ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, September 13, 2021

በኖርዌይ ሀገራዊ ምርጫ በስልጣን ላይ የነበረው የቀኝ ክንፉ ፓርቲ በግራ ዘመሙ የሰራተኛ ፓርቲ ተበልጧል።ኖርዌይ አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር ይኖራታል።

የኖርዌይ ሰራተኛ ፓርቲ ሊቀመንበር እና አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዮናስ ጋር ስቶረ Jonas Gahr Støre

====================
ጉዳያችን/Gudayachn Report
====================

በኖርዌይ አጠቃላይ ሃገራዊ ምርጫ ሲደረግ ነበር የሰነበተው።ዛሬ ሰኞ መስከረም 3 እኩለ ሌሊት አካባቢ በሀገሪቱ የቴሌቭዥን ጣብያዎች የቀጥታ ስርጭት ውጤቱ እየተገለጠ ነበር በእዚህ መሰረት የሰራተኛ ፓርቲ የተሰኘው የግራ ዘመም ፓርቲ ማሸነፉ ተገልጧል።ስለሆነም አሁን በስልጣን ላይ ያለው የቀኝ ክንፍ ፓርቲ የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ሱልበርግ ስልጣናቸውን ለሠራተኛ ፓርቲ ሊቀመንበር ዮናስ ጋህር ስቶረ  (Jonas Gahr Støre) ያስረክባሉ

ከምርጫው በፊት በኖርዌይ ዋና ከተማ የተሰቀሉ የምርጫ ቅስቀሳ ፖስተሮች ላይ አሁን ያሸነፉት የሰራተኛ ፓርቲ ሊቀመንበር እና መጪው የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዮናስ ጋህር ስቶረ   ከተለያዩ የውጭ ሀገር ተወላጆች ጋር በፈገግታ ሆነው ሲነጋገሩ የሚያሳዩ ፎቶዎች በከተማው ውስጥ ይታዩ ነበር።የኖርዌይ ሰራተኛ ፓርቲ ለኖርዌይ በርካታ ታዋቂ ፖለቲከኞች እና ዓለም አቀፍ ስም ያላቸው ሰዎችን አፍርቷል።ለምሳሌ  አሁን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ፕሬዝዳንት የንስ ስቶልተንበርግ (Jens Stoltenberg) ዛሬ ያሸነፈው የኖርዌይ ሰራተኛ ፓርቲ የቀድሞ  ሊቀመንበር እና የቀድሞው የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደነበሩ ይታወቃል።

የኖርዌይ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች  

በቀኝ አክራሪው እና አሁን በእስር ላይ የሚገኘው ቤቭርክ አቀናባሪነት 77 ንፁሃን የኖርዌይ ወጣት የሰራተኛ ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች የፓርቲውን የወጣት ክንፍ አባላት ኡታያ በተባለ ደሴት ላይ ልዩ ዝግጅት ላይ እንዳሉ የተገደሉት የዛሬ አስር ዓመት ሐምሌ 22፣2011 ዓም እኤአቆጣጠር ነበር።ይህ ድርጊት የኖርዌይ ሰራተኛ ፓርቲ ሃዘን ብቻ ሳይሆን የመላው ኖርዌጅያን እና የሰው ዘር ሁሉ ሃዘን ሆኖ አልፏል።

ዛሬ የኖርዌይ የሰራተኛ ፓርቲ ማሸነፉ ከታወቀ በኃላ የፓርቲው ሊቀመንበር እና መጪው አዲሱ የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር በሀገሩ የምርጫ ውጤት እንደታወቀ የሚደረገው ባህል መሰረት እኩለ ሌሊት ገደማ ከፓርቲያቸው ቢሮ በፓርቲው ባለስልጣናት እና ጋዜጠኞች ታጅበው በእግራቸው በቀጥታ ወደ ኖርዌይ ፓርላማ አምርተዋል።ይሄውም ከእዚህ በፊት እንደሚደረገው በቀጥታ በቴሌቭዥን ለሕዝቡ ተላልፏል።

በመጨረሻም ተሰናባቿ የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ አርነ ሱልበርግ ፓርቲያቸው ለመጪው ጠቅላይ ሚኒስትር መልካሙን እንደሚመኙ ገልጠው ፓርቲያቸው በእየጊዜው እያደገ መምጣቱ እና መሻሻሻሉ አሁን ያገኘው ውጤትም ቀላል አለመሆኑን ገልጠዋል።
============///============
ከጉዳያችን የሚያገኙትን ዜና በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሲያስተላልፉ ምንጭዎ ጉዳያችን መሆኑን መጥቀስ ስነምግባራዊ ግዴታ ነው።


No comments:

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...