ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, October 15, 2013

የእንግሊዙ ባርክሌይስ ባንክ ከትልቁ የሱማሌ የገንዘብ አስተላላፊ- ከደሃብሺል ጋር የነበረውን የስራ ግንኝነት ሊያቆም ነው (ጉዳያችን ጡመራ ልዩ ጥንቅር)



የእንግሊዙ ባርክሌይስ(Barclays) ባንክ መሰረቱን ዱባይ ላይ ካደረገው ከድሃብሺል(Dahabshiil) ጋር የነበረውን የስራ ግንኙነት ሊያቆም መሆኑን ብሉምበርግን ጨምሮ የተለያዩ የዜና ወኪሎች አስታውቀዋል።የእንግሊዙ ባርክሌይስ ባንክ በሃምሳ ሀገሮች ቅርንጫፎቹ ከአርባ አምስት ሚልዮን በላይ ደንበኛ ያለው ባንክ መሆኑ ሲታወቅ የደሃብሺል የገንዘብ አስተላላፊ ጋር የሚያደርገው የስራ ግንኙነት መቆረጥ ከእንግሊዝ ብቻ ወደ ተቀረው ዓለም (በተለይ ወደ ሱማልያ) የሚላከውን በዓመት ከአንድ መቶ ስልሳ ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር የሚሆን ገንዘብን ያግዳል።

ከጉዳዩ ጋር ተያይዘው የወጡት ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት እራሷን ችላ መቆም ያልቻለችው ሱማልያ በውጭ ከሚኖሩ ዜጎቿ የሚላከው የገንዘብ መጠን በዓመት እስከ  1.5 ቢልዮን ዶላር እንደሚደርስ ያመላክታሉ።እንደምዕራባውያን አስተያየት በደሀብሺል በኩል ለሱማልያውያን የሚላከው ገንዘብ  ቀጠናው እንዳይረጋጋ ከሚፈልጉ ኃይሎች እጅ እየገባ  መሆኑ  ስጋት ላይ ጥሏቸዋል።

የባርክሌይስ ባንክ ከደሃብሺል ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት ማቆም ተከትሎ በትውልድ ሱማልያዊ በዜግነት እንግሊዛዊ የሆነው ታውቂው አትሌት ሞፋራህ የባንኩ ውሳኔ ብዙ ሱማልያውያንን እንደሚጎዳ በማስገንዘብ ያቀረበውን ተማፅኖ ባንኩ አለመቀበሉ ውሳኔው  ምን ያህል ቁርጥ መሆኑን አመላካች ሆኗል።

በሌላ በኩሉ የሱማልያው የወቅቱ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ጉዳዩን አስመልክተው ሲናገሩ - ''ጉዳዩን በአትኩሮት እየተከታተልነው'' ካሉ በኃላ በሀገራቸው ላይ ስለሚያመጣው አሉታዊ ተፅኖ ሲያብራሩ '''' ህዝባችን ከረጅም እና አሰልቺ ጦርነት ገና ማገገሙ ነው።በሚልዮን የሚቆጠሩ ሱማልያውያን ጥገኛ የሆኑበት እና  የሕይወት አድን መንገድ የሆነውን ሕጋዊውን የገንዘብ ማስተላለፍያ መስመር ዘግቶ ሕዝቡን የመቅጫው ጊዜ አሁን ሊሆን አይገባውም ነበር።ምክንያቱም ጥቂቶች በሚሰሩቱ ወንጀል የዋሃንን መቅጣት ተገቢ አደለም።'' ብለዋል።
 “Our people are now recovering from a long and devastating civil war and this is not the time to punish them again by closing the legitimate lifeline on which millions of Somalis absolutely depend,'' he said. "Innocent millions should not be made to suffer because of the crimes of the guilty few.''

ደሃብሺል ከኢትዮጵያን የግል ባንኮች ጋር በገንዘብ ማስተላለፍ ሥራ ጋር ትብብር ያለው ሲሆን በአንድመቶ ሃምሳ ሀገሮች ውስጥ በሚገኙት ቢሮዎቹ በአብዛኛው የሱማሌ ማህበረሰብን ያገለግላል።በሱማልያ የሚገኙ የረዴት ድርጅቶችም ሆኑ የተባበሩት መንግሥታት ቢሮዎች ማናቸውንም የፕሮጀክትም ሆነ ለተመሳሳይ ሥራ የሚውል ገንዘብ የሚተላለፈው በደሃብሺል በኩል መሆኑ ይታወቃል።ድርጅቱ በአዲስ አበባም የቦሌ ሩዋንድን ጨምሮ ቅርንጫፍ የገንዘብ መክፈያ ቢሮዎች አሉት።

.//////////ከጉዳያችን ጡመራ የሚወጡ ማናቸውንም ፅሁፎችን በተለያዩ ድህረ ገፆች ሲያወጡ የጡመራውን ምንጭነት መጥቀስ ይገባል።/////////

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...