ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, July 19, 2021

''ጥፊ ያላት ከተማ ነጋሪት ቢጎሰምባት አትሰማም''



  • ''በአማራ ላይ ሂሳብ እናወራርዳለን'' ለሚለው የተረፈ ህወሓት አመራሮችን አደገኛ የዘረኝነት ንግግር የተቃወመ የተጋሩ የፖለቲካም ሆነ ማኅበራዊ  ድርጅት ወይንም ስብስብ አለ?

 ''ጥፊ ያላት ከተማ ነጋሪት ብጎሰምባት አትሰማም'' እንዲሉ ህወሓት የሽብር ተግባሩን በመቀጠሉ  ከጥሞና ጊዜ በኃላ መንግስት የጠነከረ እርምጃ እንደሚወስድ ግልጥ እየሆነ መጥቷል።የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰኔ 21፣2013 ዓም  በተናጥል የተኩስ አቁም ውሳኔ የእርሻው ወቅትን ገበሬው እንዲጠቀምበት በማሰብ ትግራይን ለቆ ሲወጣ የህወሓት ሽብር ተግባር በትግራይ ከተሞች እና ገጠር ደጋፊ ያልሆኑ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር የነበሩ በሚል ቁጥሩ ከፍ ያለ ሕዝብ በመግደል ነበር የጀመረው።

ከግድያው ተከትሎ ተከታታይ የድንፋታ መግለጫዎች በህወሓት የሽብር ቡድን ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ መሰጠት ተጀመረ።በእዚሁ መግለጫ ላይ ጦርነቱን ወደ አማራ እና ኤርትራ እንደሚያስፋፉት መዛት ጀመረ።ቀደም ብሎየህወሓት የተረፉ አመራሮች በግልጥ በአማራ ሕዝብ ላይ ጦርነት አውጀዋል።ይህንንም ደጋግመው እየተቀባበሉ ''በአማራ ላይ ሂሳብ እናወራርዳለን'' በማለት ተናግረዋል።

 ህወሓት በአማራ ላይ ያላት ጥላቻ በ1967 ዓም ባወጣችው ማኔፈስቶ በግልጥ አስቀምጣለች።ይህ የናዚያዊ ትርክቷ አድጎ ዛሬ ሂሳብ አወራርዳለሁ ወደማለት አሳድጋዋለች።ይህ ንግግር በሀኪም ማስረጃ አይሰጣቸው እንጂ የአዕምሮ ህመም ላይ ባሉ የህወሓት ሽብርተኞች መነገሩ ባይገርምም።ይህንን ንግግር ያወገዘ የተጋሩ የፖለቲካም ሆነ ማኅበራዊ ድርጅት ወይንም ስብስብ አለመኖሩ ግን ሌላው ከባድ ጥያቄ ነው።ከአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ እብደታቸውን በልክ ማድረግ የማይችሉ ግለሰቦች መፈጠራቸው አይደንቅም።የሚደንቀው ግን ከእዛው ማኅበረሰብ ውስጥ በምንም ዓይነት መልክ የሚገኝ ስብስብ አለማውገዙ ግን ሌላ አደገኛ ጉዳይ ነው።

አሁን ያለንበትን ጊዜ በሚገባ ማወቅ ክምር መረዳት ያስፈልጋል።የተረፈው የህወሓት ስብስብም ሆነ አብረውት የቆሙት ጀሌዎቹ ጥያቄያቸው ግልጥ ነው።እኩልነት አንፈልግም።በቅኝ ገዢነት እንግዛችሁ ነው።ይህን ቅኝ ገዢነት ካልተቀበላችሁ ደግሞ ኢትዮጵያን እናፈርሳታለን የሚል ዛቻ ተደጋግሞ ተሰምቷል።አሁን ጉዳዩ ቁርጥ ነው።ይህ ቀላል ጉዳይ አይደለም።ኢትዮጵያን አጠፋለሁ ብሎ በአደባባይ የዛተ  እንዴት እንደሚጠፋ በቅርብ ዘመን ላልተመለከተ ታዳጊ ወጣት ታሪክ የሚሆን እርምጃ በተረፈ ህወሓት ላይ እንደሚወሰድ አትጠራጠሩ። 

ጥሞና ጊዜው ጥሩ አጋጣሚ ነበር።ወደ ሰላም መጥቶ ቆሜለታለሁ የሚሉትን ሕዝብ ማዳን አንዱ አማራጭ ነበር። ከእዚህ አልፎ ዛቻ፣ንፁሃንን መግደል እና መዝረፍ ግን እጅግ የመረረ ምላሽ ከኢትዮጵያ መከላከያ እንደሚኖር አለመጠበቅ የዋህነት ነው። የመከላከያ እታማዥር ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ዛሬ  በግልጥ ተናግረዋል።እኛ በትዕዛዝ ውጡ ስንባል እንወጣለን። መልሶ ግቡ ስንባል እንገባለን ብለዋል።መንግስት ለህሊናም ያልተሞከረ መንገድ እንዳለ በኃላ ይህ ቀርቶ ነበር ከመባል በሚል ከባድ ውሳኔ የሆነውን ለቆ መውጣት እና በተናጥል የተኩስ ማቆም አውጆ ሞክሮታል።ነገር ግን ይህ ለውጥ አላመጣም ይልቁንም ጦርነት የተጠሙት የተረፉት የህወሓት አመራሮች በመቀሌ እና ሌሎች ከተሞች ወጣቱን እያፈሱ የሦስት ቀኖች ስልጠና እየሰጡ ወደግንባር ወንድምህን ግደል ብለው እያዘመቱት ነው። መንግስት ዝቅ ብሎ ይህንን ያህል ሲያስተናግደው በትዕቢት የተወጠረው ተረፈ ህወሓት ከእንግዲህ ወዲህ የሚወሰድበት እርምጃ  የከፋ ነው።በእርምጃው ደግሞ የልማት አውታሮች አይፈርሱም ማለት አይቻልም።አሁንም ትምህርት ቤቶች ሳይቀሩ የእሳት ማንደጃ ማዕድቤት ያደረገ ያለው የሽብር ቡድን ለሚፈርሱ የልማት አውታሮች ቅንጣት ታህል አያስብም።

ባጠቃላይ  አሁን ሁኔታው  ''ጥፊ ያላት ከተማ ነጋሪት ቢጎሰምባት አትሰማም'' እየሆነ ነው። ይህ ሲባል አንዳንዶች ተራ ሟርት ይመስላቸዋል።ይህ ግን ፈፅሞ አይደለም።ምክንያቱም  ኢትዮጵያ ማበዳቸውን ለማረጋገጥ የሃኪም ማስረጃ ብቻ በቀራቸው ሽብርተኞች ሰላሟ አይታወክም። በእርግጥ አንድ እና ብቸኛው መስመር የትግራይ ማኅበረሰብ ህወሓትን በቃኝ ከህዝብ እያጋጨህ የወደፊት የመኖር ተስፋዬን አታጨልምምብኝ  ማለት ነው።ይህንን እንደማኅበረሰብ  በማድረግ ድምፁን ያሰማበት ሁኔታ ደግሞ እስካሁን አልተሰማም።በእርግጥ በግለሰቦች ደረጃ  ህወሓትን ሲታገሉ የኖሩ አሉ።ለእነርሱ ክብር ይገባቸዋል።ቢያንስ ከአማራ ጋር እንደህዝብ ለማጋጨት ሂሳብ እናወራርዳለን ንግግርን  አለመቃወም ግን የማስተዋል መጉደል ውጤት ነው።

==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...