ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, September 14, 2021

ሰበር ዜና - ደብረፅዮን እና ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ከፍተኛ የተረፈው የህወሓት አመራር የአዕምሮ መዛባት ቀውስ ላይ እንዳሉ ታማኝ መረጃዎች እየወጡ ነው።የትግራይ ሕዝብ እና ዲያስፖራ መመርያ ከእነማን እየተቀበለ እንዳለ ደግሞ ማሰብ አለበት።



Breaking News - Reliable sources confirm Top TPLF leaders, including DebreTsion and Getachew Reda, are in Mental disorder.

የደብረፅዮን እና ጌታቸው ረዳ ጀሌ ሆኖ ያገለገለው የትግራይ ወጣት በአስር ሺዎች እየሆነ በሰሜን ወሎ፣ሰሜን ጎንደር እና አፋር ለመውረር የገባው ወጣት እንደቅጠል እረግፏል።ጦርነቱን በድል የሚያጠናቅቁ የመሰላቸው የህወሓት አመራሮች ከገበሬ ልጆች እስከ መምህራን፣ከመምህራን እስከ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የህክምና ዶክተር እና የጤና ባለሙያዎች፣ከዩንቨርስቲ ሰራተኞች እስከ ጋዜጠኞች ሁሉን እያንጋጋ ወደ ጦርነቱ ከከተተ በኃላ ትግራይን ባዶ አድርጎ አንድ ትውልድ አስፈጅተዋል።

ይህ እልቂት መጀመርያ የትግራይ ሕዝብ እንዳይሰማው ቢሰማም አዲስ አበባ ልንገባ ነው በሚል ድለላ ሕዝቡን ሊያፅናና ሞክረው ነበር።ሆኖም ግን ቆይቶ የትግራይ ሕዝብ በባትሪ ራድዮ ከአሜሪካ ራድዮ እና የጀርመን ድምፅ ሳይቀር እውነቱን ተረዳው።በመቀጠልም በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈፀመው ዘረፋ ሳይቀር ትግራይ ተሰምቷል።የትግራይ ወጣቶች ማለቅ በተመለከተ የተደናገጡ ወላጆች ለቅሶ መቀመጥ ጀምረዋል።በተለይ ከደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ወሎ እያመለጠ ወደ ትግራይ ለመመለስ የሚሞክረው የትግራይ ወጣት ላይ የህወሓት ታማኝ ጀሌ ወዴት ትመለሳለህ እያለ ተኩስ እየከፈተ መሆኑ እና ብዙ ወጣት ማለቁን ከተኩሱ ያመለጡ ወደ ወላጆቻቸው ተደብቀው የተመለሱ መቀሌ ሳይቀር ወሬውን አድርሰዋል።

አሁን ህወሓት የሰራዊቱ እልቂት እና የመዋጋት ፍላጎት መውረድ፣የኢትዮጵያ መከላከያ ምን ዓይነት እርምጃ ቀጥሎ እንደሚወስድ ምንም መረጃ አለመኖር እና የትግራይ ሕዝብ ልጆቼን ብሎ እየጠየቀ መሆኑ የህወሓት አመራሮች የሚይዙት የሚጨብጡት አሳጥቷቸዋል።በቂ መረጃ አለን የሚሉ ወገኖች እንደገለጡት በሳተላይት ስልክ ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣናትን ለማናገር የሞከሩ የምዕራብ የመረጃ ሰራተኞች እና በትግራይ ያሉ የእርዳታ ድርጅቶች ሰራተኞች ሳይቀር  የህወሓት ባለስልጣናት አእምሮ ቀውስ ላይ እንዳሉ ለመረዳት እንደቻሉ እና ይህም ጊዜያዊ የስካር ስሜት አለመሆኑን ከንግግራቸው በመረዳታቸው ደጋፊ የውጭ አካላትን ሳይቀር አስደንግጧል።የህወሓት ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ሰራዊት መቀሌን ለቆ ከወጣ በኃላ በትግራይ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ግድያ ስለፈፀሙ የኢትዮጵያ መከላከያ ወደ መቀሌ ቢመጣ ህዝቡ እንደቀደመው ጊዜ እንደማይደብቃቸው ይልቁንም እንደሚነሳባቸው አውቀዋል።ትግራይን ትተው ወደ ውጭ እንዳይወጡ የሁመራ መስመርን ማስከፈት አልቻሉም።የምዕራብ መስመር ቢከፈት ኖሮ የተወሰነ አመራር ከውጭ ሆኖ እንዲያታግል ተወሰነ በሚል በርካታ አመራሮች በሱዳን በኩል ለመውጣት አቅደው ነበር።በመሆኑም ህወሓት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መቀሌን በተቆጣጠረ ጊዜ ካለበት ሁኔታ ሳይቀር ማሽቆልቆሉ ግልጥ እና የሚታይ ነው።አሁን የህወሓት ባለስልጣናት ከመሃል የትግራይ ሕዝብ፣ከሰሜን ኤርትራ፣በደቡብ የኢትዮጵያ ኃይሎች ከበውታል።የህወሓት ባለስልጣናት በእዚህ ጊዜ የአዕምሮ መዛባት ላይ መሆናቸው ሲያንስ ነው። 

የአዕምሮ መዛባት ከከፍተኛ ጭንቀት እና ተስፋ መቁረጥ የሚመጣ ሲሆን የነገሮች መደባለቅ እና ቅደም ተከተሎችን ከማዛባት በላይ የሚሰሩትን እንዳያውቁ የሚያደርግ አደገኛ የመቀወስ መገለጫ ነው።ይህ የአዕምሮ መዛባት ያለባቸውን አመራሮች ትዕዛዝ የትግራይ ሕዝብ እየተቀበለ መሄድ ከቀጠለ ሙሉ ትውልዱን የማጣት ዕጣ እንደሚገጥመው ባለሙያዎች የሚያሳስቡት ጉዳይ ነው።የአዕምሮ መዛባቱ ደረጃ በደረጃ ባሉ የህወሓት አመራሮች ላይ የታየ ሲሆን ጉዳዩ በሕዝቡም ውስጥ ሳይቀር እየተወራ እና ከአማራ እና አፋር ተደብቀው የተመለሱ የህወሓት ዝቅተኛ እና ከፍተኛ አዋጊዎች ላይ ሁሉ የታየ መሆኑን ሕዝቡ እየተናገረ ነው።

የትግራይን ጦርነት ለማቆም የትግራይ ሕዝብ ደብረፅዮን እና ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣናትን ይዞ ለመንግስት አሳልፎ መስጠት ብቻ ነው የሚጠበቅበት። ይህ ሳይሆን ሕዝብ እና ክልሉ ይጥፋ የሚል ውሳኔ ይዞ በጦርነት ሕዝብ ለመማገድ የሚፈልጉ በጦርነት ለማትረፍ የሚሯሯጡ መሆናቸው ግልጥ ነው።አሁን የታወቀው ጉዳይ ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣናት የአእምሮ መዛባት ህመም ላይ መውደቃቸው ነው።ይህንን ለመረዳት ጌታቸው ረዳ በትውተር ገፁ፣ደብረፅዮን ደግሞ በድምፅ እየሰጡ ያለውን ቃለ መጠይቅ በቀላሉ መመልከት በቂ ነው።
==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...