ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, September 30, 2013

በኢትዮጵያ ከሰማይ የወረደው መስቀል ጉዳይ..በሶርያ ሰሞኑን የተሰራው ተአምር... (የቪድዮ ትምህርት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት)

በእዚህ በያዝነው ወር መስከረም 18/2006 ዓም (september 28/2013 ዓም እ.አ.አቆጣጠር) የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ከሰማይ ወረደ ተብሎ ስለተነገረው መስቀል መሰረት አድርጎ እንዲህ ዘግቦ ነበር-
''በአቃቂ ቃሊቲ ገላን ጉራ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን፣ ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ ከሰማይ ወረደ ስለተባለው መስቀል፣ ቅዱስ ሲኖዶስ መርምሮ ውሳኔ  እንደሚያስተላልፍ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳትና የጅማ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አስታወቁ፤ ሕዝቡ የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ በትዕግሥት እንዲጠባበቅ ብፁዕነታቸው አሳስበዋል....''

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከሰማይ የወረደው መስቀል ጋር በተያያዘ  በአጠቃላይ ስለ ተአምራት እንዲሁም በቅርቡ በሶርያ ሀገር በሀገሪቱ ቴሌቭዥንም ጭምር  ከተናኘው ሌላ ተአምር ጋር አያይዞ በአዲስ ዓለም ማርያም  ሰሞኑን ያስተማረው ትምህርት ወቅታዊ ግንዛቤ ይሰጣል።ይመልከቱት።
ጉዳያችን GUDAYACHNgetachewb221@gmail.com

1 comment:

Anonymous said...

hagere nafeqegn. Tewahdo le zelalem nurilign. qalehiwot yasemalin!