ጉዳያችን GUDAYACHN
መስከረም 27/ 2009 ዓም
================================
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር በተወለዱባት ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት) በእሬቻ በዓል ፣በጎንደር፣ጎጃም፣ኮንሶ እና ሌሎችም ቦታዎች የደረሰው እልቂት እንዳሳዘናቸው ከገለፁ በኃላ የሚከተሉት 5 ተግባራት እየተከናወኑ እና ትኩረት የሚሹ መሆናቸውን ገልፀዋል።በንግግራቸው ማጠቃለያ ላይ ያነሷቸው አምስት ነጥቦች በአጭሩ:-
1/ ድርጅታቸው ዝግጅቱን በቅርቡ አጠናቆ ሊደበቅ በማይችል መልኩ ስራው እንደሚታይ፣
2/ የሕዝባዊ እምብተኝነቱ አንቀሳቃሾች በስርዓቱ የኢኮኖሚ አቅም ላይ ማተኮር እና እምብተኝነቱ በሁሉም አካባቢዎች በተመሳሳይ ጊዜ ማድረግ ወያኔ የህዝቡን አቅም እንዳይከፋፍል ያደርጋል፣
3/ የስርዓቱ ወታደሮች፣ፖሊሶች፣በሕወሓት አጋር ድርጅቶች ውስጥ ያሉ ሁሉ ስርዓቱን ከድተው ሲመጡ በሚገባ መቀበል እና ማበረታት ይገባል፣
4/ ስርዓቱ ሕዝብ ከህዝብ ለማጋጨት የሚሰራው ሥራ በመኖሩ በእነርሱ ወጥመድ ውስጥ እንዳንገባ እና ኢላማችን ሕዝብ ሳይሆን ጥቂት የስርዓቱ አቀንቃኞች ላይ መሆኑን ለይቶ ማወቅ እና ዓላማችንም ይህ ብቻ መሆኑን ወያኔን በገንዘብ ለሚደግፉም ጭምር ማስመስከር አለብን እና
5/ ከወያኔ በኃላ የሚመጣው ስርዓት እውነተኛ ስርዓት መሆኑን ለማሳየት እና ኢትዮጵያ ፎቅ እና ፋብሪካ በመገንባት ብቻ ሳይሆን በአስተሳሰብ እና በመንፈስ እየተሸጋገረች መሆኗን ለማሳየት እና የሚመጣው ስርዓት እውነተኛ ዲሞክራስያዊ መንግስት መሆኑን ለማሳየት በሁሉም ለዲሞክራሲ ስርዓት የቆሙ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች፣ሲቪክ ማኅበራት እና የህዝባዊ እምቢተኝነት ተሳታፊዎች ሁሉ የሚጋሩት የጋራ የሽግግር ሰነድ ማዘጋጀት እና በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ማሰራጨት እና የጋራ አስተሳሰብ እንዲይዙ ማድረግ ይገባል።ለእዚህም ይህንንም ከአጋር የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በጋራ እየሰራን ስለሆነ በቅርቡ እውን ይሆናል።
ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment