ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, September 9, 2021

ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ምጥን መረጃዎች -

በእዚህ ምጥን መረጃዎች ውስጥ - 

- የጦርነቱ ሁኔታ፣
- የባዕዳን እንቅስቃሴ እና 
- ያልተሰሙ አዳዲስ  መልካም ዜናዎች ያገኛሉ።

=============
ጉዳያችን ምጥን 
============

ጦርነቱ 

- የኢትዮጵያ ኃይሎች በሁሉም ግንባሮች የሽብርተኛውን ህወሓት ጀሌ ከሰሜን ወሎ እስከ ሰሜን ጎንደር የበላይነታቸውን አሳይተዋል።
  • ህወሓት ለቆ በሚሄድባቸው ቦታዎች ላይ የዘር ማጥፋት መፈፀሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተጋለጠ ነው።
  • እስካሁን ባለፉት ሦስት ወሮች ውስጥ ብቻ ህወሓት የዘር ማጥፋት የፈፀመባቸው ቦታዎች 
    • አጋምሳ ወሎ 
    • ጋሊኮማ አፋር 
    • በትግራይ በሚኖሩ የኤርትራ ስደተኞች እና 
    • ባሳለፍነው ሳምንት ደግሞ በጭና ደባርቅ ወረዳ የሚጠቀሱ ናቸው።
  • በአማራ ክልል ገበሬው ከመቼውም ጊዜ በላይ ተነስቷል።ከጁንታው ላይ መልሶ መታጠቅ ችሏል።
  • ከኦሮምያ፣አፋር፣ሱማሌ እና ደቡብ የተውጣጡ ልዩ ኃይሎች በግንባሮቹ ውጊያ ላይ ተሳትፈዋል።ትልቁን ድርሻ ግን መከላከያ እና ፋኖ ወስደዋል።

የባዕዳን እንቅስቃሴ 
  • ባዕዳኑ ከካርቱም እስከ ካይሮ፣ከካይሮ እስከ ዲሲ በህወሓት መሸነፍ ተደናግጠዋል።
  • የውሸት ዘመቻውን እንደገና ለመቀስቀስ እየሞከሩ ነው።
  • ለውሸታቸው በተለይ ከትውተር ሰራዊት እየገጠማቸው ያለው ምላሽ ግን ቀላል ሆኖ አላገኙትም 
  • የምዕራባውያን ዜጎችም የራሳቸው ሀገሮች ሚድያዎች እየዋሹ እንደሆነ በእዚህ የኢትዮጵያ ትውተር ዘመቻ እና ማስረጃ ሲቀርብ ትልልቆቹን ሚድያዎች አላስጨነቀም ማለት አይቻልም።
  • ትናንት በእንግሊዝ ፓርላማ በትግራይ ጉዳይ ላይ ስብሰባ ነበር።በስብሰባው ላይ ጫፍ የረገጠ ውሸት ለማውራት የሞከሩ የምክር ቤት አባላት ቢኖሩም፣ኢትዮጵያ እጅግ አስፈላጊ ሀገር ነች።ከሱማሌ ሰራዊቷን እያወጣች ነው ይህ ማለት ከባድ አደጋ አለው ኢትዮጵያን ልንገነዘባት ይገባል ይህች ሀገር ትልቅ ታሪክ ያላት ሀገር ነች በማለት ያስረዱ የምክር ቤት አባላት ነበሩ።
  • ይህ የምክር ቤት ስብሰባ ግን በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ትኩረት አልሳበም።ትኩረት አለመሳቡ እንግሊዞች የፈለጉትን ተፅኖ ፈጣሪ ነን የሚል  ፍላጎታቸውን ባለማሟላቱ አልተናደዱም ማለት አይቻልም።የእንግሊዝ ምክር ቤት ስብሰባን የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ሚድያም ትኩረት አልሰጠውም።
  • የሽብርተኛው ህወሓት መመታት ያስደነገጣቸው ባዕዳን በተለይ ግብፅ እና ሱዳን ከጀርባ አይዟችሁ በሚሏቸው ሃገራት ግፊትም ጭምር በሱዳን ድንበር በኩል ግጭት ለመፍጠር እንደሚፈልጉ ነገር ግን በቅድምያ ሱዳን የሰለጠነው ሳምሪ የተባለው በማይካድራ የዘር ማጥፋት ላይ የተሳተፈው ቡድን ለመላክ እንደሚሞክሩ ግልጥ ነው።
  • ባዕዳኑ ኢትዮጵያን በምጣኔ ሀብት ለማዳከምም መሞከራቸው እንደማይቀር የታወቀ ነው።ስለሆነም ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ምርቷ ላይ መትጋት እና የህዝቡን መሰረታዊ ፍላጎቶች ከውጭ ተፅኖ ማላቀቀ አስፈላጊ ነው።ለምሳሌ የመጪው የመከር ምርት በቁጠባ መሰብሰብ እና ስርጭቱ ላይ ቁጥጥር ማድረግ ያስፈልጋል።
መልካም ዜናዎች 

በእዚህ ሁሉ ውስጥ በኢትዮጵያ እጅግ አበረታች የሆኑ መልካም ዜናዎች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ -

  • መንግስት ከውጭ የሚገቡ ምግቦች ላይ ሙሉ በሙሉ ቀረጥ አንስቷል።በሀገር ውስጥም በምግብ ላይ የነበረውን የቫት ቀረጥ አንስቷል።በእዚህ መሰረት የምግብ ፍጆታዎች ዋጋ በተወሰነ ደረጃ ከአዲስ ዓመት በኃላ መሻሻል ያሳያል ተብሎ ይጠበቃል።በተለምዶም የክረምት ወራት የምግብ ዋጋ የሚንርበት ነው።ምክንያቱም ገበሬው የምርቱን ሁኔታ ካወቀ በኃላ ነው ያለውን ወደገበያ የሚያወጣው።የገንዘብ ሚኒስትር ዴታ ዶ/ር ኢዮብ ለኢትዮጵያ መገናኛዎች እንደገለጡት የቀረጥ ማንሳቱ ሥራ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቀጥል ነው።
  • የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በአፍሪካ የ6ኛ ደረጃ ይዟል።ዩንቨርስቲው በዘመነ ህወሓት በጣም እየወረደ መጥቶ እንደነበር ይታወቃል። አሁን በለውጡ የዩንቨርስቲው አዳዲስ የቦርድ አባላት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ እየሰራ ሲሆን ባለፈው ዓመት ከነበረበት 10ኛ ደረጃ ዘንድሮ አራት ደረጃ አሻሽሎ 6ኛ የሆነ ሲሆን ከምሥራቅ አፍሪካ ደግሞ ቀዳም መሆኑን በዓለም አቀፍ የዩንቨርስቲ መስፈርት ላይ የሚሰራ በአሜሪካ ሀገር የሚገኝ ደረጃ አውጭ በሰጠው መስፈርት መሆኑን ዩንቨርስቲው ገልጧል።
  • የኢትዮጵያ አዲሱ የትምህርት ፖሊስ በአዲስ ዓመት የሙከራ ትግበራ በ2015 ዓም ደግሞ ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ እንደሚውል የትምህርት ሚኒስቴር ገልጧል።የኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲ በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ወደ ስልጣን እንደመጡ በመጀመርያ የተገኙበት ስብሰባ የትምህርት ፖሊሲ የተመለከተ ስብሰባ ነበር።አሁን ተጠንቶ ሥራ ላይ በሚውለው አዲሱ ፖሊሲ ላይ በርካታ ለውጦች የተደረጉበት ሲሆን ከእዚህ ውስጥ የስነምግባር ትምህርት እስከ 6ኛ ክፍል መስጠት እና ከ6ኛ ክፍል በኃላ የስነ ዜጋ ትምህርት ይሰጣል።
  • ኢትዮጵያ ዘንድሮ የነበረባትን ዕዳ ካለፉት ዓመታት በተሻለ መቀነሱ ተነግሯል።በእዚህ መሰረት ከጠቅላላ ምርቷ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ለእዳ ክፍያ ታውል የነበረች ሀገር ዘንድሮ ከጠቅላላ ምርቷ የብድሯ መጠን ከ50% በታች ከመድረሱ በላይ በእዚህ ዓመት በጀት የሀገር ውስጡን ጨምሮ 1ነጥብ 6 ቢልዮን ዶላር ከዘንድሮ በጀቷ ከፍላ እዳዋን ዝቅ አድርጋለች። በዘመነ ሕወሓት ኢትዮጵያ የመበደር አቅሟ ከመውረዱ በላይ የውጭ የግል ባንኮች ደረጃ ወርዳ መበደር ጀምራ ነበር።ዘንድሮ ኢትዮጵያ የንግድ ብድር ካለመውሰዷ ባለይ ሁሉም የመንግስት የልማት ድርጅቶች አንዳቸውም ኪሳራ  ሳያሳዩ ማሳለፋቸው ነው የተገለጠው።
  • በከፍተኛ ኪሳራ እና አላግባብ የሆነ ብድር በተለይ ለህወሓት ሰዎች በመስጠት ችግር ላይ ወድቆ የነበረው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከኪሳራ ወጥቶ ዘንድሮ 3ነጥብ 3 ቢልዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን ገልጧል።ባንኩ ዓመታዊ በዓሉን በአዲስ አበባ ግራንድ ኤልያና ሆቴል ሲያከብር የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንድ አያሌው እንደተናገሩት ባንኩ ከፍተኛ የመዋቅር ለውጥ እያደረገ ሲሆን  ወደ ዓለም አቀፍ ባንክ ለማሸጋገር እየሰሩ መሆኑን ገልጠዋል።
  • ጎንደር ጫት መቃም፣ማስቃም እና መሸጥ ተከልክሏል።የከተማው አስተዳደር ይህንን ሕግ ከነሐሴ 28/2013 ዓም ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን ከእዚህ በፊት በጫት ንግድ ላይ የተሰማሩ በሌላ የንግድ ዘርፍ እንዲሰማሩ ክልሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጧል።ጫት እንደ እንግሊዝ እና ሳውዲአረብያ ያሉ ሀገሮች በአደገኛ ዕፅነት የተመደበ ሲሆን የምቅም ሰው በወንጀል እንደሚጠየቅ ይታወቃል። በዘመነ ህወሓት ህዝቡ ጫት እንዲቅም ከመቸውም ጊዜ በላይ የተለቀቀ ሲሆን በተለይ የጫት መቃምያ ቦታዎች በትምህርት ቤት እና ዩንቨርስቲ አካባቢ ሆን ተብሎ ሲከፈት መንግስት አንዳች እርምጃ ወስዶ አያውቅም። በአንድ ወቅትም አቶ መለስ ወጣቶች በሚሊንየም አዳራሽ ሰብስበው እራሳቸው ጫት እንደሚቅሙ የተናገሩበት ጊዜ እንደነበርም እናውስታውሳለን።
  • በአዲስ አበባ አራት ኪሎ ፓራላማ ፊት ለፊት የሚገኘው ቦታ እየተሰራ ያለው መፃሕፍ ቤት በቅርቡ ይመረቃል።መፃህፍት ቤቱ 38687 ካሬ ላይ ያረፈው መፃህፍት ቤት በአንድ ጊዜ 3500 ሕዝብ የሚይዝ ሲሆን የሕፃናት እና ያዋቄዎች ክፍሎች አሉበት።በተጨማሪም ሶስት አዳራሾች፣ትያትር ቤት እና በቂ የመኪና ማቆምያ ያለው ነው።
የአዲሱ መፃህፍት ቤት ፎቶዎች በከፊል ከስር ይመልከቱ
 
 









============
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።