ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, October 2, 2016

ዛሬ በኦሮሞ ወንድሞቻችን ላይ የፈፀማችሁት ያቀዳችሁትን ነው።ትንሽነት ስለሚሰማችሁ የተከበሩ የአገሪቱን ዜጎች ትገላላችሁ።

ዛሬ መስከረም 22፣2009 ዓም በቢሸፍቱ (ደብረዘይት) በነበረው የእሬቻ በዓል ላይ የአጋዚ ወታደር  ምድሪቱን በኢትዮጵያዊው ኦሮሞ ደም አጨቀዩት።ከምድር በመትረጌስ ከሰማይ በኤሊኮፍተር ተኮሱበት።
በእዚህ የመፈራትን ካባ እንቀዳጃለን ብላችሁ ካሰባችሁ እንደልማዳችሁ ተሳሳታችሁ።የበለጠ ለመሞት የቆረጠ፣የበለጠ ወያኔን ከማጥፋት ሌላ አንዳች የቀረ እንጥፍጣፊ ተስፋ እንደሌለ ደግማችሁ አረጋገጣችሁ።ከሁሉም ከሁሉም በእስረኛው መገናኛ ብዙሃናችሁ የተናገራችሁት ልብ ያቆስላል።

ኢትዮጵያ የኦሮሞው አገሩ ነች።ሌላ አገር አያውቅም።
በቄጤማው ውሃውን ቢመታ፣እንደ አባቶቹ ባህል የፈለገውን ቢያደርግ በኢትዮጵያ በምድሩ ነው።ይህንን የእረቻ በዓል ለማክበር ከመላው የኢትዮጵያ ምድር ተጠራርቶ ሲመጣ፣ ከአውሮፓ እና አሜሪካ ድረስ ሁሉ በብሸፍቱ (ደብረ ዘይት) ምድር ሲሰበሰብ የእርሱኑ መልክ ያላቸው የሕወሓት አጋዚ ወታደሮች እንደ ባዕዳን በመትረጌስ ከምድር እና ከሰማይ በኤሊኮፍተር  እገደላለሁ ብሎ አይደለም። 

እናንተ ግን በሚልዮን በሚቆጠር ሕዝብ ላይ የጥይት መዓት አወረዳችሁበት። ኢትዮጵያ ዛሬ ዳግም አነባች። እርግጥ ነው ዛሬ በኦሮሞ ወንድሞቻችን ላይ የፈፀማችሁት ያቀዳችሁትን ነው። 

ለእዚህ ማሳያው የፖለቲካ ድባቡን ታውቁታላችሁ።ማንኛውም ስብስብ በእናንተ ላይ ቢያንስ የመፈክር ተቃውሞ እንደሚኖር ማንም መሃይም የፖለቲካ ስሜቱን ለክቶ ማወቅ ይችላል።ይህ ማለት ለጥቂት ደቂቃዎች መፈክር ይሰማል።ስሜት ይገለጣል።አበቃ!በዓሉ ሲያበቃ ሕዝብ ተሰነባብቶ ወደቤቱ ይሄዳል።ይህንን ማለት ግን ትንሽነት ለሚሰማችሁ ለእናንተ እንደ ትልቅ ውርደት ቆጠራችሁት ይህ ብቻ ሳይሆን የዐማራ ህዝብን እንደምትጠሉት ሁሉ ኦሮሞን ጥንቃላችሁ እና እንዴት ይደረጋል ብላችሁ በሕዝቡ ገንዘብ በገዛችሁት መሳርያ ባለቤቱ ላይ አርከፈከፋችሁ። ብዙ መቶዎችን ገደላችሁ።

የቀረውን በጭስ እያፈናችሁ ወደ ገደል ከተታችሁት።ይህ ፅሁፍ እየተፃፈም የሞተው ቁጥር ከ300 በላይ እንደሆነ እየተነገረ ነው።አሁንም አስከሬን  ተሰብስቦ አላበቃም። አናሳ ስለሆናችሁ ብዙሃንን ትጠላላችሁ።ትንሽነት ስለሚሰማችሁ የተከበሩ የአገሪቱን ዜጎች ትገላላችሁ።ይህ ቀን በትክክል ይቀየራል።

የአቀያየሩ ዋጋን ግን እንዴት ከፍላችሁ እንደምትጨርሱት ሳስብ ለእናንተው አዝናለሁ።
ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

No comments:

መንግስት ከዲፕሎማሲያዊ መፋዘዝ ይውጣ! የአረብ ሊግ በአባይ ግድብ አንጻር የወሰነውን የጸብጫሪነት ተግባር በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የምላሽ መግለጫ ብቻ የሚበቃ ሊሆን አይገባም።መንግስት ያልሰራው ግዙፍ ስራ ኢትዮጵያን ለአደጋ እንዳያጋልጣት ያሰጋል።

የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መስሪያቤት መንግስት በፍጥነት ሊሰራቸው የሚገቡት አምስት ወሳኝ ዲፕሎማሲያዊ ተግባራት ========= ጉዳያችን አለርት ========= የአረብሊግ አንዱ የሚታወቅበት መለያው እንደባዶ ቆር...