ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, September 18, 2021

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ ከ3.6 ሚልዮን ብር በላይ ለሀገራቸው አዋጥተው ልከዋል።ከእዚህ ውስጥ 1ነጥብ 8 ሚልዮን ብር በእዚህ ሳምንት የላኩት ነው።

የኢትዮጵያ አየርመንገድ አብራሪ ካፒቴን አምሳለ፣ ኦስሎ ዓለም አቀፍ አየርማረፍያ  
(Photo - VG March 8,2019) 
-----------------------------
ጉዳያችን / Gudayachn
----------------------------
ኢትዮጵያውያን በሥራ፣በስደት እና በኑሮ ከሚገኙባቸው የአውሮፓ ሀገሮች ውስጥ ኖርዌይ አንዷ ነች። በኖርዌይ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት የሚጀምረው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከመጀመሩ ጥቂት ዓመታት ጊዜ ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ በእንግሊዝ በስደት በነበሩበት ጊዜ ከኖርዌይ ንጉሳዊ ቤተሰብ ጋር ያደረጉት ግንኙነት መሰረት ሆኖ አገልግሏል።በመቀጠል ኖርዌይ በኢትዮጵያ መዋለ ንዋይ የሚያፈሱ ጥቂት ባለሀብቶች ለምሳሌ በመሃል አራዳ ታዋቂው የሞዝቭኦልድ ኩባንያ ይጠቀሳሉ።በሌላ በኩል ኖርዌይ የኢትዮጵያ የመጀመርያ ባሕር ኃይል በማሰልጠን ረገድም አስተዋፅኦ ነበራት።

የኢትይጵያ እና የኖርዌይ ግንኙነት ወደየተሻለ ደረጃ ያደረሰው ሌላው የግንኙነት መስኮት ደግሞ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1954 ዓም ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ በኖርዌይ ያደረጉት ጉብኝት ነበር። በአሁኑ ጊዜ ኖርዌይ በዓለም ላይ 12 ቁልፍ የልማት አጋሮች ከምትላቸው ሀገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷ መሆኑና የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድረ-ገፅ ያሳያል።በእዚሁ ገፅ ላይም ኢትዮጵያ የሚገኘው የኖርዌይ ኤምባሲ በአፍሪካ ኖርዌይ ካሏት ኤምባሲዎች ትልቁ እና ሰፋ ያሉ ስራዎች የሚሰሩበት መሆኑን ይገልጣል።

በኖርዌይ እና በኢትዮጵያ መካከል የሁለትዮሽ ትብብር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1995 ዓም የተፈራረሙ ሲሆን በ2017 ዓም እኤአ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኦስሎ የቀጥታ በረራ ጀምሯል።በአሁኑ ጊዜ አየር መንገዱ የሰሜን አውሮፓን ከአፍሪካ ጋር ከሚያገናኙት ቀዳሚ አየር መንገዶች ውስጥ ገብቷል።

ይህ በእንዲህ እያለ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ወደ 3ነጥብ 6 ሚልዮን ብር ወይንም 640ሺህ የኖርዌይ ክሮነር አዋጥተው ወደ ሀገር ቤት ልከዋል። ይሄውም በኖርዌይ የሚገኙ የሲቪክ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ኮምንቲ በኖርዌይ ጋር በመተባበር ባለፈው ግንቦት ወር ለዓባይ ግድብ 331,659 የኖርዌይ ክሮነር አዋጥተው ወደ ግድቡ ፕሮጀክት ያስገቡ ሲሆን በያዝነው ሳምንት ውስጥ ብቻ 1 ነጥብ 8 ሚልዮን ብር (342 ሺህ 411 የኖርዌይ ክሮነር) ወደ ሀገር ቤት ልከዋል።በሰሞኑ የተላቀው ገንዘብ ለሰብዓዊ አገልግሎት የሚውል ሲሆን በአማራ እና አፋር ክልል በሽብርተኛው የህወሓት ቡድን ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ እና በችግር ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚውል መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

በመጨረሻም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከመቼውም ጊዜ በተለየ ለሀገራቸው መድረስ ያለባቸው ወሳኝ ጊዜ አሁን ሲሆን፣በውጭ ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ብዛት እና አቅም አንፃር ከእዚህ በላይ ለማድረግ አሁንም እንደሚቻል ለማወቅ ይቻልል።
============================

============
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...