ጉዳያችን GUDAYACHN
መስከረም 24/2012 ዓም (ኦክቶበር 5/2019 ዓም)
በአዲስ አበባ ዙርያ ከዓመታት በፊት ለልማት ተነስተው የነበሩ እና በምትኩ ለእርሻም ሆነ ለመኖርያ ቦታ ተሰጥቷቸው የነበሩ የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ቀድሞ ከተሰጣቸው ምትክ ካሳ በተጨማሪ በሚመጣው ሰኞ በሚሊንየም አዳራሽ በሚደረግ ስነ ስርዓት የኮንደምንየም እደላ ሊደረግ መሆኑን ከአዲስ አበባ ተሰምቷል።
መረጃውን በተመለከተ ጉዳያችን ለማጣራት እንደሞከረችው ከእዚህ በፊት ካሳ ተሰጥቷቸው የነበሩት ብዛት ሶስት ሺህ ሲሆኑ የተቀሩት 20 ሺህ የሚሆኑት በውሸት የተፈናቀሉ ነበሩ በሚል ስም ከተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች ውስጥ ተመርጠው የሚመጡ እና ካለምንም ዕጣ እና ክፍያ የሚሰጣቸው መሆኑ ተሰምቷል።በሌላ በኩል ለእነኝህ አካላት የሚሰጠው የኮንደምንየም እደላ ልዩ የብድር አገልግሎት ይመቻችላቸዋል የሚል መረጃ አለ።የተረጋገጠው ጉዳይ ግን የአዲስ አበባ ሕዝብ በዜግነት መብቱ ተመዝግቦ እና ዕጣ አውጥቶ ኮንደሚንየም እየጠበቀ ቢሆንም ከ23 ሺህ የማያንሱ ኮንደሚንየም ቤቶች በሙሉ ከላይ ለተጠቀሱት አካላት የሚሰጥ መሆኑ ነው።
በኮንደሚንየም አሰጣጡ ኢ-ፍትሃዊ አካሄድ ደግሞ ቀድሞ ካሳ ለተሰጣቸው ድጋሚ ኮንደሚንየም ሲሰጥ፣በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ሁለቴ እና ሶስቴ እየተሰጠ ሲሆን ለምሳሌ በቤተሰብ ውስጥ ለቤተሰቡ ሶስት መኝታ ክፍል ከተሰጠ በኃላ በቤተሰቡ ውስጥ ላሉ ከአስራ ስምንት ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች ላሏቸው ለልጆቹ ለብቻቸው ሌላ የኮንደሚኒየም ቤቶች እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ በእንዲህ እያለ ዛሬ በአዲስ አበባ የእረቻ በዓል ዋዜማ በሚል በመስቀል አደባባይ የኦሮምያ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ''የኦሮሞ ሕዝብ የተሰበረው እዚህ ነው፣የነፍጠኛ ስርዓትን ዛሬ ሰበርነው፣የኦሮምያ ሕዝብ ደስ ይበልህ'' የሚል አደገኛ የዘር ቀስቃሽ ንግግር (ምናልባትም የሁቱ እና ቱትሲ ግጭት የመሰለ ንግግር) መናገሩ ከፍተኛ ውጥረት ኢትዮጵያ ውስጥ ፈጥሯል።
የአቶ ሽመልስ ንግግር የኦዴፓ ድብቅ እና ከፋፋይ ዓላማ በግልጥ ያሳየበት ብቻ ሳይሆን ኦዴፓ ከፅንፍ ኃይሎች ጋር አፍ ለአፍ ገጥሞ እየሰራ መሆኑ ግልጥ ማሳያ ሆኗል።ሌላው የንግግራቸው ማሳያ አሁን ለውጡ ሙሉ በሙሉ ሐዲዱን እየለቀቀ መሆኑን ማሳያ ተደርጎ መወሰድ ይችላል።
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

ለኢትዮጵያ ነፃነት ከታገሉ የኢትዮጵያ ነፍጠኛ አርበኞች መካከል ፋሺሽት ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት 1928 ዓም አዲስ አበባ
Determined Ethiopian young patriot NEFTEGNA at the beginning of the second world war, when Italy invaded Ethiopia in 1935.
Determined Ethiopian young patriot NEFTEGNA at the beginning of the second world war, when Italy invaded Ethiopia in 1935.
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment