ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, July 27, 2021

ተረፈ ህወሓት እና ጀሌው እየተነሳ ነው? ወይንስ ሊነሳ ወደማይችልበት አዘቅት እየወረደ? ብሔራዊ ጦር ሙሉ በሙሉ ወደ ጦርነቱ አለመግባቱስ የሚደነቅ ስልት ወይንስ የሚነቀፍ?

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ (ዶ/ር)

የሁሉንም ጥያቄዎች ምላሾች በእዚህ ፅሁፍ ውስጥ ያገኛሉ።

አንድን ጉዳይ ከስር መሰረቱ መመልከት እና ዕውነታውን ሀቅን መሰረት ባደረገ መልኩ መመልከት ተገቢ ነው።ከእዚህ በተለየ  በሆይሆይታ እና በየቦታው በተበጣጠሱ የማኅበራዊ ሚድያ ሽርፍራፊ ቪድዮዎች እና በውሸት ሰበር ዜና በተጥለቀለቀው የዩቱብ ተዳዳሪዎች የህልም ወሬ እና እየሆነ ያለው እውነታ ፈፅሞ የተለያየ ነው። 

ሽብርተኛው ህወሓት አመራሩ ከ70 በመቶ በላይ ሳይደመሰስ በፊት ማለትም የዛሬ 9 ወር ገደማ  ከ300 ኪሎ ሜትሮች በላይ የሚወነጨፍ ሚሳኤል ይዞ ነበር።በአንድ ወቅት በጠቅላይ ዓቢይ እንደተገለጠው የኢትዮጵያን የመከላከያ አቅም እስከ 80 በመቶ በእጁ ነበር።በልዩ ኃይል ስም ያሰለጠነው ሰራዊት ወደ 200 ሺህ ይጠጋ ነበር።በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጦር ውስጥ ከመገናኛ ክፍሉ እስከ አየር ኃይል የራሱ የሚላቸው ከፍተኛ መኮንኖች ነበሩ።የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብትን ከአስመጪ እና ላኪ እስከ ሆቴል እና ማዕድን ማምረት ውስጥ ሁሉ እጁ ነበረ።ይህ ሁሉ በእጁ የነበረው በኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ እየተመራ ያለው የለውጥ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ በኃላ ሁሉ ነው።

በሕዝባዊ ማዕበል ፈርጥጦ መቀሌ የገባው የህወሓት አመራር እና ጀሌው ፈርጥጦ ሲገባ ሁለት ነገሮችን ታሳቢ አድርጎ ነበር።እነርሱም - የመጀመርያው የመሃል ሃገሩን  የአማራ እና የኦሮሞን እንዲሁን የሱማሌ እና ደቡብን ጭምር የጦርነት ማዕከል ማድረግ እና ትግራይን እጅግ ሰላማዊ መዳረሻ ማድረግ ሲሆን፣ሁለተኛው ደግሞ በመሃል ሀገር በሚለኩሰው ጦርነት ህዝብም ሆነ ዓለምአቀፍ የጥቅም ተጋሪ ባዕዳን አዣዞቹ ወደ ስልጣን ተመልሶ ሀገር እንዲረጋጋ እለመናለሁ የሚሉ ሕልሞች ነበሩ።በእዚህም መሰረት ከቡራዩ እስከ ጌድዮ፣ከጅጅጋ እስከ መተከል፣ከሻሸመኔ እስከ ኮንሶ ከፅንፈኛ ኃይሎች ጋር በመሆን በቆሰቆሳቸው እና ባስቆሰቆሳቸው ግጭቶች ብዙ ሺዎች ተፈናቀሉ፣አያሌዎች ሞቱ፣የእምነት ቦታዎች ተቃጠሉ፣በርካታ ንብረት ወደመ።ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቱን ለይቶ አውቆ የተፈናቀሉትን እየመለሰ፣ቤተሰቦቻቸው የሞቱባቸውን እያፅናና ሁሉን መሻገር ቻለ።በህወሓት ወደ መሃል ሀገር የተወረወረው ትኩስ የመከራ ድንች መሃል ኢትዮጵያን እንደፈለጉት ሊያተራምስ አልቻለም።ስለሆነም ''ጥራ ቢሉት እራሱ መጣ'' እንዲሉ መጨረሻ ላይ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የተቀናጀ ጥቃት ከፍቶ ኢትዮጵያን ከመከላከያ ሰራዊት ውጪ አድርጎ ኢትዮጵያን ለባዕዳን ለማስረከብ ተደራደረ።አንዳንድ ባዕዳን የህወሓትን በመከላከያ ላይ የሚፈፅመው ጥቃት ቀድመው እንደሚያውቁ ቆይቶ የታዩ ምልክቶች ያሳያሉ።

ጥቅምት 24፣2013 ዓም በትግራይ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ሲፈፅም አሁንም 'ትኩስን ድንች' ወደመሃል ኢትዮጵያ ወርውሮ መሃል ሃገሩን ለማጋጨት እና ወደ የማያባራ እልቂት ለመክተት ማቀዱ ግልጥ ነበር። ለእዚህም ዋና ማሳያው በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት እንደፈፀመ ወዲያውኑ ወደ አማራ እና አፋር ክልል ጥቃት ለመሰንዘር ሞክሮ ነበር።ሆኖም ግን የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር እንዲሁም የአማራ ልዩ ኃይል እጅግ በፈጠነ እና በሚያስደንቅ ጀግንነት ህወሓት እና ጀሌውን ከመመከት አልፎ ማጥቃት ቻለ።የመከላከያ ኃይሉ በቀናት ውስጥ መላዋ ትግራይን መቀሌን ጨምሮ ከህወሓት ጀሌ ነፃ አወጣት።ይህ ብቻ አይደለም የህወሓት ጥርስ የነበረው የመካናይዝድ ጦር እና ሚሳኤል ጨምሮ መከላከያ ኃይል መልሶ ተረከበ።የህወሓት አመራር ከ70 በመቶ በላይ ያለው አመራሩ እና ጀሌው እርምጃ ተወሰደበት።የቀረውን የጦር መሳርያ ደግሞ መከላከያ ባለበት አመከነው።በእዚህ ተረፈ ህወሓት እና ጀሌው እየተነሳ ነው?  ወይንስ ሊነሳ ወደ የማይችልበት አዘቅት እየወረደ? 

መከላከያ በትግራይ ከቆየ በኃላ ሰኔ  21/2013 ዓም በፖለቲካዊ ውሳኔ መከላከያ ሰራዊት ከመቀሌ ወጣ።ሰራዊቱ ከመቀሌ የወጣበትን ምክንያት በግልጥ ተነግሯል።የትግራይ ገበሬ የሚያርስበት ጊዜ ለመስጠት እና በመጪው ዓመትም የህዝብ እና የሀገር ሸክም እንዳይሆን እና  በህወሓት እና ጀሌው ፕሮፓጋንዳ የተወናበደው ሕዝብ በቂ የጥሞና ጊዜ እንዲያገኝ ነው።ይህም ሆኖ ግን ህወሓት ወደ መሃል ሀገር ልትገፋው የፈለገችው የጦርነት አውድማ እዚያው ትግራይ ውስጥ ገብቶ ትግራይን ሰላም አሳጣት።መከላከያ ከወጣ በኃላ ትግራይ ለትግራይ ሕዝብ ሲኦል ሆናለች።ወጣቶች ይታፈሳሉ፣እናቶች ለተረፈ ህወሓት ስልጣን ሲባል ልጆቻቸውን ካልሰጡ እርዳታ እንደማይሰጣቸው ተነግሯል።ማጅራት መቺው በከተማ፣አድፍጦ የሚዘርፈው በገጠር ተሰማርቶ ሕዝቡን እያመሰ ነው።ሕፃናት እየተነዱ ወደ ጦርነት ተማገዱ። በራያ ግንባር ብቻ በአንድ ቀን ብቻ በአስር ሺዎች የህወሓት ጀሌ ረገፈ።አስከሬኖቹን ለመቅበር ሳምንታት አይበቁንም ሌሊት አስከሬኖቹን ለመብላት የሚመጡት ጅቦች አስቸገሩን ያለው የአፋር አርብቶ አደር በራሱ መቅበር ይዟል።
በእዚህ ተረፈ ህወሓት እና ጀሌው እየተነሳ ነው?  ወይንስ ሊነሳ ወደ የማይችልበት አዘቅት እየወረደ? 

ዛሬ ትግራይ በኢትዮጵያ ካሉት ክልሎች በሙሉ የተጎሳቆሉ ሰዎች የሚኖሩባት፣በ1ነጥብ 2 ሚልዮን ይቆጠር የነበረው በምግብ እርዳታ የሚኖረው ሕዝብ አሁን ሁሉም በሚያስብል ደረጃ ተመፅዋች ሆኗል።ይህንን የተራበ ሕዝብ በምግብ እየደለለ ወደጦርነት ለመክተት ተረፈ ህወሓት እየሞከረች ነው።ትምህርት ቤቶች፣የጤና ጣብያዎች፣ገበያዎች ባዶ ሆነዋል።የትግራይ ወጣቶች በሙሉ ካሉበት ክፍል ወደ የሚቀጥለው ሳይሸጋገሩ ባሉበት ይደግማሉ።የተረፈ ህወሓት እና ጀሌው የመሃል ሀገር ደጀን ኢትዮጵያን ለማተራመስ ሲወራጭ የተደረሰበት ከሆቴል ንግድ እስከ አስመጪ እና ላኪ ሕጋዊ እርምጃ እየተወሰደ ነው።በኤፈርት እና ትግራይ ልማት ማኅበር ስም ሲመዘብር የነበረው የምጣኔ ሀብት ጉልበት ተሽመድምዷል።አሁን የቀረው በአዲስ አበባ በራይድ ታክሲ እየተሹለከለከ ሴራ የሚያሴረው ነው።ይህም በዕይታ ውስጥ ስለሆነ የትም አያመልጥም።በእዚህ ተረፈ ህወሓት እና ጀሌው እየተነሳ ነው?  ወይንስ ሊነሳ ወደ የማይችልበት አዘቅት እየወረደ? መልሱ ግልጥ ነው።ህወሓት እየተናሳ ሳይሆን ሊነሳ ወድየማይችልበት አዘቅት እየወረደ ነው።የቁልቁለት ጉዞው በአዘቅት ውስጥ በመግባት የሚቆም አይደለም።ታሪኩም ይቀበራል።አሟሟቱ እና አቀባበሩ ሲተረክ ህወሓት ለመጪዎቹ ትውልዶች ሁሉ 'በዘራችሁ አይድረስ' በሚል ዓረፍተ ነገር የታጀበ ይሆናል።ዛሬ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ትግርኛ በመናገራቸው ብቻ የተሰለፉ ያፍራሉ።ለልጅ ልጆቻቸውም የሚያቆዩት የባንዳነት ጠባሳ ብቻ ይሆናል።የባንዳነት ጠባሳ አያኮራም።አንገት ያስደፋል።ከእዚህ ውርደት ለመዳን 'አንድ ሐሙስ በቀረው' ተረፈ ህወሓት ላይ ተነስቶ የትግራይን ሕዝብ ነፃ ማውጣት ብቻ ነው ያለው መፍትሄ።

ይህ በእንዲህ እያለ የኢትዮጵያ መከላከያ ሙሉ በሙሉ ወደ ፍልምያው አለመግባቱ ትክክለኛ ስልት ነው ወይንስ ሌላ? ይህንን እያነሱ አንዳንዶች ሕዝብ ለመከፋፈል ጥቂቶች ደግሞ ሳይገባቸው የሚያነሱት ጥያቄ ነው።እዚህ ላይ ኢትዮጵያ በዙርያዋ እና በማዶ ያሉ ባዕዳን ታሪካዊ ጠላቶቿን የማይመለከቱ እና የኢትዮጵያ ጠላቶች ዋና ግብ ያልገባቸው ናቸው።ከተረፈ ጁንታው እና ጀሌው ጋር የኢትዮጵያ መከላከያን በትነው ኢትዮጵያን ለመቀራመት የተነሱ ባእዳን ዋና ግብ እና ስልት የሚያጠነጥነው በመከላከያ ሰራዊትን አቅም ማድከም እና በእርስ በርስ ጦርነት መወጠር ነው። የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ከተረፈ ህወሓት ጀሌ ጋር ሲፋተግ በሚፈጠረው መድከም ሁለት ክፍተቶች እንዲፈጠሩ የባንዳው ተረፈ ህወሓት ጀሌ እና የኢትዮጵያ ባዕዳን ጠላቶች ምኞቶች ናቸው።እነርሱም ፣ የመጀመርያው መከላከያው ሲዳከም ባዕዳን በኢትዮጵያ ላይ የቀጥታ ጥቃት እንዲፈፅሙ ስለሚረዳቸው እና ሁለተኛው ደግሞ የመከላከያው ከተረፈ ህወሓት እና ጀሌው ጋር ሲዋጋ በመሃል ሀገር የጎሳም ሆነ የሃይማኖት የፅንፍ ኃይሎች ማዕከላዊ መንግስትን እንዲገዳደሩ በማድረግ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የታቀደ ዕቅድ ነው። 

እነኝህ የኢትዮጵያ መከላከያን በተረፈ ጁንታው ሽብር ውግያ ወጥሮ ኢትዮጵያን የማፍረስ ሙከራ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ መንግስት በሚገባ ተረድቶታል።በመሆኑም መከላከያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ''ልፍያ ውስጥ አንገባም'' በማለት የገለጡት የመከላከያውን ወደ የማያበቃ ፍትግያ  በመክተት በመደበኛ ውግያ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ለሚፈልጉ ባዕዳን ሃገርን ከማጋለጥ የሽብርተኛውን የተረፈ ጁንታ እብሪት ከመላዋ ኢትዮጵያ በተውጣጡ የልዩ ኃይሎች፣የደጀን ተዋጊ እና በሚልሻም ጭምር ትዕቢቱን ከአፈር እየደባለቀ የመከላከያ ሰራዊት እና የአየር ኃይል አስፈላጊ በሆኑ ቁልፍ እና ስልታዊ ስራዎች እንዲያግዝ መደረጉ የኢትዮጵያን ባዕዳን ጠላቶች እና ባንዳው ተረፈ ጁንታውን ያስደነገጠ እና ዕቅዱን ሁሉ ያከሸፈበት ነው። ዛሬ ሺዎች ከመላዋ ኢትዮጵያ የተረፈ ጁንታውን እና ጀሌውን ለመደምሰስ ተሟል።የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል እስኪደመም ድረስ ደጀኑ ሕዝብ ታጥቆ ደርሷል።ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚሞክር እንዴት እንደሚፈራርስ ዓይናችን የሚያይበት ቀን ደርሷል።ከውስጥ እና ከውጪ ሆነው በወሬ ኢትዮጵያውያንን ለማተራመስ የመንግስት ተቃዋሚ እና የአማራ ሕዝብ ወዳጅ እየመሰሉ ሊያታልሉ የሚሞክሩ እና የተረፈ ጁንታው የውስጥ አርበኛ ለመሆን ትግርኛ መናገርን እንደ መስፈርት አድርገው የትግራይን ሕዝብ ለማታለል የሚሞክሩ በአዲስ አበባ እና በውጭ በምቾት የሚኖሩ የሕፃናት ደም ተጎንጪዎች ከሃይማኖት ድርጅት እስከ ምሁር ነኝ ባይ፣ከጠጅ ቤት እስከ መንግስት መስርያቤት ያሉ ሁሉ  ከህዝብ ዓይን አያመልጡም።አንድ በአንድ ይጋለጣሉ።ፍርዳቸውን ይቀበላሉ።==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ታላቅ ተልዕኮ የሚኖረው ሀገራዊ የምምክር ኮሚሽን በተመለከተ ምን ያህል እናውቃለን?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ባካተተ መልኩ አዋቅሯል። በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉት ነጥቦች ምላሽ ያገኛሉ፡  ኮሚሽኑ እንዴት ተመሰረተ?  የኮሚሽኑ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት ተመ...