ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, October 18, 2013

ትግራይ ኦን ላይን'' በማለት እራሱን የሚጠራው ድህረ-ገፅ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያሰፈረው ፅሁፍ መሰረተ ቢስ እና ፍርሃት የተቀላቀለበት ነው።

''ትግራይ ኦን ላይን'' በማለት እራሱን የሚጠራው ድህረ-ገፅ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያሰፈረው ፅሁፍ እጅግ የሚያሳዝን ነው።ፅሁፉ መሰረተ ቢስ እና ፍርሃት የተቀላቀለበት ነው።

ከእዚህ በፊት በማኅበሩ ላይ የሐሰት መፅሐፍ መሰል ፅሁፍ በመፃፉ በኢትዮጵያ ሕዝብ ከትዝብት ላይ ወድቆ የነበረው ግለሰብ ዛሬ ''ትግራይ ኦን ላይን'' ላይ ማኅበሩን እንደፈለገ እንዲሳደብ ተፈቅዶለታል።ግለሰቡ በከፈተው ''ሳልሳዊ ወያነ'' በሚለው ገፁ መግቢያ ላይ ኢትዮጵያን እንደሚጠላት በአደባባይ ማወጁን ለማወቅ ይቻላል።በገፁ መግቢያ ላይ ''ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንጅ ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም!'' ይላል።

ከግለሰቡ የሐሰት ጥርቅም ፅሁፍ ባለፈ አስገራሚው ነገር ''የትግራይ ኦን ላይን'' ድህረገፅ ሊንኩን ለመንካት በእንግሊዝኛ የለጠፈው አርዕስት፣ ድህረ-ገፁ ከግለሰቡ ከቀረበለት ፅሁፍ ባለፈ የእራሱን የተሳሳተ አስተሳሰብ ያንፀባርቃል።ፅሁፉ በአማርኛ ቀርቦ ሳለ ''ትግራይ ኦን ላይን'' ግን በእንግሊዝኛ ''ማኅበረ ቅዱሳን ፀረ ኢትዮጵያ አንድነት፣ አሸባሪ...'' የሚሉ ቃላትን ከድህረ ገፁ ፊት ላይ ያስነብባል።

በመጀመርያ በትግራይ ሕዝብ ስም የተከፈተ ድህረ ገፅ ቢያንስ በስሙ የተከፈተበት ሕዝብን ትልቅ የሆነ የሃይማኖት ስሜት የሚነካ የሐሰት ወሬ ለማሰራጨት እንዴት ተደፋፈረ? ለእንደዚህ አይነቱ እርካሽ ፅሁፍ ምላሽ መስጠት በእራሱ የጊዜን ጥቅም አለመረዳት ነው።በጉዳዩ ላይ እግዚአብሔር እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍርድ ይሰጡበታል!


ማሳሰብያ ዘግይቶ የተገኘ - 
''ትግራይ ኦን ላይን'' ድህረ ገፅ ትንሽ ኤዲት ዛሬ ከቀትር በኃላ አደረገ። በእንግሊዝኛ ከራሱ ጨምሮት የነበረው ባለ 4 መስመር ማኅበሩን የሚያጥላላ አረፍተ ነገር ከቀትር በኃላ አንስቶ ወደ ፅሁፉ የሚያመራውን የገፅ ''ሊንክ'' ግን እንዳለ አስቀርቷል። የእንግሊዝኛ ትርጉሙ ከላይ እንደተገለፀው እንዳለ ተቀምጧል።
አሁንም የእግዚአብሔር እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍርድ አይለየን!




ጉዳያችን GUDAYACHN

1 comment:

Anonymous said...

It is surprising that Tigray online is standing on the side of anti-christian individuals. This is pure terrorism is it not?

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።