ፕሮፌሰር ጋቢሳ እጄታ
ፕሮፌሰር ጋቢሳ እጄታ በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ባንኪሙን በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ላሉት ድርጅቶች የበላይ አመራር አካል (executive heads of U.N. organizations) በሳይንስ በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ ክህሎት ዙርያ ምክር የሚሰጠው የሳይንቲስቶች ቦርድ አባል ሆነው ተመረጡ። ሃያ ስድስት አባላት ካሉት የሳይንቲስቶች ቦርድ አባላት ውስጥ ፕሮፌሰር ጋቢሳ እጄታ ብቸኛ የእርሻ ሳይንቲስት መሆናቸው ተነግሯል።ፕሮፌሠር ጋቢሳ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በ 1965 ዓም ከአለማያ ዩንቨርሲቲ በእፅዋት ሳይንስ፣የማስትሬት እና የዶክትሬት ዲግሪአቸውን ከፕዩድረ ዩንቨርሲቲ በእፅዋት ማዳቀል እና ጄኔቲክስ አግኝተዋል።
በሥራ ዓለም በተለያዩ ድርጅቶች በፕዩድረ ዩንቨርስቲ በረዳት ፕሮፌሰርነት ጨምሮ በዓለም አቀፍ የእርሻ ምርምር ማዕከል -International agricultural research centers (IARCs)፣በዓለም የምግብ ድርጅት (FAO)፣በሮክ ፌለር ግብረ ሰናይ ድርጅት፣በሳሳካዋ አፍሪካ ፕሮግራም (Sasakawa Africa Program) በቦርድ አባልነት አገልግለዋል።
ይህ ብቻ አይደለም ፕሮፌሰር ጋቢሳ በ2002 ዓም የዓለም የምግብ ሽልማት አሸናፊ የሆኑበት እና ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ያስገኘላቸው በምርምር ያገኙት ድርቅ እና በሽታን የመቋቋም ችሎታ ያለው የማሽላ ዝርያ ግኝት ባለቤትም ናቸው።ኢትዮጵያውያን ብቃታቸው በተመሰከረላቸው ባለሙያዎቻችን መኩራትም መጠቀምም መቻል አለብን።መልካም የስራ ዘመን ለሳይንቲስቱ ፕሮፌሰር ጋቢሳ።
1 comment:
let God help him and lead Us too to his way!
Post a Comment