ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, September 7, 2021

የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር እና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በመንፈሳዊ ዕይታም ብንመለከተው የሙስሊሙም የክርስቲያኑም እኩል መነሻ ታሪክ እና ሀብቶች ናቸው።የሁለቱም እምነቶች ሊቃውንት ይህንን ያውቃሉ።ህዝቡም ማወቅ አለበት።

==========
ጉዳያችን ምጥን 
==========
የእንቁጣጣሽ ቀን በኦስሎ ምን አለ? (የአንድ ደቂቃ ቪድዮ ከስር ያገኛሉ)

ሰንደቅ ዓላማችን እና የዘመን አቆጣጠራችን በመንፈሳዊ ዓይንም  የክርስቲያኑም የሙስሊሙም የጋራ ሀብት 

ኢትዮጵያ የፈጣሪ ልዩ ሀገሩ ነች።ሁለቱ ቀደምት የኢትዮጵያ እምነቶች ክርስትና እና እስልምና ለዘመናት ተከባብረው፣ተደጋግፈው እና ሕዝብ በአንድነት አስማምተው የኖሩት የሁለቱም እምነቶች መሪዎች መፃህፍቶቻቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ ሊቃውንቶቻቸው ስለሚመሯቸው እምነታቸውን ጠብቀው ኢትዮጵያን በተመለከተ ያስቀመጡልን ውርሶች ሁሉ የጋራ ሀብቶቻችን ሆነው ኖረዋል ወደፊትም ይኖራሉ።አላዋቂነት ክፉ ነው እና በዘመናችን በተለይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን የአንድ ወገን መለያ ብቻ የምትመስላቸው ቢኖሩ የእምነታቸውን ሊቃውንት ጠጋ ብለው አለመጠየቃቸው ያመጣው እንጂ ኢትዮጵያ ስንዱ እመቤት ነች ሲባል ለሁሉም ማለት መሆኑን የበለጠ ባወቅናት ቁጥር የምንረዳው ነው።

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እና የዘመን አቆጣጠራችን ሙሉ ኢትዮጵያዊ ነው።

እውቁ ፀሐፊ ከበደ ሚካኤል “ታሪክና ምሳሌ አንደኛ መጽሃፍ” መግቢያ ላይ “ሰንደቅ ዓላማ የነፃነት ምልክት፣ የአንድ ህዝብ ማተብ፣ የኅብረት ማሰሪያ ጥብቅ ሐረግ ነው….. ሰንደቅ ዓላማ ትዕምርተ ሃይል ትዕምርተ መዊዕ ነው፡፡ ሰንደቅ ዓላማችን አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ፣ ሦስት ቀለማት ናቸው፡፡ ምሳሌያቸውም አረንጓዴው ተስፋ፣ ልምላሜና ሀብት፣ ብጫው ሃይማኖት አበባና ፍሬ፣ ቀዩ ፍቅር መስዋዕትነትና ጀግንነት ነው፡፡”በማለት ገልጠውታል።

በእዚህ ምጥን ፅሁፍ ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን በመንፈሳዊ ዓይን ለሚተረጉሙ አንዱ መነሻ ለኖህ የተገባለት ቃል ኪዳን በሰማይ መታየቱን ነው። የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫም አንዱ መገለጫ የጥፋት ውሃ ጎድሎ ኖህ መሬት ወርዶ ለፈጣሪ ምስጋና ያቀረበበት ነው።አብርሃም እና ኖህ ደግሞ የክርስቲያኑም የሙስሊሙም ጥንት አባቶች ናቸው።ገና በእግዚአብሔር ለሚያምነው የሙሴ ሕግ ሳይሰጥ፣ በአላህ ለሚያምነውም ቁራን ሳይወርድ በቁራንም በመፅሐፍ ቅዱስም  የኖህ ታሪክ ሁለቱም ላይ ተከትቧል።ኢትዮጵያ እንዲህ ነች። እርስ በርሷ የታረቀች!

ለእዚህ ነው ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችም ሆነ ሙስሊሞች ሰንደቅ ዓላማቸው እና ዘመን አቆጣጠራቸው ከእምነት አንፃርም የጋራ ሀብታቸው ነው።ይህንን ለልጆች ማስታወቅ ይገባል።

ስለ ኖህ ቁራን እንዲህ ይላል -

''አላህ ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች የኑህን ሴትና የሎጥን ሴት ምሳሌ አደረገ።ከገቢዎቹም ጋር አላትን ግቡ ተባሉ'' 
 ቁርአን ሱረቱ 66፣10
'' ኑሀንም አለ ጌታዬ ሆይ ከከሃዲዎቹ በምድር ላይ አንድንም አትተው።'' ቁርአን ሱረቱ 71፣26

ስለ ኖህ መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል - 

 ''እግዚአብሔርም አለ። በእኔና በእናንተ መካከል፥ ከእናንተም ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል፥ ለዘላለም የማደርገው የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው፤ ቀስቴን በደመና አድርጌአለሁ፥ የቃል ኪዳኑም ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል።በምድር ላይ ደመናን በጋረድሁ ጊዜ ቀስቲቱ በደመናው ትታያለች፤'' ዘፍጥረት 9፣12-14

ስለሆነም የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር እና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በመንፈሳዊ ዕይታም ብንመለከተው የሙስሊሙም የክርስቲያኑም እኩል መነሻ ታሪክ እና ሀብቶች ናቸው።

የእንቁጣጣሽ ቀን በኦስሎ ምን አለ? ቪድዮውን ይመለከቱ።



 

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...