ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, August 26, 2021

ሰበር ዜና - የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ሩስያ፣ሕንድ እና ቻይና ከኢትዮጵያ ጎን መቆማቸውን አረጋገጡ።ቻይና ጉዳዩ የፀጥታው ምክር ቤት በመወያየት መፍትሄ አይመጣም ስትል ሩስያ ዕርዳታን ፖለቲካዊ ማድረግ እና መርዛማ ሚድያዎች የችግሩ ምክንያቶች ናቸው ብላለች። (የሩስያ, የቻይና ሙሉ ንግግር ነጥቦች በአማርኛ ይንብቡ)

ሩስያ አሜሪካንን በትግራይ ጉዳይ በገደምዳሜ ወረፈቻት ''ኢትዮጵያ የሚደረገውን የሰብዓዊ እርዳታ ከፖለቲካዊ ጉዳይ ውስጥ መውጣት እንዳለበት የሩስያ እምነት ነው። በእዚህ በኩል መርዛማ ሚድያዎች በመጠኑ ዕድል ያገኙ ይመስላል።'' በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የሩስያ አምባሳደር ነሐሴ 20፣2013 ዓም 

''We are convinced to address the situation in Northern Ethiopia (Tigray), it is necessary to depoliticize the North Ethiopian Humanitarian activities. In this regard the toxic media atmosphere seems gets a little chance.'' Russia Ambassador to UN Security Council, August 26,2021

 ''ይህንን ጉዳይ (የትግራይን ጉዳይ) በፀጥታው ምክር ቤት በመወያየት መፍትሄ አያመጣም።ከእዚህ ይልቅ እያንዳንዱ የፀጥታው ምክር ቤት አባል ችግሩን ለመፍታት የራሱን ጥረት ሲያደርግ ነው።'' በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የቻይና  አምባሳደር ነሐሴ 20፣2013 ዓም 

''No one can solve the problem (Tigray conflict) by discussing in Security Counsel but the solution comes when each member of the security council made its contribution to solve the problem.'' Chaina Ambassador at UN Security Council August 26,2021

''የትግራይ ክልል ችግር መፍትሄ ኢትዮጵያዊ መር መሆን አለበት'' - በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የህንድ አምባሳደር ነሐሴ 20፣2013 ዓም 
''The solution to the Tigray region must be Ethiopian led''.- Indian Ambassador at UN Security Council August 26,2021

====================
ጉዳያችን / Gudayachn
====================

''የአፍሪካ ሰላም እና ፀጥታ'' በሚል ርዕስ ስር የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያ ትግራይ ክፍለሀገር የፀጥታ ጉዳይ ላይ መክሯል።ስብሰባው እንዲጠራ የጠየቁት ስቶንያ፣ፈረንሳይ፣ኖርዌይ፣አየርላንድ፣እንግሊዝ እና አሜሪካ ናቸው።

ስብሰባው የፀጥታው ምክር አባላት አምባሳደሮች የየሀገሮቻቸውን ሃሳቦች ያዳመጠ ሲሆን በመጨረሻም የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴን ንግግር አድምጧል።

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ በቅድምያ መነሻ ንግግር ካደረጉ በኃላ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት በየተራ ንግግራቸውን አቀረቡ።ካቀረቡት ውስጥ ከሞላ ጎደል ገዢ የሆኑ ሃሳቦች እንደሚከተለው ለአማርኛ አንባቢ ኅብረተሰባችን ለማቅረብ እሞክራለሁ።

አሜሪካ 

ከባለፈው ጊዜ ወዲህ ብዙ ለውጥ የለም በማለት የጀመሩት የአሜሪካው ተወካይ በመቀጠል የሚከተለውን ብለዋል።
- ለድርድር የቀረቡ ሃሳቦች መንግስት አልተቀበለም።ህወሓትም ጦሩን ወደ አጎራባች የአማራ እና የአፋር ክልል አስገብቷል።
- በእነዚህ ክልሎች እየተካሄደ ያለው የወያኔ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እያፈናቀለ ነው እና ይህ  በቶሎ ማቆም አለበት።
- ዛሬ በእነዚህ ሶስት ስጋቶች ላይ ማተኮር እፈልጋለሁ - አስከፊው የሰብአዊ ሁኔታ ፣ ወደ ዘላቂ የተኩስ አቁም አስቸኳይ ድርድር አስፈላጊነት እና የኤርትራ ኃይሎች መውጣት።
- ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል አንድ የሰብዓዊ ሠራተኛ በሕወሓት ኃይሎች የተገደለ ሲሆን ሰብዓዊ ተሟጋቾች ዕቃዎቹ ወደ ትግራይ እየተወሰዱ የሕወሓት መንግሥታዊ ያልሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ መሥሪያ ቤቶችን እና መጋዘኖችን ሲዘረፉ ተመልክተዋል። ይህ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም።
- ቀውሱን በማባባስ ደረጃ ኤርትራ ተጠያቂ ነች።
- አሜሪካ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመደገፍ ፍቃደኛ ነች።
እዚህ ላይ የአሜሪካው ወኪል ማንሳት ያልፈለጉት የኢትዮጵያ መንግስት የተናጥል ተኩስ አቁምን እንዳላየ አልፈዋል።በአማራ እና አፋር ላይ ህወሓት ያደረገችውን ወረራ በአረፍተ ነገር ጠቀስ አድርገው አለፉ እንጂ በሚገባ አላወገዙም።ይህ አሳፋሪ ነው።



ሩስያ 

- ሩስያ የአካባቢውን ሁኔታ በጥንቃቄ እየተከታተለች ነው።
- ሩስያ በሰኔ በተናጥል ተኩስ አቁም የኢትዮጵያ መንግስት ያወጀው በህወሓት እንደተጣሰ ታምናለች።
- ህወሓት ከእዝያ በኃላም ጦርነቱን ቀጠለ/
- የምግብ እርዳታው እንዲደናቀፍ ያደረጉ የህወሓት ተዋጊዎች ናቸው በጅቡቲ እና በአዲስ አበባ መሃል ያለውን መንገድ ለመቁረጥ ሞክረው ነበር።
- በእዚህ ወረራቸው የስደተኞች ቁጥር እና የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እንዲጨርም አድርገዋል።
- የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ ቀውሱን ለመቀነስ የዓለም ምግብ ፕሮግራም እርዳታ መኪናዎች ወደ ትግራይ እንዲሄዱ ማድረጉ ይታወቃል።
- ኢትዮጵያ የሚደረገውን የሰብዓዊ እርዳታ ከፖለቲካዊ ጉዳይ ውስጥ መውጣት እንዳለበት የሩስያ እምነት ነው። በእዚህ በኩል መርዛማ ሚድያዎች በመጠኑ ዕድል ያገኙ ይመስላል።
''We are convinced to address the situation in Northern Ethiopia (Tigray), it is necessary to depoliticize the North Ethiopian Humanitarian activities. In this regard the toxic media atmosphere seems gets a little chance.'' Russia Ambassador to UN Security Council, August 26,2021

- የሰብዓዊ ዕርዳታ ከትግራይ ሌላ ለሌሎቹ ለምሳሌ አምሐራ፣ኦሮምያ እና ሱማሌም ያስፈልጋቸዋል 
- እነኝህ አካባቢዎች በድርቅ፣በጎርፍ እና በአንበጣም ጭምር የተጎዱ ናቸው።
- ይህ ደግሞ በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ እርዳታ መርህም የሚያዘው ነው።
- የፖለቲካ ንግግር ከተባለም በራሳቸው በኢትዮጵያውያን አነሳሽነት እና መሪነት እንጂ በውጭ ኃይል ግፊት ሊሆን አይገባም።
- የሰኔው የኢትዮጵያ ምርጫ ያሳየን ነገር የተመረጠው የኢትዮጵያ ፈድራል መንግስት የኢትዮጵያን አንድነት የመጠበቅ አቅም እንዳለው ነው።
- እኛ ኢትዮጵያውያን አሁን ያለውን ችግር እንደሚፈቱት እና ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ሀገሪቱን እንደሚመልሱ ሙሉ እምነት አለን።
- የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እና የአፍሪካ ህብረት የሚጠበቅባቸው የኢትዮጵያ መንግስትን መልካም ጅምሮች በቀላሉ መደገፍ ብቻ ነው።
- ከእዚህ በተለየ በተናጥል በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የሚደረግ የተናጥል ዕቀባ ወደ የባሰ አለመግባባት የሚመራ ነው።
- ከእዚህ በተጨማሪ ማንም ይህንን ጉዳይ (የትግራይን ጉዳይ) በፀጥታው ምክር ቤት በመወያየት መፍትሄ አያመጣም።ከእዚህ ይልቅ እያንዳንዱ የፀጥታው ምክር ቤት አባል ችግሩን ለመፍታት የራሱን ጥረት ሲያደርግ ነው።
No one can solve the problem (Tigray conflict) by discussing in Security Counsel but the solution comes when each member of the security council made its contribution to solve the problem.
- የሚያስፈልገው የሁለትዮሽ ግንኙነት ከኢትዮጵያ ጋር በመፍጠር መፍታት ነው።
አመሰግናለሁ!




ቻይና 

- የሰብአዊ እርዳታ ለአማራ እና አፋር ክልልም የሚያስፈልግበት ሁኔታ አለ።
- ቻይና ለትግራይ ክልልም እርዳታ ልካለች።
- ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሲሰሩ የተባበሩት መንግሥታት መመርያ እና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሊያከብሩ ይገባል።
- ቻይና የኢትዮጵያ መንግስት እና ሕዝብ የሀገራቸውን አንድነት፣መረጋጋት እና ሰላም ለመደገፍ የሚያደርጉትን ጥረት ሁሉ ትደግፋለች።
- የዓለም አቀፍ ማኅበረስብም ይህንኑ ሊያደርግ ይገባል።
- ቻይና በሰብዓዊ መብት ሰበብ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረግ ማናቸውንም ጣልቃ ገብነት አጥብቃ ታወግዛለች።
- እኛ የአፍሪካ ጉዳይ በአፍሪካውያን ይፈታ የሚለውን መርህ እንደግፋለን።
- ቻይና የኢትዮጵያ መንግስት አሁን ያለውን ችግር ለመፍታት አቅምም ሆነ ጥበብ እንዳለው እና የኢትዮጵያ ሕዝብም አሁን የገጠመውን ፈተና በአሸናፊነት እንደሚወጣ ታምናለች። 
- ቻይና ለኢትዮጵያ ሰላም እና አንድነት ከሚሰራ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጎን ሁል ጊዜም ትቆማለች።

ሜክሲኮ 

- ስቶንያ፣ፈረንሳይ፣ኖርዌይ፣አየርላንድ፣እንግሊዝ እና አሜሪካ ይህንን ስብሰባ በመጥራታቸው አመስግናለች።
- ኢትዮጵያ የሜክሲኮ ታሪካዊ ግንኙነት ያላት ሀገር ነች።
- ኢትዮጵያ ለአፍሪካም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ቁልፍ ሀገር ነች።
- በተባበሩት መንግሥታት እና በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽኖች በጥምረት እየተደረገ ያለውን የሰብዓዊ ጥሰት ምርመራ ውጤት ሜክሲኮ ትጠብቃለች።
- የባንክ እና የመገናኛ መቆም የእርዳታ ሂደቱን ያደናቅፋል።
- ሁሉም ወገኖች የተባበሩት መንግስታትን እና የዓለም አቀፍ ሕግ ማክበር አለባቸው ብላ ሜክሲኮ ታምናለች።
- የቀድሞው የናይጀርያ ፕሬዝዳንት ኦቦሳንጆ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ተወካይ ሆነው በአፍሪካ ህብረት መሾማቸውን እንደግፋለን።




ሕንድ 

- አሁን ግጭቱ እየተስፋፋ ያለው በህወሓት ነው።ወደ አጎራባች ክልሎች አማራ እና አፋር በመግባቱ 
- በእዚህ ወረራውም ሕፃናት፣ልጆች እና አዛውንቶች ተገድለዋል።
- ህወሓት የሕፃናት ወታደሮች እየተተቀመችም ነው።ይህም ትልቅ የሰብዓዊ ጥሰት ነው።
- የኢትዮጵያ መንግስት በሰኔ ወር ላይ የወሰደው የተኩስ አቁም ትልቅ እርምጃ ነበር።
- ሆኖም ግን በህወሓት በኩል በተፈጠረው ወረራ የአንድ ወገን ጥረት ውጤታማ አልሆነም።
- የሰብዓዊ ዕርዳታው ቁጥር ጥሩ እንደሆነ እና እየደረሰ እንደሆነ የተባበሩት መንግሥታት ኦቻ ስታትስቲክስ ያሳያል።
- በኢትዮጵያ መንግስት እና በእርዳታ ድርጅቶች መሃል ያለው ግንኙነትም ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በእጅጉ ተሻሽሏል።
- ለእዚህም ማሳያው በሰመራ የተመሰረተው የኢትዮጵያ መንግስት የዓለም ምግብ ድርጅት እና የእርዳታ ድርጅቶች በጥምረት የመሰረቱት ጣብያ በአፋር በኩል ምግብ ለማድረስ ጥሩ ድልድይ ፈጥሯል።
- ስለሆነም ኢትዮጵያ አሁን ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ሁሉንም ዓይነት ድጋፍ ያስፈልጋታል።
- የትግራይ ክልል ችግር መፍትሄ ኢትዮጵያዊ መር መሆን አለበት (The solution to the Tigray region must be Ethiopian led.)

ከእዚህ በተጨማሪ የኬንያ እና የእንግሊዝ አምባሳደሮች የተናገሩ ሲሆን በተባበሩት መንግሥታት  የኢትዮጵያ ባለሙሉ አምባሳደር ታዬ ሕፅቀሥላሴ  ንግግር አድርገዋል።አምባሳደር ታዬ ሕፅቀሥላሴ በንግግራቸው ኢትዮጵያ የሕግ ማስከበር ስርዓቱን ጨምሮ ሉአላዊት ሀገር በመሆኗ ሙሉ መብቷ መሆኑን እና ከእዚህ ውጭ የሚደረግ የውጭ ጣልቃ ገብነትን ኢትዮጵያን ፈፅሞ እንደማይቀበሉ በለሰለሰ የዲፕሎማሲ ቃል ተናግረዋል። 

==================///================

==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 







No comments: