ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, September 27, 2021

የመስቀል ደመራ በመቀሌ እና ሌሎች የትግራይ ከተሞች በመስቀል አደባባይ ላይ ያልተከበረበት እውነተኛ ምክንያት እና የቪኦኤ መቀሌ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ የተዛባ ዘገባ


==============
ጉዳያችን / Gudayacn
==============
ከዜናው ስር የዘንድሮ የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ  ሙሉ አከባበር ቪድዮ ያገኛሉ።
===============

የመስቀል ደመራ በዓል በመላው ኢትዮጵያ በደመቀ እና ካለምንም የፀጥታ ችግር መከበሩን ለማወቅ ተችሏል።በተለይ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያሪኮች፣የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ፣የባህል ሚኒስትር እና አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች በተገኙበት ቁጥሩ ከግማሽ ሚልዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ በተገኘበት ተከብሯል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በትግራይ መቀሌ የመስቀል ደመራ በመስቀል አደባባይ  አለመከበሩን ለማወቅ ተችሏል።በዓሉ በአጥብያ አብያተ ክርስቲያናት ግን ቁጥሩ ውሱን ሕዝብ በተገኘበት ከስጋት ጋር ተከብሯል።ይህንኑ ሁኔታ የቪኦኤ አማርኛ እና ትግርኛ የመቀሌ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አረጋግጧል።ሆኖም ግን ጋዜጠኛ ሙሉጌታ የደበቀው እውነትም አለ። 

በመቀሌም ሆነ በሌሎች የትግራይ ከተሞች የመስቀል ደመራ በአደባባይ ያልተከበረበት እውነተኛ ምክንያት  የሚከተለው ነው። የመጀመርያው ምክንያት ሽብርተኛው ህወሓት የግዳጅ አፈሳ በከተሞች ውስጥ ከመቼውም ጊዜ በባሰ አፈሳ ላይ በመሆኑ እና ወላጆች ልጆቻቸውን በቤት ውስጥ እየደበቁ እና የቻሉት ደግሞ ራቅ ወዳሉ የገጠር ቦታዎች ከመላካቸውም በላይ ትግራይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ካህናትም  የመስቀል ደመራ በአደባባይ እንዲከበር በማድረግ ልጆቻችንን ወደ ጦርነት አንልክም በማለት በእየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እንዲከበር ወስነዋል።በአጥብያ አብያተ ክርስቲያናትም ወጣቶች በተቻለ መጠን ለመደበቅ የሞከሩ ሲሆን በዕድሜ የገፉ እና ታዳጊ ወጣቶች እየፈሩም ቢሆን በአጥብያ አብያተ ክርስቲያናት ተገኝተው በዝማሬ እና በደመራ አክብረዋል። 

በሌላ በኩል የትግራይ ክልልን በውስን ደረጃ ተቆጣጥሮ የሚገኘው የህወሓት ቡድን በዓሉ በመቀሌ በአደባባይ እንዲከበር ለማስገደድ የሞከረ ቢሆንም የበዓሉ በአደባባይ ሲከበር የተደበቁ ወጣቶች እንዲወጡ እና ለማፈስ በማቀድ መሆኑን ያወቁት የቤተክርስቲያኒቱ ኃላፊዎች አልተቀበሉትም።አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ስጋት ደግሞ ከአፈሳም በዘለለ የሄደ ነው።በትግራይ የሚገኙ የዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ሰራተኞች ያሾለኩትን ዜና ያገኘችው ጉዳያችን እንደተረዳችው፣ህወሓት በመቀሌ በመስቀል አደባባይ የመስቀል በዓል እንዲከበር  የፈለገበት ምክንያት ከፍተኛ የህዝብ እልቂት እንዲፈፀም አድርጎ የፌደራል መንግስት የአየር ጥቃት በሕዝቡ ላይ ፈፀመ ወይንም የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እንዲገኙ ተደርጎ ፍንዳታ ፈፅሞ መንግስት አደረገው በሚል የደረሰበት ሽንፈት ላይ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በመጮህ ነፍስ ለመዝራት የመስቀል ደመራን ሊጠቀምበት ይፈልጋል የሚል ጥርጣሬ በሕዝቡ ውስጥ ሲወራ ነው የሰነበተው። 

በመጨረሻም ከመቀሌ ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ የአማርኛ እና ትግርኛ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ በዓሉ በአጥብያ አብያተ ክርስቲያናት ተወስኖ እንዲከበር የተደረገበትን ምክንያት ከእውነተኛ ምክንያት ከመደበቁም በላይ አንድም ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የቤተ ክርስቲያኒቱን ኃላፊዎች ወይንም የህወሓት ተጠሪዎችን ሳያቀርብ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ዘንድሮ ለማክበር አያስፈልግም አሉ በሚሉ ቀላል ቃላት አልፎታል። የአሜሪካ ራድዮ ከላይ በጉዳያችን የደረሳትን ምክንያቶች አንስቶ ጋዜጠኛ ሙሉጌታን እንደሚጠይቀው ተስፋ አለን። አሁን የትግራይ ሕዝብ እውነታውን ሰብሮ መውጣት አለበት።ህወሓት ማለት ትግራይ አይደለም።ትግራይ ካለህወሓት መኖር ትችላለች።ይህን ሳይናገሩ እና ለእዚህም ሳይታገሉ የትግራይ ሕዝብ በህወሓት ሲፈጅ እየተመለከቱ የራሳቸውን የምቾት ኑሮ በውጭ ሀገር እና በመሃል ሀገር የሚኖሩ የትግራይ ኤሊቶች የትግራይ ሕዝብ በታሪክ ይፋረዳቸዋል።

የ2014 ዓም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ቪድዮ ክፍል 1 እና 2 
ምንጭ - ኢቢሲ 
ክፍል 1

ክፍል 2 







No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...