ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, October 20, 2013

''ያልተከፈለ ዕዳ'' የደርግን ''የአስናቀ ገፀ ባህሪ በ ሰው ለሰው ድራማ '' ኢህአዲግን?



''ያልተከፈለ ዕዳ''
''ያልተከፈለ ዕዳ'' የተሰኘ ድራማ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በልጅነት ዘመኔ ማየቴ ትዝ ይለኛል።ድራማው ላይ በዋና ተዋናይነት ትጫወት የነበረችው አለምፀሐይ ወዳጆ ነበረች።ድራማውን ካልዘነጋሁት አለምፀሐይ ባለቤቷ በስውር ታፍኖ ይገደልባታል።የገደለባት ደግሞ የእራሷ ወዳጅ መሳይ ነው።ዘግይታ ግን ደረሰችበት።
አንድ ቀን ታድያ አለምፀሐይ ያልተከፈለ ዕዳ ያለበትን ሰው ልትቀጣው ሽጉጧን በቦርሳዋ ይዛ ሄደች።ከቤቱ ደረሰችና ግቢ ውስጥ ትገባለች እንደገባች ሶፋ ላይ ተቀምጦ የነበረ  ገዳይ ወዳጇን ሰው ውስኪ ሲጠጣ ታገኘዋለች....በቦርሳዋ የያዘችውን ሽጉጥ ታወጣለች።ሰውየው ምን እንዳጠፋ እየጠየቀ ይማፀናታል። ''ያልተከፈለ ዕዳ  አለብህ!'' ብላ ትተኩሳለች።ፊልሙ   ''ያልተከፈለ ዕዳ'' ነውና ከሶፋው ስር የወደቀው ሟች እራሱ እንደገደለው ለማድረግ ሽጉጡን በእጁ እንዲይዝ ይደረጋል።ፖሊሶች ይመጣሉ።ምርመራው ይቀጥላል።

በማግስቱ ነፍሱን ይማረውና ለአባቴ የማታው ድራማ ደስ እንደማይል ስነገረው።ዝም ብሎ ቆየ እና ድራማው ሚስጥር ያለው ይመስለኛል አለኝ።ቀጠለናም  በወቅቱ የነበረውን የደርግ ዘመንን እንደሚያመላክት ነገረኝ።ታፍነው የተገደሉ ንጉሱን የሚወክል ገፀ ባህሪ እንደሚሆን አፍኖ የገደለው ደርግ እንደሆነ ወዳጅ የመሰላት አለምፀሐይ የኢትዮጵያ ገፀ ባህሪ እንደያዘች፣''ያልተከፈለ ዕዳ'' ያለችው ኢትዮጵያ ልጆቿን በደርግ ቀይሽብር አጥታ ያልተከፈላት ዕዳ እንዳለ ስታመላክት ነው አለኝ።በልጅነት አዕምሮ የነገረኝን አሰብኩት።በተለይ በደርግ ዘመን ዘፈኑ ሲወጣ የሚሰጠው ትርጉም ሁሉ ስለነበር ይህ ድራማ አባቴ ካለው ጋር ለመዛመዱ ቅንጣት ታክል አልተጠራጠርኩም።

''ሰው ለሰው ድራማ ተዋናይ የአስናቀ ገፀ ባህሪ ኢህአዲግን?''

በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በተከታታይ የሚታየው የሰው ለሰው ድራማ ዋና ተዋናይ አስናቀ የኢህአዲግን ገፀ ባህሪ ሌሎቹ ደግሞ ከሀገር ውስጥ ተቃዋሚ እስከ ባህር ማዶ፣ከኢትዮጵያ እስከ ልጆቿ፣ከኢህአዲግ ''አቦ አቦ'' ባዮች እስከ ውስጥ አሸርጋጅ የሚወክል ገፀ ባህሪ እንደተካተተበት የኢሳቱ አቤ  ቶክቻው በዛሬው በእሁድ ጥቅምት 10/2006 ዓም ''በዋዛ እና ቁምነገር'' በተሰኘ ፕሮግራሙ ያቀረበበት አቀራረብ አስደናቂ ነበር።
ፕሮግራሙን ከእዚህ በታች ባለው ሊንክ ተጭነው ይመልከቱት።
http://ethsat.com/video/waza-ena-kumneger-oct-20-2013/

No comments:

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...