ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, October 20, 2013

የኢትዮጵያ ስነ-ህዋ ሳይንስ ምርምር ማኅበር አመርቂ ተግባራት (ጉዳያችን ጡመራ ልዩ ጥንቅር)
ስለ ስነ-ህዋ መመራመር ለበለፀጉ ሃገራት ብቻ መስጠት በብዙዎች ዘንድ የታመነበት ተግባር ነው።ኢትዮጵያ በምጣኔ ሃብት በማነሷ ብቻ ስለህዋው ጉዳይ ለማጥናት መብት የሌላት ያህል ዝቅ አርገው የሚመለከቱ አይጠፉም።እሳቤያቸው ከበጎ አስተሳሰብም የሚነሳ አሉ።''ኢትዮጵያ ብዙ ወጪ የሚጠይቀውን የህዋው ምርምር ላይ ከመትሰራ መጀመርያ እርሻው በአግባቡ በታረሰ'' መሰል ጥያቄ የሚያነሱ አሉ።ይህ ግን የተሳሳተ እሳቤ ነው።በዓለም ዙርያ የአሜሪካውን የህዋ ምርምር ጣቢያ (ናሳን) ጨምሮ የሚያማክሩ እና በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ያሉ የመጀመርያ ዲግርያቸውን ግን በኢትዮጵያ የሰሩ ተመራማሪዎች አሏት -ኢትዮጵያ።

ይህ ብቻ አይደለም ''የኢትዮጵያ ስነ-ህዋ ምርምር ማኅበር'' (Ethiopia Space Scince Society- http://www.ethiosss.org.et/index.php/en/ ) በአዲስ አበባ አበረታች እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።በ2004 ዓም እአአ የተመሰረተው ማኅበር  በወቅቱ ሃሳቡን ሲገልፅ አንዳንዶች በቀልድ መልክ ተመልክተውት ነበር።''የእብድ ማኅበር '' በማለት የተሳለቁም ነበሩ።ሆኖም ግን ዛሬ ማኅበሩ በምስራቅ አፍሪካ በጥራቱም ሆነ በብቃቱ ተወዳዳሪ የሌለው የስነ-ህዋ ማጥኛ ማዕከል ወደመሆን እራሱን ቀይሯል።

ማኅበሩ እስካሁን 1500 በዘርፉ ዙርያ ምርምር የሚያደርጉ እና ለዘርፉ ድጋፍ የሚሰጡ አባላትን አሰባስቧል።በእዚህ አላቆመም። በእንጦጦ ተራራ ላይ ከመሰረተው ጣብያ ላይ በቅርቡ ከሁለት ዓመት በፊት እንዲሰሩ ያዘዛቸውን 80 ሚልዮን ብር የሚያወጡ እጅግ ዘመናዊ ቴሌስኮፖች በቅርቡ ከጀርመን ሀገር እንደሚያስመጣ እና እንደሚተክል ለማወቅ ተችሏል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ከባህር ጠለል በላይ ከ2000 ሜትር በላይ መገኘቷ እና ባብዛኛው ወራት ሰማይዋ በደመና ያለመሸፈኑ ታክሎበት ለዘርፉ ምርምር ተፈጥሮ ያደላት መሆኑን ብዙዎች ያወሳሉ።በነገራችን ላይ የስነ-ህዋ ምርምር ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ይሰጣል።ይሄውም ለዘመናዊ እርሻ እድገት፣ለኢንዱስትሪ ልማት፣ለሕዋ ቱሪዝም ለመሳብ(ቱሪስቶች ወደ እንጦጦ ተራራ ሄደው በክፍያ ህዋውን በልዩ ቴሌስኮፕ እንዲመለከቱ በማድረግ-Astronomy tourism) ወዘተ ጥቅም አለው።

በመጨረሻም በጥቂት ተነሳሽ አባላት ስራውን የጀመረው ማኅበር አሁን የምርምር ጣቢያውን ከከፈተበት ከእንጦጦ ተራራ በተጨማሪ ከላሊበላ ከተማ በስተሰሜን ላይ ከሚገኘው በከፍታው ከባህር ጠለል በላይ 4200 ሜትር ከፍታ ላይ ሌላ የመመልከቻ ማማ  እንደሚከፍት ለመረዳት ተችሏል።በእዚህ አላቆመም።ኢትዮጵያ የሕዋ-ፖሊሲ እንዲኖራት ለመንግስት ሃሳቡን አቅርቦ ፖሊሲው እንዲወጣ እየሰራ ይገኛል።በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተለይ በዘርፉ ሙያ ያላቸው ሊደግፉት የሚገባ ተግባር ነው።በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን መኪና ወደሀገራችን ሲገባ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ነዳጅ የለን፣መንገድ የለን፣ሹፌር የለን ብለው የመኪና ወደሀገራችን መግባትን አልተቃወሙም ዘመን አሻግረው አስፈላጊነቱን ተረዱ። ዛሬም ይህ ማኅበር አርቆ የተመለከተው ለአንዳንዶች ሕልም የሚመስለው ነገር ፍሬ ማፍራቱ አይቀርም።ለነገሩ ዓለም እራሱ ስለህዋ የተማረው ከኢትዮጵያ መሆኑን ልብ ይሏል።መፅሐፈ ሄኖክ የተሰኘው የቤተክርስቲያን መፅሐፍ በመላው ዓለም ጠፍቶ የተገኘው ኢትዮጵያ ነው።መፅሐፉ እግዚአብሔር ስለፈጠራቸው ስነ-ህዋ በሚገባ እንደሚናገር ይታወቃል።

ማገናዘብያ 
http://www.ethiosss.org.et/index.php/en/ 

http://www.channelnewsasia.com/news/lifestyle/ethiopia-unveils/852640.html 

http://voicesofafrica.co.za/tag/ethiopian-space-science-society/ 

No comments:

ለፕሮፌሰር መራር፣ልደቱ፣ጀዋርና ኢንጅነር ይልቃል ዘፈን ይህችን ዜማ እንምረጥላቸው።

በቅድምያ ስለ አራቱም የመግቢያ ማስታወሻና ወቅታዊ ሁኔታቸው። አራቱም ከመስከረም በኋላ መንግስት የለም ብለው ኢትዮጵያን ለእርስ በርስ ጦርነት ሊነክሯት ሞክረዋል።ዝርዝሩን፣ከእነማን ጋር መክረው እንደነበር፣ለኢትዮጵያ ደግሰው...