ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, September 4, 2021

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በጳጉሜን ወር ጸሎት እና ምሕላ እንዲደረግ ወሰነ።የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን በንቃት በምትሳተፍበት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤም ከትናንት በስቲያ ተመሳሳይ ውሳኔ አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በወርኀ ጳጉሜን ለሀገር ሰላምና አንድነት መጪው አዲስ ዓመት (ዘመነ ማርቆስ) የሰላም እና የፍቅር የመልካም ሥራና የዕድገት እንዲሆን በመላው ዓለም በምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጸሎትና ምሕላ እንዲደረግ ነሐሴ 26/2014 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ላይ ወስኗል፡፡

በሌላ በኩል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን በንቃት በምትሳተፍበት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤም ከትናንት በስቲያ ተመሳሳይ ውሳኔ ማስተላለፉ ለማወቅ ተችሏል። የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይን አስመልክቶ የአዲስ ዓመት ዋዜማ እንደመሆኑ መጠን የጳጉሜ ወርን አምስት ቀናት ልዩ የጸሎት እና የጾም ጊዜ በየቤተ እምነቱ እንዲሆን በማሰብ ለሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ ለሚገኙ የሚዲያ አካላት አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በዚህም መሰረት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጳጉሜ 1-5 ያለውን ቀን በጸሎት እና ጾም መንፈስ በርትቶ ወደፈጣሪ እጁን እንዲያነሳ ተቋሙ ጥሪውን ያቀረበ ሲሆን በተለይ የመጀመርያው ቀን ሰኞ ጳጉሜን 1 በኢትዮጵያ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ምንም ዓይነት ዓለማዊ ሙዚቃ ባለማሰማት እንዲተባበሩ  የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጥያቄ አቅርቧል።


ከእዚህ በታች የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ቪድዮ ከእዚህ በታች ይከታተሉ።
EOTC TVNo comments:

ሽብርተኛው ህወሓት የአፄ ዮሐንስን ራስ ደግሞ ቆረጠው።

===== ጉዳያችን  ===== በአባታቸው ከተንቤን በእናታቸው ከእንደርታ የሚወለዱት አጼ  ዮሐንስ 4ኛ የነገሱት በቀድሞ ስማቸው ደጃች በዝብዝ ካሣ ተብለው በሚጠሩት ዘመን  ነበር ከአፄ ተክለጊዮርጊስ ጋር አድዋ አካባቢ ተዋ...