ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, August 7, 2021

ልዩ ዘገባ - ደብረፅዮን ቆስለዋል፣ በጄኔራል ፃድቃን ቡድን ተገደው ቁስላቸውን ደብቀው መግለጫ እንዲሰጡ ዛሬ ተደርገዋል።አሁን ያለው ነባራዊው የጁንታው ሁኔታ።የኢትዮጵያ ደህንነት የጠለፈው የጁንታው ስብሰባ ውሳኔ ሙሉ ይዘት። ኢትዮጵያ በጦርነት ውስጥም ሆና አስደሳች የልማት ስራዎች ዜናዎች እየወጡ ነው።(ሁሉንም በዘገባው ውስጥ ያገኛሉ)



===============================
ጉዳያችን ልዩ ዘገባ  /Gudayachn Special Report
===============================
ደብረፅዮን ቆስለዋል፣ፃድቃን ላይ የደብረፅዮን ቡድን ደጋፊ ሕዝብ ተነስቶባቸዋል

የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር ደብረፅዮን ክፉኛ መቁሰላቸው ከታማኝ ምንጮች ተሰምቷል።ይህንን ለማስተባበል ደብረ ጽዮንን በማስገደድ መግለጫ ሰጥተው ለማሰራጨት እየተሞከረ ነው። አሁን በትግራይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የስልክ እና ሌሎች መገናኛዎች አለመኖራቸው ነው እንጂ የህወሓት ጀሌ እና ሚሊሻ በደረሰበት የሰው እልቂትም ሆነ በምግብ እጥረት  የትግራይን ሕዝብ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አድቅቆታል። በመሆኑም በቀጣይ የሚዋጋበት አቅም ባለመኖሩ አሁን ጀሌውን ወደ አፋር እና አማራ ሲልኩት ዘርፈህ ብላ፣ ዘርፈህ ተመለስ እየተባለ እንደሆነ የታመኑ ምንጮች ይጠቁማሉ።

በሌላ በኩል በጄኔራል ፃድቃን ቡድን እና በደብረፅዮን መካከል የተነሳው ፀብ እጅግ ከመባባሱ የተነሳ ፃድቃን ከሃዲ ነው ትግራይን አስወደማት፣በድርድር ህዝቡ ሳያልቅ ንብረት ሳይጠፋ ትግራይን ማስቀጠል እንችል ነበር።በፃድቃን እና ጌታቸው ረዳ ድንፋታ ነው ይህን ያህል ጥፋት የደረሰው የሚለው የደብረ ፅዮን ቡድን ደጋፊ አሁን በፃድቃን ቡድን ላይ ተነስቶበታል።ይህ በእንዲህ እያለ ቀደም ባለው ጦርነት ቀኝ እጃቸውን የተመቱ እና ለመታከም የሞከሩ ቢሆንም በኃላ ከፃድቃን ቡድን በተተኮሰ ጥይት እንደገና መመታታቸው ነው የተነገረው።የደብረ ፅዮንን ሃሳብ የሚደግፉት ፈትለወርቅ (ሞንጆሪኖ) እና ዓለም ገብረዋህድ አብረዋቸው መሆናቸው ስሰማ ሆኖም ግን የፃድቃን ቡድን ከጦርነት ውጪ የሚታያቸው መንገድ የለም። 

ይህ በእንዲህ እያለ የደብረ ፅዮን ቡድን እና የፃድቃን ቡድን ለመገዳደል ሁሉ የሚፈላለጉበት ደረጃ እንደደረሱ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት።ይህንን ለማብረድ ደብረ ፅዮን እና ፃድቃን አብረው እንዲታዩ ለማሳየት ቢሞከርም በሃሳቡ ልዩነት ግን የፀና እምነት ያላቸው ካድሬዎች እና የጋንታ መሪዎች ሳይቀሩ በተለያዩ ቦታዎች ግጭት እየፈጠሩ ነው ያሉት።ይህን ሁኔታ የሚያውቁት ጥቂት የጁንታውን ዲያስፖራ ክንፍ አባላት ሲሆኑ ሌላው ከሹክሹክታ ባለፈ በግልጥ አያውቁም።

የኢትዮጵያ ወታደራዊ ድህንነት በሚስጥር የጁንታው ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አመራር እና የዲያስፖራው ክንፍ በዙም ያደረጉት ሙሉ ስብሰባ ጠልፎ አብሮ ተከታትሏል።

የኢትዮጵያ መከላከያ የጥሞና ጊዜ ለመስጠት እና ለትግራይ ገበሬ የሚያርስበት ጊዜ ለመስጠት ሰኔ 21 መቀሌን ለቆ እንደወጣ የተረፈው የህወሓት ጁንታ የፖለቲካ አመራር እና የወታደራዊ አመራር እንዲሁም የዲያስፖራ ክንፍ በጋር ስብሰባ ተቀምጠው ነበር።ስብሰባውን የኢትዮጵያ ወታደራዊ ደህንነት ክፍል ጠልፎ ገብቶ አብሮ ሙሉውን ተከታትሏል።በእዚህ መሰረት የስብሰባው ውጤት የሚከተሉት እንደነበሩ የፍትህ መፅሄት ዛሬ በሶስተኛ ዓመት፣ ቁጥር 144 ነሐሴ 2013 ዕትም እንደሚከተለው ዘግባለች።

ህወሀት መከላከያ መቀሌን ጥሎ ከወጣ በኋላና ወደ ከተማዋ እንደገባ የጦር መሪዎቹና ፖለቲከኞቹ ለ6ቀናት የzoom ስብሰባ (ውጭ ያሉት ጋርም) አድርገው ነበር። የኢትዮጵያ መከላከያ ሙሉ መረጃውን አብሮ (በሚስጥር) ተከታትሏል።
በ6ቀኑ ቆይታቸው ከተስማሙባቸው ጉዳዮች ውስጥ
1. ትግራይን ለመገንጠል ኢትዮጵያ ውስጥ 3አብዮቶች የግድ ያስፈልጋሉ፣
2. የኦሮሞ ብሔር ምንም የጋራ አገራዊ ማንነት ስለሌላቸው የአአን ጉዳይ "ፊንፊኔ ኬኛ"ብለው እንዲነሱ ማድረግ፣ ለዚህም ተጋሩ የሚከፈለውን ዋጋ ከፍለው የኦነግን ሃይል መደገፍና ፊንፊኔ ኬኛን ማጦዝ አለባቸው፣
3. በአፋርና ሶማሌ ግጭት መፍጠርና አፍር ላይ የተወሰኑ መሬቶችን በኛ በኩል በመውረር አፋር existential threat እንዲሠማው በማድረግ ጅቡቲ ካሉ አፋሮች ጋር እንዲተባበርና ግጭቱ እንዲሠፋ ማድረግ፣
እኛ በምንወጋው ጊዜም ስነልቦናዊ ውድቀት ደርሶበት በኢትዮጵያ ተስፋ እንዲቆርጥ ማድረግ፣
4. የአፋርና ሶማሌ ጦርነት ሰፍቶ የታላቋ ሶማሊያን ፕሮጀክት ማስጀመርና የጂቡቲ አፋሮችና የሶማሊያ ሶማሌዎች ኢትዮጵያ ውስጥ የproxy (የውክልና ጦርነት) ጦርነት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲከሰት ማድረግ፣
5. ባድመ በግድ እንደተወሰደች አድርጎ በኤርትራ ጦርነት መክፈትና የኤርትራን ተጋሩ ማነሳሳት፣ ለዚህም የኤርትራ ዲያስፖራን መጠቀም፣
6. ኢሳያስ በሚሞትበት ጊዜ የትግራይን ብሔርተኝነት በማቀንቀን ለኤርትራ ትግሬዎች የመጨረሻ እድል መስጠት፣
7. ኤርትራ ውስጥ ያሉ አፋሮች ኢትዮጵያና ጅቡቲ ካሉት ጋር ተባብረው አገር እንዲመሠርቱ ማድረግና መደገፍ፣
8. በኢትዮጵያ በሶማሊያና በጅቡቲ ያሉ ሶማሌዎች ወደ ዋናው አገር ሶማሊያ እንዲቀላቀሉ መስራት፣
9. ባጠቃላይ የታላቋን ትግራይ ለመመስረት ያሁኖቹ ኢትዮጵያ ፣ ጅቡቲ፣ኤርትራና ሶማሊያ የግድ ቅርጻቸውን መቀየር አለባቸው፣
10. ለትግራይ አገር መሆን 4አገሮች የግድ ያስፈልጉናል፣ ግብጽ፣ አሜሪካ ፣ እንግሊዝና እስራኤል፣
👉 ግብጽ ትግራይን የምትደግፍ ከሆነ ግድቡን በትግራይ ወታደሮች እንዲፈርስ እንደምናደርግ ማሳወቅ፣
👉ለእስራኤል እኛም የነሱን መንገድ እንደምንከተል መናገርና ሁሌም ከነሡ ጋር እንደምንሆን ማሣመን፣
👉ከእንግሊዝና አሜሪካ ጋር በሚደረገው ውይይት የምትመሠረተው ትግራይ የኒዮ-ሊብራሊዝም ተከታይ እንደምትሆንና ትግራይ ውስጥ ያሉ ማዕድናት በሙሉ ለUSና USA ባለሀብቶችና ድርጅቶች እንደምንሰጥ ቃል መግባት፣
👉USናUK የሚያቀርቧቸውንም ማናቸውንም ነገሮች ያለቅድመ ሁኔታ መቀበል፣
11. ለምዕራቡ አለም(USAና UKን ጨምሮ) በኤርትራ እየተስፋፋ ያለውን እስልምና እንደሚያሠጋንና ይሄንን ለማጥፋትም አብረን ከነሱ ጋ እንደምንሰራ ማሳመን" የሚሉ ናቸው።

አሁን ያለው ነባራዊው የጁንታው ሁኔታ 

አሁን ያለው የህወሓት ጁንታው እና ትግራይ ውስጥ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ፈፅሞ የተዳከመበት እንደሆነ ነው የውጭ የሎጀስቲክ ጥናት ባለሙያዎችም ሆኑ ውስጣዊ የጁንታውን ሁኔታ የሚያውቁ የውጭ ወኪሎቻቸው የሚናገሩት። ለእዚህ ደግሞ የሚሰጡት በቂ ምክንያቶች አሉ። እነርሱም -
  • ከጥቅምት 24ቱ በኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ ካደረሱት ጥቃት ጀምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ እና የኤርትራ ሰራዊት በጥምር በወሰዱት እርምጃ ዋናው የልዩ ኃይላቸው አስክዋል እና ንዑሱ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።
  • በቀጣይ ወደ አማራ እና አፋር ለመግባት ባደረጉት ጥረት በምዕራብ ግንባር ብቻ 12 ጊዜ በብዙ የሰው ኃይል ጥቃት ባለፉት ሶስት ሳምንታት ብቻ ቢሞክሩም ቀድሞ ቆልፍ ቦታዎች የያዘው የአማራ ልዩ ኃይል እና የመከላከያ ሰራዊት ለወሬ ነጋሪ አላስቀረም።በሰሜን ወሎ እና አፋር በአንድ ቀን እስከ ሰላሳ ሺህ ሚሊሻ ነው ያለቀው።ወደ አፋር የተደረገው ሙከራ ላይ በተለይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሄሊኮፍተሮች የጁንታው ኃይል በተዘናጋበት ሰዓት ከቀትር በኃላ 11 ሰዓት ገደማ እስከ ምሽት 2 ሰዓት ድረስ በፓውዛ በተደረገ ጥቃት የተረፈ የህወሓት ጀሌ የለም።
  • ከእዚህ በኃላ የተበታተነው የህወሓት ጀሌ የተሰጠው መመርያ በቻለው እየተገናኘ በወልድያ በኩል አድርጎ ወደ ደቡብ ጎንደር በጋይንት በኩል አድርጎ እንዲገባ ያስገድዱት ገቡ።ይህንን የሚያዙት የተቆራረጠ ጀሌ ከኃላው ብዙ ደጋፊ ኃይል እንደሚላክ በውሸት እየተነገረው ነው። ስለሆነም የተበታተነው ጀሌ አንዴ አላማጣ፣አንዴ ላሊበላ ገባ ወጣ የሚል ጀሌ መታየት ጀመረ።
  • በትግራይ ውስጥ ያለው የነዳጅ እና ምግብ ነክ ያልሆነ ያዋጋል ብሎ ጁንታው ያሰበው እስከ ነሐሴ መጀመርያ የሁመራ መንገድን ስለምናስከፍት ከነሐሴ በኃላ  ሎጀስቲክ ከሱዳን ይመጣል በሚል እሳቤ ነበር።ሆኖም ግን ይህ ባለመሆኑ አሁን ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብቷል።
  • ላለፉት ስምንት ወራት ለማረስ ጊዜ ያላገኘው ገበሬ (ቀድሞ ከነበረው 2 ነጥብ 5 ሚልዮን ሕዝብ በላይ እርዳታ ላይ ነበር) አሁንም በክረምት ባለማረሱ ምክንያት ለዘር የቀረውን ሳይቀር በመጨረሱ አሁን ረሃብ ሕዝብ ውስጥ ገብቶ ተጨማሪ ወታደር የማግኘት ሕልም ከሳምንታት በኃላ  የሚታይ አይሆንም።
  • በቀጣይ ኤርትራን እንዲወሩ ከውጭ መንግሥታት በተሰጣቸው መመርያ መሰረት አስመራን ለመውጋት ማቀዳቸው ግልጥ ሆኗል።በመሆኑም ኤርትራ ተመልሳ እንደምትመጣ፣የኢትዮጵያ መከላከያም የተኩስ አቁሙ ሲያበቃ ተመልሶ እንደሚመጣ ሕዝቡም ጁንታውም ያውቀዋል።ስለሆነም የውጭ መንግስታት በቶሎ ወደ ድርድር እንዲመጡ እንዲገፉላቸው እየጠየቁ ነው።
  • ነባራዊው ሁኔታ ሲጠቃለል ጁንታው ከውጫዊው ኃይል ባላነሰ የውስጣዊው ቅራኔ እና የችጋር ቆፈን በከፍተኛ ደረጃ ወጥሮ ይዞታል።
የህወሓት ጁንታ ወረራ ውጤቱ ምን ይሆናል?

ባጭሩ አሁን ያለው ሁኔታ እንደ 1983 ዓም የኢትዮጵያ ሕዝብ ተሰላችቶ የሚተወው ጦርነት የሚመስላቸው የጁንታው ደጋፊዎች ብዙ ናቸው።አሁን ሁኔታው እንደዛ አይደለም።ጊዜ በፈጀ ቁጥር የእነፃድቃን የትዕቢት መንገድ ትግራይን ሙሉ በሙሉ ያወድማታል።የመሰረተ ልማት ጉዳይ አይታሰብም።ሕዝብ ግን በከፍተኛ መንገድ መሰደዱ ይቀጥላል።አሁንም ነጭ ጨርቅ እያውለበለቡ ወደ ኤርትራ እና የቀረው የኢትዮጵያ ክፍል እየተሰደደ ያለው ሕዝብ ቁጥሩ እየጨመረ ነው።በቀጣይ የህወሓት ጁንታ የወረራ ውጤት የትግራይ ክልል በክልልነት ላትቀጥል ትችላለች። ከሰሞኑ የተቆራረጠው የጁንታው ጀሌ አንዳንድ የአማራ፣የአፋር እና የኤርትራ ቦታዎች ዘረፋ ይጨምር ይሆናል።በሳምንታት ውስጥ ግን ከማሰልጠኛ የሚወጣው ብቻ ሳይሆን አሁን እየቆረጠ የተነሳው ሕዝብ ሙሉ በሙሉ እንደሚያፀዳው ምንም ጥርጥር የለውም።የእዚህ ጊዜ የፃድቃን ትዕቢት ምን ያህል እንዳልሰራ ቆይቶ ከደነዘዙበት የሚነቁት እራስ በራስ መመታታት መጀመሩ አይቀርም።

የጁንታው ወረራ ለትግራይ የሚል አጀንዳ የለውም።ዋና ዓላማው ''ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እስከ ሲኦል እንወርዳለን'' በማለት በአደባባይ እንደተናገሩት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እና የባዕዳንን ተልኮ ማስፈፀም ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብም የሚዋጋው ለኢትዮጵያ ሕልውና ነው።ለኢትዮጵያ ህልውና ደግሞ ከመቶ ሚልዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ ሕልውናውን የማስከበር ግዴታ ስለሆነ ውጤቱ የሚሆነው በጁንታው መቃብር ላይ ኢትዮጵያን በሁለት እግሮቿ ማቆም ነው።

ኢትዮጵያን ላለፉት 50 ዓመታት ከባእዳን ጋር ሆኖ ሕዝብ ወደ ድህነት የመራው የህወሓት ሽብርተኛ ቡድን ያደረሰው ጥፋት ቀላል የሚባል አይደለም።በኮ/ል መንግስቱ ጊዜ አንድ ወቅት እንደጠቀሱት የወያኔ ጦርነት ኢትዮጵያን ድሃ እንዳደረጋት ሲገልጡ ጦርነቱ ባይኖር ኖሮ ኢትዮጵያ ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ፣ከምዕራብ እስከ ምስራቅ ድረስ የባቡር ሐዲድ መዘርጋት ትችል እንደነበር ገልጠዋል። ይህ ሳይበቃቸው ላለፉት 27 ዓመታት ያህል በቤተ መንግስት ውስጥ ሆነው ኢትዮጵያን በእርዳታ እና በብድር ያገንገችውን ሁሉ ሲዘርፉ እንደኖሩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ጥናት ዘገባዎች ሳይቀሩ ከ11 ቢልዮን ዶላር በላይ በሕገ ወጥ መንገድ እንዳወጡ ተጠቅሷል።ዛሬም ጠግበውባት ''ኢትዮጵያን ለማፍረስ እስከ ሲኦል ድረስ መሄድ ካለብን እንሄዳለን'' ብለው በኢትዮጵያ ላይ ካራ ስለውባታል። አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ካለፈው ተምሯል።እየተዋጋ ሃገሩን ያለማል።

ኢትዮጵያ በጦርነት ውስጥም ሆና አስደሳች የልማት ስራዎች ዜናዎች እየወጡ ነው።

ሰሞኑን ኢትዮጵያ በጦርነት ላይም ሆና የልማት መልካም ዜናዎች ተሰምትወባታል። ከእዚህ በታች በአጭር በአጭሩ ለማቅረብ እሞክራለሁ።የእዚህ ዓይነቱ ዜና አስፈላጊ የሚሆነው ሁሉም ስለማይዘምት እና በመሃል የምጣኔ ሃብቱን እና የልማት ሥራውም አንዱ ግንባር በመሆኑ ከግንዛቤ ውስጥ ለማስገባት ነው።ከእዚህ በታች ያሉት የልማት ስራዎች ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ በኢትዮጵያ የተዘገቡ ናቸው።

  • በአዲስ አበባ መብራት መቆራረጥ ለማስቀረት የመብትራት ኃይል አመርቂ ሥራ ሰርቷል 
ከ600 ሚልዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለመስመሮች መቆራረጥ ምክንያት የሆኑ 625 ኪሎ ሜትር የምረዝሙ  አሮጌ መስመሮችን በአዲስ የመቀየር ሥራ  መፈፀሙ የተነገረ በእዚህ ሳምንት ነው።በቀጥያ የ400 ኪሎ ሜትር ገመዶች መቀየር ይቀጥላል።ይህ በከተማዋ የመብራት መቆራረጥ እንደሚያቃልል ተነግሯል።
  • በኢትዮጵያ የመኪና ላይ እና የእግር ጉዞ ጂ ፒ ኤስ አገልግሎት በኢትዮጵያውያን ኩባንያዎች ሥራ ላይ ውሏል።
በኢትዮጵያ ያሉ ከተሞች እና ገጠር ለቅሞ የሚያሳይ እና በድምፅም በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ የሚመራ ጂፒኤስ አዲስ አበባ ላይ የተመረቀው በእዚህ ሳምንት ነበር።ጂ ፒ ኤሱ ከኢትዮጵያ ድንበሮች ዙርያ ሁሉ የሚያመላክት መሆኑን እና የቤት ቁጥር እና መንገድ ቁጥር የሌላቸው ቦታዎች ከመብዛታቸው አንፃር ጂፒኤሱ ሁሉም ቦታዎች አመላካች ገፅታን የሚያሳይ መሆኑን እና እየተሻሻለ እንደሚሄድ ተነግሯል።በሌላ በኩል ጂ ፒ ኤሱ አንዴ ሞባይል ላይ ዳውንድ ሎድ ከተደረገ በኃላ ካለ ኢንተርኔት ሊጠቀሙበት እንዲችሉ ተደርጎ መሰራቱ ነው የተነገረው።
  • የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ተቆጣጣሪ መስርያቤት ተጠሪነቱ ለፓርላማ እንዲሆን ተወሰነ 
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ጥራት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በከፍተኛ ትምህርት ኮሚሽን ስር ሆኖ በተለይ የመንግስት ዩንቨርስቲዎች ጥራት መቆጣጠር ላይ ስሽኮረመም የነበረው ኤጀንሲ ተጠሪነቱ ለፓርላማ እንዲሆን እና ሁሉንም የግል እና የመንግስት ዩንቨርስቲዎች እኩል እንዲቆጣጠር እና ሪፖርት ለፓርላማ ከመስከረም ጀምሮ እንዲያቀርብ ተወስኖ በራሱ እንዲደራጅ መወሰኑ ለማወቅ ተችሏል።
  • የትምህርት ሚኒስቴር ለአንደኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የመማርያ መፃህፍት አስረጂ ባለ ቪድዮ ድረ ገፅ አስመረቀ 
ድረ ገፁ በያንዳንዱ ክፍል ያሉ መፃህፍት በቪድዮ የሚሰጥ ገለጣ ተማሪዎች የሚማሩበት ድረ ገጽ ለተማሪዎች በጣም የሚያግዝ እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል።ተማሪዎች በትምህርት ቤታቸው መግቢያ በቀላሉ ገብተው የሚያጠኑበት መንገድ አሁን ተመቻችቷል።
  •   የአድዋ ዜሮ ፕሮጀክት መስከረም ላይ እንዲመረቅ ጥድፍያ ላይ ነው።67% ተፈፅሟል።
ኢትዮጵያ አድዋ በዓል በየዓመቱ ይከበር እንጂ ሁነኛ የሆነ የመታሰብያ ቦታም ሆነ ከውጭ ለሚመጣ ጎብኝም የምናሳየው ደረጃውን የጠበቀ ሙዜም የለም።በቅርብ መንግስት በአዲስ አበባ መሃል አራዳ አድዋ ዜሮ ፕሮጀክት በውስጡ ሙዜም፣መፃህፍት ቤት እና ሌሎች ድንቅ የአገልግሎት ክፍሎች እየተሰሩ መሆኑ ተነግሯል።ፕሮጀክቱ በመጪው መስከረም ለመጨረስ ጥድፍያ ቢኖርም ምናልባት በወራት ሊቀጥል ይችላል የሚል ግምት አለ።አሁን ግን 67% ተፈፅሟል።
  • 3ነጥብ 6 ቢልዮን ዶላር ገቢ 
ኢትዮጵያ ከእዚህ በፊት አግኝታ ከምታውቀው በላይ ከውጭ ንግድ ማግኘቷ የተሰማው በእዚህ ሳምንት ነው።በእዚህ መሰረት በያዝነው ዓመት 3 ነጥብ 6 ቢልዮን ዶላር ማግኘቷ ለማወቅ ተችሏል።
  • 90 ሚልዮን ዶላር 
ኢትዮጵያ ከኤሌክትሪክ ሽያጭ 90 ሚልዮን ዶላር ማግኘቷ የተጠቀሰውም በእዚህ ሳምንት ነው።ይህ ገቢ ለጅቡቲ እና ሱዳን ብቻ ከተሸጠው የተገኘ ገቢ ሲሆን የሱዳን መንግስት አሁን የሚያገኘው 200 ሜጋ ዋት ሲሆን በቅርቡ ኢትዮጵያ 1000 ሜጋ ዋት እንድትሸጥላት  እንደጠየቀች በእዚህ ሳምንት ተነግሯል።መንግስት አሁን ካለው የሱዳን እና የኢትዮጵያ ግንኙነት አንፃር የሚያየው እንደሚሆን የብዙዎች ግምት ነው።
  • የአዲስ አበባ ማዘጋጃ እድሳት (አንድኛው ክንፍ) መስከረም መጨረሻ ይመረቃል።
የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ከተሰራ ጀምሮ እንደ አሁኑ ሙሉ እድሳት ተደርጎለት አይታወቅም።አሁን ታሪካዊ ይዘቱን ሳይለቅ ነገር ግን እጅግ ዘመናዊ በሆነ መልኩ እድሳቱ ተጀምሯል።እድሳቱ በተራ በሁለቱ ክንፍ እየተሰራ ሲሆን የአንደኛው ክንፍ በ62 ሚልዮን ብር እድሳት ከመስከረም መጨረሻ በፊት ይመረቃል። አሁን የሚመረቀው የልጆች መጫወቻ እና 150 መኪናዎች ማቆምያ ሁሉ ያካተተ እንደሆነ ለማወቅ ይቻላል።
===================///================= 

================
 ማስታወቂያ / Advertisment
====================
የጓደኞችዎን ወይም የቤተሰብዎን የሞባይል አየር ጊዜ ለማሳደግ ከዚህ በታች ያለውን አገናኝ ጠቅ ያድርጉ።
በአንድ ሁኔታ ውስጥ በሚመገብ ቤት የሚኖር የቤተሰብ እውነተኛ የወዳጅነት ስልክዎ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን የሚመለከት ከስር ሊ መረጃን ይጫኑ - 
Open the link to mobile top up at home







No comments: