Wednesday, October 12, 2016

ሰበር ዜና - የሩስያ እና የአሜሪካ ፍጥጫ ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል

Photo = independent.co.uk 

ጉዳያችን/ Gudayachn
ጥቅምት 4/ 2009 ዓም 
=======================
የሩስያ እና የአሜሪካ ፍጥጫ ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል።መገናኛ ብዙሃን ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እና የሁለተኛው ቀዝቃዛ ጦርነት ጅማሮ ብለውታል። በሶርያ ጉዳይ ላይ መስማማት አለመቻላቸው እንደዋና የፍጥጫ መነሻ ይወሰድ እንጂ ጉዳዩ ሩስያ ወደ ምስራቅ የመስፋፋት ዝጋት እና የቻይና በምጣኔ ሀብት መለጠጥ የፈጠራቸው ስጋቶች ናቸው ።ላለፉት ወራት ሶስቱም አገሮች በከፍተኛ የሳይበር ጦርነት ላይ እንደነበሩ ተገልጧል።አሁን ጎንቶ የወጣው ፍጥጫ ግን የሩስያ እና የአሜሪካ ሲሆን የሚታየው ምክንያት የሶርያ ጉዳይ ሆኗል።

የፍጥጫውን ደረጃ ለመረዳት የሩስያው ፕሬዝዳንት ዛሬ ባለሥልጣኖቻቸውን ያዘዙትን ትዕዛዝ መመልከቱ በቂ ነው።በዛሬው እለት ፕሬዝዳንት ፑቲን ባለሥልጣኖቻቸው በውጭ ሀገር የሚገኙ ዘመዶቻቸውን ሁሉ ወደ ሀገር ቤት እንዲጠሩ ማዘዛቸውን ´´ዴይሊ ሜል´´ ´በድረ-ገፁ ገልጧል። ለእዚህ ደግሞ የተሰጠው ምክንያት ሩስያ ወደ ጦርነት የምትገባ መሆኑ ሲሆን ሩስያ በሌላ በኩል የኒኩለር አረሯን ወደ ፖላንድ ድንበር ማስጠጋቷ ተሰምቷል። (www.dailymail.co.uk Russia orders all officials to fly home any relatives living abroad, as tensions mount over the prospect of a global war) 

በጦርነቱ ወሬ ላይ የአሜሪካም ሆኑ የሩስያ መገናኛ ብዙሃን እያሟሟቁት ነው። ወደ ሀገራችን ጉዳይ እንምጣ እና በተባለው ፍጥነት ፍጥጫው ከመጣ በኢትዮጵያ ያለውን የኃይል አሰላለፍ ላይ ተፅኖ ይኖረዋል? የውጭ ፖሊሲዎች መቀያየር ይታይ ይሆን? ወይንስ እንደተለመደው የአንድ ሰሞን ወሬ ሆኖ ይቀራል።

ከእዚህ በታች ያለው አጭር ቪድዮ የውጥረቶቹ እድገቶች በያዝነው ዓመት ብቻ ያለውን ገፅታ ያሳያል።


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

No comments:

የመስቀል ደመራ በዓል በንግስት ዕሌኒ ሀገር በግሪክ ቅዳሜ መስከረም 16፣2019 ዓም በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።በግሪክ የምትገንኘው የአቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ምእመናን ለቅዱስ ሲኖዶስ አቤቱታቸውን ደግመው አቀረቡ።

======== ልዩ ሪፖርታዥ ======== በእዚህ ርዕስ ስር የሚከተሉትን ንዑስ ርዕሶች ያገኛሉ።እነርሱም ፡  የመስቀል ደመራ ለምን ይከበራል? ግማደ መስቀሉ  ወደ  ኢትዮጵያ እንዴት መጣ? የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል...