ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, September 5, 2021

የ2013 ዓ.ም 9 ኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርሃ ግብር ክብርት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ዛሬ እጅግ በደመቀ ስነስርዓት ተካሂዷል።The 9th BEGO SEW award was held today at Addis Ababa Intercontinental Hotel, in the presence of President Sahlewerk Zewde.

የዘንድሮ አሸናፊዎችን ስም እና ያሸነፉበት ዘርፍ ዝርዝር በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ እንዲሁም የዝግጅቱ ሙሉ ቪድዮ በእዚህ ስር ያገኛሉ።
Please find the English translation of the news under Amharic version
=================
ጉዳያችን/ Gudayachn
================
ዘጠነኛው የበጎ ሰው ሽልማት ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።በእዚህ መሰረት በመንግስታዊ የስራ ኃላፊነት በብቃት መወጣት ዘርፍ ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ ሲያሸንፉ በልዩ ተሸላሚ ፀሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ተመርጠዋል።
ለዘንድሮው የበጎ ሰው ሽልማት በአስር ዘርፎች ከ500 በላይ ዕጩዎች ተጠቁመው፥ ከእነዚህ መካከል 30 ሰዎች የመጨረሻ ዕጩ ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል።
በዛሬው ዕለትም በአስር ዘርፎች ለመጨረሻ ዕጩ ከቀረቡት ሶስት ሶስት ዕጩዎች ውስጥ የመጨረሻ አሸናፊዎች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት 
1) የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ የመንግስታዊ የስራ ኃላፊነትን በብቃት የመወጣት ዘርፍ የዓመቱ የበጎ ሰው ሽልማትን አሸንፈዋል።
2) በመምህርነት ዘርፍ ዶክተር ልዑልሰገድ አለማየሁ፤ 
3) በቅርስና ባህል ጥበቃ ዘርፍ ቢላል ሃበሽ የማህበረሰብ ሙዚየም ማዕከል፣ 
4) በሳይንስ ዘርፍ ፕሮፌሰር አለማየሁ ተፈራ፣
5) የማኅበራዊ ጥናት ዘርፍ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ፣ 
6) በንግድና ስራ ፈጠራ ዘርፍ አቶ በላይነህ ክንዴ ፣
7) በዳያስፖራ ዘርፍ  አቶ ኤሊያስ ወንድሙ፣
8) በአርት እና ኪነጥበብ ዘርፍ በዕውቀቱ ስዩም፣
9) በበጎ አድራጎት ዘርፍ አቶ አማረ አስፋው፣  እና 
10) በሚድያ እና ጋዜጠኝነት ዘርፍ ዶ/ር ንጉሴ ተፈራ ሲሆኑ 

በተጨማሪም የ2013 የዓመቱ የበጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ፀሀፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ሆነዋል።
ፀሀፊ ትዕዛዝ ስለ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ የፈጸሙት ጀብድ ከታሪክ ማህደራቸው ተነቧል። በዲፕሎማሲው የሠሩት ታሪክ መቼም አይዘነጋም ተብሏል። ሙሉውን ዝግጅት ቪድዮ ከስር ይመልከቱ።
Bego Sew was founded by Muhaze Tibebat Deakon Daniel Kibret, who is also the recent national election winner to be the member of Ethiopian Parlament, to award people with role models and who made greater contribution for Ethiopia and its citizens. 
The 2021 (2013 EC) 9th Bego Sew award selected a total of 500 persons and suggested and 30 of them as final nominees, in addition to the special award category.
Therefore this year's Bego Sew award winners are:

1. Education: Dr Leulseged Alemayehu
2. Business and Entrepreneurship: Belayneh Kinde
3. Science: Professor Alemayehu Tefera
4. Social Studies: Professor Tilahun Teshome
5. Culture and Heritages: Bilal al-Habashi Community Museum
6. Public/Governmental Services: Dr. Eng. Sileshi Bekele
7. Art: Writer and poet Bewketu Seyoum
8. Humanitarian Works: Amare Asfaw
9. Media and journalism: Dr. Nigussie Tefera
10. Ethiopian diaspora who has significantly contibuted to Ethiopia: Elias Wondimu Ashenafi.

Tsehafi Taezaz Aklilu Habte-Wold has been awarded the annual special ‘Bego Sew Award’ for his contribution to Ethiopia and its people.He served Ethiopia as foreign minister from 1947 to 1958 and Prime Minister from 1961 until 1974.
የ9ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ስነ ስርዓት ሙሉ ቪድዮ / 9th BEGO SEW Award ceremony full video
ምንጭ/video = ባላገሩ ቴሌቭዥን /Balageru TV


============
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...