ከእዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት ብዙዎች ኢህአዴግ/ህወሓት በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ የተለጠፈው ኮከብ የሰይጣን ተከታዮች በአርማነት የሚጠቀሙበት ስለሆነ መነሳት አለበት ብለው ሲሞግቱ መክረማቸው ይታወቃል።አንዳንዶች ጉዳዩ ከፖለቲካ ጥላቻ የሚመስላቸው ነበሩ።ሆኖም ግን ኮከቡ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ እንዲለጠፍ በውቅቱ የነበረው የኢትዮጵያ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያሳልፍ ከእምነቱ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ይኖረዋል የሚል ምንም አይነት ግምት እንደማይኖረው ይታመናል።ሆኖም ግን ኮከቡ የተመረጠበት ሂደት እና ማን ይበልጥ እንደገፋፋ የታሪክ አጥኝዎች የራሳቸውን ጥናት ማድረግ ይችላሉ።በአደባባይ ከተገለጠው የብሔር በሄረሰቦች ጉዳይ ሌላ አጀንዳ ነበረው ወይ? የውጭ ኃይሎች ግፊት ነበር? ወይንስ ከባለስልጣናቱ በተለየ መልክ ጉዳዩን የገፋ ነበር? ይህ ሁሉ ለታሪክ አጥኚዎች የሚተው ነው።
አሁን ግን የዓለም አቀፍ ሚድያ በሆነው በ''ቢቢሲ'' ከሁለት ቀናት በፊት ቅዳሜ ሐምሌ 25/2007 ዓም (August 1,2015) ''Decoding the symbols on Satan's statue'' በሚል አርእስት ስር በፎቶ አስደግፎ ያወጣው ዘገባ ኮከቡ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ ያለው ኮከብ መሆኑ በማያሻማ መልክ ይታያል።በመሆኑም ይህ ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ እና ክርስትናንም ሆነ እስልምናን በቀደምትነት የተቀበለች ሀገር ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ፈፅሞ የሰይጣን ተከታዮች አርማ ሊደረግበት አይገባም።ጉዳዩ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠውም እና ኮከቡ ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ እንዲነሳ የሚመለከታቸው የኢህአዴግ/ህወሓት ባለስልጣናት ሊጠየቁ ይገባል።
በነገራችን ላይ የዳዊት ኮከብ ተብሎ የሚጠራው ባለ ስድስት ጫፍ ሲሆን የሰይጣን ተከታዮች ግን በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ እንዳለው ባለ አምስት ጫፍ ነው።ከእዚህ በታች ቢቢሲ በዘገባው ላይ ከለጠፈው ፎቶ ኮከቡን ብቻ ጉዳያችን ለይታ ከእዚህ በታች ታሳያለች።ዜናውን ከእዚህ በታች ባለው አርዕስት ''ጉግል'' ላይ ፈልጉት።ከእዚህ ባለፈ በዘገባው ላይ የተለጠፈውን ሃውልት ፎቶም ሆነ ሙሉ ዘገባ መዘገቡ ከሞራልም ሆነ ከሃይማኖት አንፃር አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም።የኮከቦቹን ብቻ ''ስክሪን ሾት''ከእዚህ በታች ይመልከቱ።
በጉዳዩ ላይ የዘገበው የቢቢሲ ዘገባ አርዕስት
Decoding the symbols on Satan's statue
- 1 August 2015
- Magazine
ከላይ በተፃፈው አርዕስት ስር ቢቢሲ በዘገባው ከለጠፋቸው ፎቶዎች ውስጥ ኮከቡ ዋነኛ አርማ መሆኑን መረዳት ይቻላል።ከእዚህ በታችከሙሉ ፎቶዎች ውስጥ ኮከቡ የሚታይበት ክፍል ''ስክሪን ሾት'' ተደርጉት ቀርበዋል።ተመልክተው የህሊና ፍርድዎን ይስጡ።
ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
No comments:
Post a Comment