ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, September 16, 2021

ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ነች አንድ ሚልዮን ወታደር ሊኖራት ይገባል። ወጣቶች 12ኛ ክፍል እንደጨረሱ ለስድስት ወራት የብሄራዊ ውትድርና አገልግሎት ቢሰጡ ይጠቀማሉ።መጪው አዲሱ ፓርላማ በፍጥነት ተወያይቶ መወሰን ያለበት ቀዳሚ አጀንዳ መሆን አለበት።

ከአጭር ፅሁፉ ስር ከ800 ሰው በላይ የተሳተፈበት ኢትዮጵያዬ የተሰኘው አዲስ ዜማ ያገኛሉ።

ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ነች።ከ115 ሚልዮን በላይ ለሆነው ህዝቧ እና የእንግሊዝን መሬት አራት ጊዜ ለሚበልጥ መሬቷ አንድ ሚልዮን ሰራዊት ያስፈልጋታል።ይህ ሰራዊት በሰላም ጊዜ ያመርታል።በጦርነት ጊዜ የሀገር ሰላም ያስከብራል።ሰራዊቱ የሀገር ሸክም አይሆንም።የራሱ ግዙፍ ዘመናዊ የእርሻ ቦታዎች፣ዘመናዊ ፋብሪካዎች እና በመከላከያ ስር ያሉ ሌሎች የልማት ድርጅቶች ሊኖሩት ይችላሉ።በመሆኑም ሰራዊቱ በሰላም ጊዜ የመንግስት በጀት የሚበላ ሳይሆን ራሱን በራሱ የሚያግዝ ይሆናል።

በሌላ በኩል ወጣቶች 12ኛ ክፍል እንደጨረሱ ለስድስት ወራት የብሔራዊ ውትድርና ስልጠና እንዲወስዱ ቢደረግ ይጠቀማሉ።የስድስት ወር ስልጠናው ከሱስ ነፃ ሆነው የአካል እና የአዕምሮ ስልጠና ከመውሰድ ባለፈ ተጨማሪ የሙያ ክህሎት እና ስለሀገራቸው ታሪክ፣ባሕል እና በኢትዮጵያ እና ዙርያዋ ባሉ ጂኦ ፖለቲካ ዙርያ ከፍተኛ ባለሙያዎች የሚሰጧቸው ስልጠናዎች እንዲከታተሉ ይረዳቸዋል።በእዚህም ወደ ዩንቨርስቲ ሲገቡም ሆነ ወደ ሥራ ዓለም ሲሰማሩ በሁሉም ዘርፍ ብቁ ዜጋ ያደርጋቸዋል።ይህ ቀጠሮ የማያስፈልገው እና አሁኑኑ መንግስት ሊጀምረው የሚገባው ሥራ ነው።

መጪው አዲሱ ፓርላማ በፍጥነት ተወያይቶ መወሰን ያለበት ቀዳሚ አጀንዳ መሆን አለበት።የኢትዮጵያ የሆነ ዕውነተኛ ዘመን ተሻጋሪ ትውልድ ማፍራት የሚቻለው በእዚህ መልክ ነው። የብሔራዊ ውትድርና ስልጠና በአውሮፓ ኖርዌይን ጨምሮ አሁንም በብዙ የሰለጠኑ ሀገሮች የሚሰጥ ነው።በእዚህ ስልጠና ላይ የተሳተፉ የዩንቨርስቲ መግቢያ ነጥባቸው ዝቅ እንዲደረግ ከመደረጉ በላይ ለስራ በምወዳደሩባቸው ቦታዎች ሁሉ ቅድምያ እንዲያገኙ ይደረጋሉ።

ኢትዮጵያዬ (አዲስ የወጣ ሀገራዊ ዜማ)
ድምፃዊት ራሄል ጌቱ 
ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ 
ከአውታር ቲቪ ዩቱብ የተወሰደ 






No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...