የኢትዮጵያ ምክርቤት (ፓርላማ)
=================
ጉዳያችን/ Gudayachn
=================
የኢትዮጵያ አዲሱ የፌድራል ሀገረ መንግስት ምስረታ እና የክልል መስተዳድሮችን በስምንት ቀናት ውስጥ መመስረት
ኢትዮጵያ አዲስ ሀገረ መንግስት ከስምንት ቀን በኃላ ይመሰረታል።በእዚህ መሰረት ሰኞ መስከረም 24/2014 ዓም አዲሱ የኢትዮጵያ ምክርቤት (ፓርላማ) ይሰበሰባል።በእዚህ ስብሰባም ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚመርጥ ሲሆን በዕለቱ ተመራጩ ጠቅላይ ሚኒስትር ታሪካዊ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።አሁን ባለው ሁኔታ የምክር ቤቱን አብዛኛውን ወንበር የያዘው የብልፅግና ፓርቲ ዕጩ አድርጎ የሚያቀርበውም ሆነ ድምፅ የሚሰጠው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ እንደሚሆን ይጠበቃል።እንደ ብዙዎች የኢትዮጵያውያንም ሆነ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ሁኔታ እና ያለፉት ሦስት ዓመታት ኢትዮጵያን በመምራት ሂደት በሁሉም ዘርፍ ችግሮችን ተጋፍጦ በማሻገር ሂደት አቅማቸውን ያሳዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በቀጣዩ አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን እንዳለባቸው ከገጠር እስከ ከተማ የሚኖሩ የብዙ ኢትዮጵያውያን ፍላጎት ነው።በመስከረም 24 የምክር ቤቱ ስብሰባም ከእዚህ የተለየ አካሄድ እንደማይኖር ከወዲሁ ይጠበቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከፌድራል ሀገረ መንግስት ምስረታ በፊት የክልል መስተዳድሮች ይመሰረታሉ።በእዚህም መሰረት ክልሎች በምርጫ ያሸነፉት ተመራጮችን በነባሮቹ በመተካት አዳዲስ የክልል ፕሬዝዳንቶች እና የክልል ምክር ቤት አፈጉባኤዎች እንደሚመረጡ ይጠበቃል።በእዚህ መሰረት የክልል መስተዳደሮች የሚመሰረቱበት ቀናት እንደሚከተለው ነው።
የኦሮምያ ክልል= መስከረም 15/2014 ዓም
የአዲስ አበባ አስተዳደር= መስከረም 18/2014 ዓም
የደቡብ ክልል= መስከረም 19/2014 ዓም
የአማራ ክልል= መስከረም 20/2014 ዓም
የጋምቤላ ክልል= መስከረም 20/2014 ዓም
የሲዳማ ክልል= መስከረም 20/2014 ዓም
የድሬዳዋ አስተዳደር= መስከረም 21/2014 ዓም
በመጨረሻም መስከረም 24/2014 ዓም የኢትዮጵያ ፌደራል ሀገረ መንግስት ምስረታ አዲስ አበባ ላይ ይከናወናል።
የተከበሩ የፓርላማ አባል ሙ/ጥ/ዲ/ን ዳንኤል ክብረት በሽብርተኛው ህወሓት የተወረሩ ቦታዎች ላይ የተመለከቱትን የተናገሩ - ህወሓት ለትግራይ ሕዝብ የማይራራ አደገኛ ቡድን ነው (አዲስ ቪድዮ)
ቪድዮ = አሚኮ መስከረም 14/2014 ዓም
============
ማስታወቂያ
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ?
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ -
No comments:
Post a Comment