ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, September 16, 2021

አቶ ልደቱ አያሌው - የህወሓት የተኩስ ሽፋን ሰጪ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ 

አቶ ልደቱ አያሌው የፖለቲካ ሂደቱ ሁሉ ለተመለከተ የሴራ ፖለቲካ ወራሽ ለመሆን የሚደክም ሰው መሆኑን እያስመሰከረ ነው።የኢትዮጵያን ችግር የተረዳበት ወይንም አውቆ ሊያታልለን የሚሞክርበት መንገድ ሁሉ የዕቃ ዕቃ ጫወታ እየሆነ ነው።ሌላውን ሁሉ ትተን ላለፉት ሦስት ዓመታት ብቻ ያለውን  በአጭር ዓረፍተ ነገር ለማስቀመጥ የነገሮች መዘባረቅ ያሳያል።ለውጡ እንደመጣ ወደ ፖለቲካው መጣሁ አለ፣ቀጥሎ ከፖለቲካ ወጣሁ አለ። በመቀጠል በኦኤምኤን ከጀዋር ጋር ቀርቦ ከመስከረም 30፣2013 ዓም በኃላ በኢትዮጵያ መንግስት የለም በሚል ንግግር ኢትዮጵያ ላይ እጅግ አደገኛ ጦር ወረወረ።መስከረም 30 አለፈ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ትዝብቱን በጉያው ይዞ ዝም አለ።ልደቱ ግን ቀጠለ ምርጫው የተራዘመው ለስልጣን ጥም ነው እንጂ በኮሮና ምክንያት አይደለም አለ።

ልደቱን አንዳንድ በአማራ ስም የህወሓትን አጀንዳ የሚያራምዱ  በዘውግ ፖለቲካ ሊያሞግሱት ይሞክራሉ።ሆኖም ግን እነኝህ ዘውገኞች የአማራንም ሕዝብ የማይወክሉ ነገር ግን ጥቂቶችን ለማጭበርበር የሚሞክሩ ናቸው።ልደቱ ይህንን ስለሚያውቅ አንዴ ከአማራ ዘውግ ሌላ ጊዜ ከኦኤምኤን እያለ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ጥቅሞችን የሚነኩ ነገር ግን ህወሓትን በተዘዋዋሪ ሊረዳ ይችላል  ያላቸውን አጀንዳዎች እያነሳ አትርሱኝ የሚል መልዕክቶቹን ይለቃል።

አሁን ባለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ በፀረ ህወሓት ትግሉ ላይ እጅግ በበሰለ እና ቀድሞ በሚያቅድ መልኩ ትልቅ ሚና መጫወቱ የሽብርተኛው ህወሓት ጎራን ፀጉር ያስቆመ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው።አቶ ልደቱ ሰሞኑን የለቀቀው አንድ ፅሁፍ ላይ ብልፅግና ላይ ያተኮረ መስሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ መስከረም ወር ላይ በምክር ቤት እንዳይመረጡ የሚል 'ኡኡታ' መሰል መልዕክት አስተላልፏል።በመልእክቱ ላይ የኢትዮጵያ ዋና ችግር ሽብርተኛው ህወሓትን አንዲት ቃል ሳይናገር የኢትዮጵያ ችግር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው የሚል ኑ ላሞኛችሁ የሚል ፅሁፍ ወርውሮልናል።

ይህ የአቶ ልደቱ ፅሁፍ ለህወሓት የተኩስ ሽፋን ለመስጠት የታቀደ ነው።በወታደራዊ ስልጠና ላይ የሽፋን ተኩስ የሚባል ነገር አለ። አንድ ልዩ ኮማንዶ እስረኛ ለማስለቀቅ በቡድን ሲያጠቃ ሁሉም የኮማንዶ ቡድን ወደ እስር ቤት አይገቡም።ዋናው ቡድን ወደ ውስጥ እስረኞችን ለማስለቀቅ ሲገባ የቀረው ከውጭ ሆነው የሽፋን ተኩስ ይሰጣል።ይህ የሽፋን ተኩስ አንድም ለማደናገር እና የእስር ቤት ጥበቃውን አቅጣጫ ለማስቀየር ሲጠቅም በሌላ በኩል ደግሞ ከውጭ ሌላ አጋዥ ኃይል ከመጣ ለማስቀረት ነው። የአቶ ልደቱ የአሁኑ ፅሁፍ ለህወሓት የሽፋን ተኩስ ለመስጠት የታቀደች ነች።እርሱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ እየተኮሰ ለሽብርተኛው ህወሓት መንገድ ለመክፈት ነው።ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና አመራሩ የህወሓትን አከርካሪ በቅርብም ሆነ በሩቅ ስልት እየመታው እንደሆነ ስላወቀ ያለውን ጦር የወረወረው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ነው።

ለማጠቃለል አቶ ልደቱ የግል ሆቴሉ ያለበት ቅዱስ ላሊበላ እና አካባቢው በህወሓት ጀሌ ህዝቡ ላይ የሚደርሰው በደል እንዴት አልሰማም እና ስለወቅታዊ የኢትዮጵያ ዋና ችግር ሽብርተኛው ህወሓትን ትቶ ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ መስከረም ወር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አይሁኑ ዘመቻ ላይ ተጠመደ? የኢትዮጵያ ችግር ጠቅላይ ሚኒስትር በመቀየር ይፈታል? የኢትዮጵያ ችግር ሽብረትኛው ሀወሓት ነው ወይንስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ? አቶ ልደቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግር ሳይገባው ቀርቶ ሳይሆን የሚደናገርልኝ አገኛለሁ በሚል ተስፋ የፃፋት ነች።ዓቢይን አጥብቀው የሚጠሉ የዓብይ መንገድ አጋንንታዊ መንገዳቸውን እያፈረሰባቸው መሆኑ ያበሳጫቸው ብቻ ናቸው።አቶ ልደቱ የሽፋን ተኩሱ አልተሳካም።
==========///==============

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...