለፈ ቅንጣት ታህል አይፈልጉትም። ቢፈልጉት ኖሮ ሀገር ቤት ከገቡም በኃላ በኦሮሞ ስም እንደ አሜባ እየተራቡ ባልተከፋፈሉ ነበር።
የትናንቱ የኦሮሞ ድርጅቶች ተፈራረሙ ዜና ተፈራሩ በሚለው ቢቀየር የተሻለ ነበር።የፊርማው ስነስርዓት ሲደረግ ጀዋር ጮክ እያለ ለማንበብ እየቸገረው ድምፁን እየቆራረጠ በኦሮምኛ ሲያነብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳቃቸው መጥቶ አይናቸውን ከወዲያ ወዲህ ይወስዱ ነበር። አሁን መሰረታዊው ጥያቄ ፅንፈኛው ክፍል ዓቢይን ለመምታት በፊርማ ሊያዘናጋ እየሞከረ ነው ወይንስ ዓቢይ የፅንፈኛውን አካል ጋር ተስማማ? የሚለው ነው። ይህ ጥያቄ በደንብ መመለስ ያለበት ነው።የፊርማው ስነ ስርዓት የመፈራራት ውጤት ነው።ግቡም ጊዜ መግዣ ነው።ፅንፈኛው አካል ዓቢይ ከስልጣን መውረድ እንዳለበት ያልማል።በቀላሉ ሊያደርጉ እንደማይችሉ ደግሞ ገብቷቸዋል።ዓቢይ የምንፈልገው አይደለም።የኢትዮጵያን ለውጥ ከቱንስያ ከፍ ማድረግ ነበረብን።አሁን ቆጨን እና ሌሎችም ሲሉ የነበሩ ዛሬ ፊርማ ያሉት አንድ ዓቢይ ሊያስረን ነው ብለው ስለፈሩ።ግልጥ እርምጃ የኦዴፓ ሰዎች መውሰድ ስለጀመሩ።ይህም በቀጥታ ማፈንን የጨመረ በመሆኑ ጉዳዩ ሳይከፋ የተለመደው ፊርማ ማንጋጋት መፍትሄ ነው ብለው ስላሰቡ ነው።
''ሀሎ ዓብይ ፊርማ ስነ ስርዓቱ አንተ ባለህበት መሆን አለበት'' አቶ ለማ ወደ ዓቢይ ደውለው።
''እባክህ ስራዬን ልስራበት።ከፈለጉ ወደ አስመራ መልሳቸው አርባ ዓመት ከገማ አስተሳሰብ ጋር አታነካካኝ።ካመንቅበት እንደሚሆን አድርገው'' ዓቢይ
'' ግዴለህም እንደመንግስት ስንሆን መታገስ አለብን።ይህንን ብቻ ዓቢይ የአንተ መገኘት በጣም አስፈላጊ ነው።ሰጥቶ መቀበል አርገውታል።አንተን በአደባባይ ማሳየት እንደ ሾው ነው።ሆነም አልሆነም ምን ያህል እንደታገስን የሚያስረዳ ነው የሚሆነው።እረቻ ላይ ነገር ከተበላሸ ብዙ መዘዝ አለው።እሺ በለኝ።'' አቶ ለማ።
ዓቢይ ወደ አዳራሽ ሲገባ የምንሊክ ግብር የመሰለ ከአክትቪስት እስከ ጋዜጠኛ ተሰብስቧል።ዓቢይ የውሸት ዕቃ ዕቃ የሚጫወት ነው የመሰለው።ኦነግ ምን ሲሰራ እንደነበር ሪፖርቱ አለው።ከህወሓት ጋር እነማን ምን እንደተባባሉ ቃል በቃል ሰምቶታል።ይህ ፊርማ ዓቢይ ከጀዋር ጋር ተሰለፈ ለመባል የገበያ ዋጋ እንዳለው ያውቃል።ለማን ማስቀየም አልፈለገም።ሁሉንም ከኢረቻ በኃላ ይደርሳል።ስለሆነም ስልችት እያለው እና ሳቁ እየመጣ ተፈራረመ።እንደ ኦህዴድ -ኦዴፓ ሆኖ ፈረመ።ፈርሞ ሲወጣ ዘወር ዘወር ብሎ አየ እና ''ነጋቲ'' ብቻ ብሎ ወጣ። ፊርማ ሳይሆን መፈራራት።የእውነት ሳይሆን ዓቢይን በማዘናጋት ለመምታት እና ስልጣን ለመቆጣጠር የስልት ፊርማ መሆኑ ገብቶታል።የለማ የዋህነት እና ፅንፈኛውም የእኛው ነው ነገሮችን ማረቅ አለብን የሚለው አባባል የቆየ ግን የማይሰራ መሆኑ ገብቶታል።ስለሆነም ቀጣዩ እርምጃ እና ሂደት ላይ ብቻ ነው ዓቢይ እያሰበ የወጣው።የኦነግን ፋይል ደህንነት መስርያቤት እያለ ሲያነበው ነው የኖረው።ወደ ሰውነት ማደግ ያልቻሉ የጫጩ አስተሳሰቦች እንዳሉበት ያውቃል።ስለሆነም ወደ ቀጣዩ ሂደት ላይ ማትኮር እንዳለበት ገብቶታል።
ለማጠቃለል ፍጥጫው በፊርማው ባሰበት እንጂ አልተሻሻለም።የሚሻሻል ቢሆን ኖሮ ከአምስት ወር በላይ ፈጀብን እያሉ መናገር አይሳፈልገውም ነበር።በትክክል ከታሰበ የፈጀባቸው አምስት ወር አይደለም አርባ ዓመት ነው።ከአርባ ዓመት በኃላም ስለ አንድ ኦሮሞ እያወሩ አስራ አራት ሆነው ተቀመጡ እንጂ አንዳች አልፈየዱም።ከአርባ ዓመት በኃላ ከአስመራ ሀገር ውስጥ ገብተው ጥይት አንጣጡ ባንክ ዘረፉ እንጂ አንዳች ፋይዳ ለኦሮሞ ሕዝብ አላመጡም።ኦሮሞ ይነሳል! ኢትዮጵያዊነቱን በደሙ ያስከብራል።ያን ጊዜ ለፅንፍ አውሬ ሊሰጡት ያሰፈሰፉ ሁሉ እውነተኛ ፍርዳቸውን ያገኛሉ።የወለጋ ሕዝብ የደረሰበትን እና አሁን እየደረሰበት ያለውን ይመስክር።በሰላም አርሶ መብላት እና ነግዶ ማትረፍ ሕልም የሆነበት በኦነግ እና ውላጆቹ አስተሳሰብ የተነሳ ነው።ከኦነግ ያረጀ አስተሳሰብ ጋር እሄዳለሁ የሚል ማንኛውም ኃይል ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይም ሆኑ የኦዴፓ ለኦነግ አሸርጋጆች ሁሉ የሚፋረዳቸው የኦሮሞ ሕዝብ ነው።ይህ ዕውነት አይዘገይም። ባጭሩ የኦሮሞ ድርጅቶች ተፈራረሙ ከማለት ተፈራሩ ማለቱ የተሻለ ነው።ጀግኖቹ እነ ጀነራል ጃጋማኬሎ ደምተው ባቆዩት ሀገር ፅንፈኛ አይፈነጭባትም።ጉዳዩ እየጠራ መጥቷል።ኢትዮጵያዊነት ያነገቡ ከምር የሚነሱበት የደውል ድምፅ ከፍ ብሎ እየተሰማ ነው።
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment