ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, October 16, 2014

''ነፃነት ከመዋለ ንዋይ በፊት!'' ''Freedom before investment!'' ኢትዮጵያውያን ዛሬ በከፍተኛ ቁጥር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን በኦስሎ መገኘት በመቃወም ያሰሙት ድምፅ።

























ዛሬ ጥቅምት 6/2007 ዓም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የኖርወጅያን-አፍሪካ የንግድ ማህበር (Norwegian-African Trade Association) ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ ለመገኘት ኦስሎ፣ኖርዌይ  በተገኙበት ወቅት ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ኢትዮጵያዊ ''Freedom before investment!''  ''ነፃነት ከመዋለ ንዋይ በፊት!'' በሚል ተቃውሞ አሰምቷል።

የተቃውሞ ሰልፉን ያዘጋጀው ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ  ድርጅት በኖርዋይ ሲሆን ድርጅቱ በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚገልፅ እና ኖርዌይ በኢትዮጵያ ካለው አምባገነን ስርዓት ጋር የሚኖራትን ግንኙነት ላይ በሚገባ ልታስብበት እንደሚገባ የሚያሳስብ ደብዳቤ ሰጥቷል።

በከፍተኛ ደረጃ ቁጣቸውን የገለጡት ኢትዮጵያውያን ከተቃውሞ ድምፅ በተጨማሪ እንቁላል በልዑኩ  መኪና ላይ በመወርወር ተቃውሟቸውን መግለፃቸውን የኖርዌይ ታዋቂ የቴሌቭዥን ጣብያ NRK ''Kastet egg på stats minister'' ( ''የእንቁላል ውርወራ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ'' ) በሚል አርዕስት ስር የኖርዌይ ፖሊሶች ሲያስተናብሩ አሳይቷል።አንዳንዶች ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ''ጠቅላይ ሚኒስትር'' ተብለው መጠራታቸው የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ቦታ በዶ/ር ቴዎድሮስ ተተካ እንዴ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል።

ኖርዌይ ለኢትዮጵያ ከምትሰጣቸው ርዳታዎች አንዱ በ''ኖርወጅያን ቤተክርስቲያን'' በኩል መሆኑ እና አዲስ አበባ አይቤክስ ሆቴል አጠገብ የሚገኘው የኖርዌጅያን ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ስራውን የጀመረበትን አርባኛ ዓመት ባለፈው ግንቦት ወር አዲስ አበባ ላይ ማክበሩ ይታወቃል።

ጉዳያችን
ጥቅምት 7/2007 ዓም (ኦክቶበር 17/2014)


No comments:

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)