ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, July 13, 2021

ጉዳያችን ምዕራፍ ሁለት ተመልሳለች - ብዙ ጊዜ እንደ ዋዛ ያያቸውን ዓማራ አሁን ቀስቅሰውታል።

 ጉዳያችን ምዕራፍ ሁለት ተመልሳለች።በእዚህ ምዕራፍ የተለያዩ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ።በእዚህኛው የጉዳያችን ገፅ ላይ ፅሁፉን ወደፈለጉት የዓለም ቋንቋ የሚቀይሩበት ማስፈንጠርያ ከእያንዳዱ ፅሁፍ አናት ላይ ያገኛሉ።በተጨማሪም ለጉዳያችን የሚፅፉበት ቦታም በቀኝ በኩል ተቀምጧል።

ወደ ወቅታዊው ጉዳይ ስንመለስ፣የምዕራቡ እና የምስራቁ ውጥረት በአዲስ መልክ እየመጣ ነው።ኢትዮጵያን ከግራ እና ከቀኝ ወጥሮ በውስጥ ጉዳይ ሁሉ ሳይቀር በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የተነሱትን ጎሰኞች አይዞአችሁ ብሎ ኢትዮጵያን ለመከፋፈል ብሎም አፍሪካን ለማዳከም እና የማትነጥፍ 'የጥገት ላም' ለማድረግ እሩጫው በርትቷል።

በእዚህ ሁሉ መሃል የምድያው ሚና ቀላል አይደለም።ሚድያው የማነስ እና የመተለቁ ቁምነገር ሳይሆን የሚመነጨው ሃሳብ ምን ያህል የተቀባዩን ወዳጅ ከሆነ የሞራል ስንቅ የሀገር ጠላት ከሆነ ደግሞ የተንኮል ድሩን የመበተን ኃይል ያለው አዲስ ሃሳብ ያመነጫል? ነው ጥያቄው።በአዲስ ሃሳብ ዓለም እንደገና ተቦክቶ ይሰራል።በማይቀየር ሃሳብ ደግሞ ዓለም ባለበት ይረግጣል።

ወደ እዚህ ሁለተኛ ምዕራፍ ጉዳያችን ስትገባ በኢትዮጵያ አንድ ግልጥ ሆኖ የመጣ ጉዳይ አለ። ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ጦርነት ከፍቷል።ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ረዳ ቃል በቃል ''ኢትዮጵያን እናፈርሳታለን'' ብሏል።ኢትዮጵያ ባንዳ እና ለሆዱ ያደረ አሰር ገሰስ ስታፈራ ህወሓት የመጀመርያዋ አይደለም።ከእዚህ በፊት በታሪክ ተነስተውባታል።ነገር ግን ሁሉንም አይቀጡ ቅጣት ቀጥታ አባራቸዋለች።የህወሓት ዕጣም ካለፉት የተለየ አይሆንም።

ይህንን ጽሁፍ ስፅፍ ህወሓት በሁለት ግንባሮች ማለትም በወልቃይት ሁመራ እና በራያ በኩል ቃል በቃል የተረፈ ህወሓት ሰዎች  ጀነራል ፃድቃን እና አቶ ጌታቸው እንዳሉት  ''ከአማራ ጋር ያላቸውን ሂሳብ ለማወራረድ'' በንፁሃን ላይ ግድያ ጀምረዋል።የአማራ ክልልም የክተት አዋጅ አውጇል። ብዙ ጊዜ እንደ ዋዛ ያያቸውን ዓማራ አሁን ቀስቅሰውታል።

የዛሬ 46 ዓመት የተዘፈነው ዘፈን (ከጉዳያችን ዩቱብ ድምፅ ክምችት) 





No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...