ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, July 20, 2021

መንግስት ጁንታውን ትክክለኛ ቀለበት ውስጥ አስገብቶታል።ጁንታው የትግራይ ሕዝብን እያሰቃየ ነው።



  • በጁንታው በግድ የተሰለፉ ታዳጊ ሕፃናት ወደ ኃላ ከዞራችሁ ትገደላላችሁ ስለተባሉ ሕፃናቱ በአማራ ክልል ያሉ መንደሮች ሲደርሱ ደብቁን እያሉ እያለቀሱ መሳርያቸውን እየጣሉ ወደ መንደሮች ሲገቡ ታይተዋል።

ጁንታው በሶስቱም ግንባሮች ክፉኛ ተመትቷል።

የተረፈው የህወሓት አመራር ግራ ተጋብቷል።ትግራይ ከውስጥም ከውጪም ሲኦል ሆናበታለች።ከውስጥ የተፈጠረው ቀውስ ከባድ ነው።ከትግራይ ውጪ ለማዝመት በግዳጅ የሰበሰባቸውን ጀሌዎች በላከበት ሁሉም ግንባሮች ክፉኛ እየተመታ መላወስ አልቻለም።በምዕራብ በኩል የላከው ጀሌ በፀለምት ማይጠብሪ በኩል የመጣው ሙሉ በሙሉ ተደምስሶ ተመልሷል።በራያ በኩል የተከፈተው ከፍተኛ ኪሳራ አስከትሎበታል በተለይ በእዚህ ግንባር በጁንታው በግድ የተሰለፉ ታዳጊ ሕፃናት ወደ ኃላ ከዞራችሁ ትገደላላችሁ ስለተባሉ ሕፃናቱ በአማራ ክልል ያሉ መንደሮች ሲደርሱ ደብቁን እያሉ እያለቀሱ መሳርያቸውን እየጣሉ ወደ ሕዝቡ መንደር ውስጥ ሲገቡ ታይተዋል።


ሦስተኛው የጁንታው ጥቃት የነበረው በአፋር ግንባር ነበር።በእዚህ ግንባር ያለ የሌለ ጉልበቱን አሰባስቦ ተኩስ የከፈተው ጁንታ ዋና ዓላማው የአፋር አርብቶ አደሮችን መዝረፍ እና መግደል የሚችለውን ገድሎ የጅቡቲ አዲስ አበባ መንገድ ለመቁረጥ ነበር።ይህ ትናንት እና ዛሬ የተደረገው ውጊያ የአፋር፣የኦሮሞ እና የአማራ ልዩ ኃይሎች የተሳተፉበት ሲሆን በውጊያው ከአስር ሺህ በላይ በግድ እና በውድ የተሰለፉ የጁንታው ጀለዎች ማለቃቸው ነው የተሰማው።ቁስለኞቹ በብዛት ወደ አማራ እና አፋር ክልል ተወስደው እየታከሙ ሲሆን፣የአስከሬን መቅበሩ ሥራ እስከ መጪዎቹ አስር ቀናት እንደማይጠናቀቅ ነው የተሰማው።የሰው እልቂቱ በእዚህ ደረጃ ላይ እያለ ነው በውጪ እና በሀገር ውስጥ ያሉ ነገር ግን እነርሱ እና ቤተሰቦቻቸው በምቾት እየኖሩ ምስኪኑ የትግራይ ወጣት ግን እንዲሞት ግፋ ይሉታል።

መንግስት ጁንታውን ትክክለኛ ቀለበት ውስጥ አስገብቶታል።ጁንታው የትግራይ ሕዝብን እያሰቃየ ነው።

መቀሌ ኑሮ ሲኦል ሆኗል።የንግድ እንቅስቃሴ የለም።ገንዘብ ሳይኖር እንዴት እና ምን ትነግዳለህ? መብራት የለም።አንዳንድ ቦታዎች ያሉ ጀነረተሮች የሚሰሩበት ነዳጅ እየተሟጠጠ ነው።ለመክናዎች አንዳንድ ነዋሪዎች በችርቻሮ በሃይላንድ ከሚሸጡ ሰዎች እየገዙ ሲጠቀሙ ቪኦኤ ትግርኛ በፊልም አስደግፎ ከትናንት በስትያ አሳይቷል።በትግራይ ከተሞች እና ገጠር ቦታዎች ላይ የሚገኙ የጁንታው ታጣቂዎችን ማጅራት እየመታ መሳርያ የሚወስደው ወጣት በዝቷል።ለሚጣሱ ሕጎች ዳኛ የለም።የመንግስት መዋቅር ባለመኖሩ የመንግስት ሰራተኛው ደሞዝ ከተከፈለው አንድ ወር ሆነው። በኢትዮጵያ ኑሮ የመንግስት ሰራተኛ ከአንድ ወር የበለጠ አስቤዛ መግዛት አይታሰብም። 

ከእዚህ ሁሉ በላይ ሌላ አዲስ ፈተና ደግሞ የትግራይ ወጣት ላይ ተደቅኗል።ጁንታው ከተማ እና ገጠር የተገኘውን ወጣት ማፈስ እና ለሶስት ቀናት ተኩስ እያለማመደ ወደ ግንባር መላክ ጀምሯል። እናት ልጇን ለማዳን የማትችልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።እናቶች ልጆቻቸውን ለማዳን መቻል ቀርቶ ጁንታው በጅምላ ህዝቡ ገንዘብ እና ምግብ እንዲያዋጣ ጥሎበታል።ለራሱ ተረጂ የሆነ ሕዝብ መግብ አምጣ ይባላል። የእናቶች ሃሳብ ይህ ብቻ አይደለም።ልጆቻቸው ክትምህርታቸው ቀርተዋል።ይህ ማለት ዘንድሮ ሁሉም ባሉበት ክፍል መድገም የግድ ይሆንባቸዋል። በመጪው ጥቅምት ወር ላይ በመላ ኢትዮጵያ የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ይሰጣል። የትግራይ ተማሪዎች ግን ዘንድሮ ለፈተናው መቀመጥ አይችሉም።

ይህ ሁሉ የትግራይ ወጣቶች ፈተና፣የእናቶች ሰቆቃ እና የተማሪዎች ቢያንስ በአንድ ዓመት ወደኃላ መቅረት እንዲሁም በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች በከንቱ ጦርነትን መርገፍ ዋናው ምክንያት ለዶ/ር ደብረፅዮን፣ጌታቸው ረዳ እና ፃድቃን ስልጣን ጥበቃ ሲባል የሚደረገው ከንቱ ልፋት ነው።ጁንታው የትግራይን ሕዝብ ከጉሮሮው መንጠቁ ሳይበቃው በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ዕርዳታ በኩል ወደ ትግራይ በአፋር መስመር በኩል እህል ጭነው ሊገቡ የነበሩ 169 ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች የጫኑ የጭነት መኪናዎች ከጁንታው በአስሩ ላይ በመተኮሱ 169ኙም መኪናዎች ወደትግራይ ከመግባት ተገትተዋል።የዕርዳታ መኪናዎቹ ወደትግራይ የማይገቡት በተደረገባቸው ተኩስ መሆኑን እራሱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባወጣው መግለጫም አምኗል።ቢቢሲ አማርኛም ይህንኑ ጠቅሶ ነገር ግን ማን ተኮሰ የሚለውን ቢቢሲ አማርኛ አለመናገሩ ብዙዎች ዘንድ ግርምት ፈጥሯል። ምክንያቱም ሮይተርስ ብቻ ሳይሆን እራሱ የጁንታው ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳም አፋር አርብቶ አደር ላይ ተኩስ መክፈታቸውን አምነው እያለ ቢቢሲ በዕርዳታ መኪናዎቹ ላይ ማን እንደተኮሰ ለመፃፍ ስሽኮረመም ታይቷል።

ባጠቃላይ የተረፈው የጁንታው አመራር የትግራይን ሕዝብ ወደ ጦርነት መማገድ ብቻ ሳይሆን ለዕርዳታ የመጣለትን ምግብ እንዳይገባ ተኩስ ከፍቶበታል። በአማራ እና አፋር ያሉ  የትግራይ አዋሳኝ ወረዳዎች እና ከተሞች  ያሉትን ነዋሪዎች እንዲፈናቀሉ እያደረጉ ነው። መንግስት  የመከላከያ ኃይልን በሙሉ ኃይል ገና አላንቀሳቀሰም።እስካሁን በሶስቱም ግንባሮች የተመታው የጁንታ ኃይል ባብዛኛው በአማራ ልዩ ኃይል እና ከሁሉም ክልሎች በተውጣጡ ልዩ ኃይሎች ነው።የሱማሌ ልዩ ኃይልም በምክትል አዛዥ ኮለነል እየተማራ ዛሬ አዲስ አበባ መግባቱ እና ወደ ግንባር መንቀሳቀሱ ተሰምቷል።የደቡብ፣የሲዳማ፣የኦሮሞ፣የሐረር እና የሌሎች ክልሎች ልዩ ኃይሎች ወደ ግንባር ቀደም ብለው ተንቀሳቅሰዋል።መንግስት ግን ባቀደው መልክ የጁንታውን ኃይል በትክክለኛ ቀለበት ውስጥ አስገብቶታል። በእዚህም የኢትዮጵያ የቅርብ እና የሩቅ ጠላቶችም በጭንቀት ሁኔታውን እየተከታተሉ ነው።በተለይ ጁንታው ኢትዮጵያን ለመበተን የመነሳቱን ሂደት በከፍተኛ ደረጃ የሚደግፉት የውጭ የጠላት ኃይሎች ለጁንታው ምናልባት በሳተላይት የተደገፈ መረጃ ከመስጠት እና  እንደ ግብፅ ያሉት ደግሞ የወታደራዊ አማካሪዎቻቸው በምክር ለመርዳት ከመሞከር ውጪ ምንም ሊያደርጉ አይችሉም።የሰሞኑ ጁንታው በአፋር አርብቶ አደሮች ላይ ተኩስ ከፍቶ የጅቡቲ አዲስ አበባ መንገድን እንዲዘጋ የሚለው ምክረ ሃሳብ ከኢትዮጵያ ጠላቶች የተገኘች እንደሆነች መገመቱ ቀላል ነው።እርሱም ቢሆን ተመትቷል።የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያን ለመበተን በግልጥ እየነገረ ከሚያዘምተው የራሱም ሆነ የኢትዮጵያ ጠላትን እየደገፉ ከመሄድ ከጁንታው ጋር አጭር ትግል አድርገው ቀሪዎን ጊዜ ብሩህ ዘመን ማድረግ በእዚህ የፅሞና ጊዜ ለትግራይ ሕዝብ የቀረበ ታሪካዊ ጥሪ እና ዕድል ነው።

==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...