ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, August 9, 2021

የአሸባሪው ህወሓት ስውር የሽብር ወሬዎች የሚመጡበት ሰባት መንገዶች።የሽብር መንዣ ስምንቱ የመጀመርያ ዓረፍተ ነገሮች።


የአሸባሪው ህወሓት ስውር የሽብር ወሬዎች የሚመጡበት ሰባት መንገዶች።

1) ከቤተሰብዎ እራሱ ወይንም እራሷ ባላወቁት መንገድ የውሸት ዜናዎች ይነዛሉ። ዜናውን የነዛላቸው ሰው ዓላማው ለቤተሰብ እንዲያወራ ነው።በተለይ የታወቁ ሰው ከሆኑ ወይንም የህወሓት ተቃዋሚ መሆንዎን ካወቁ ከቤተሰቡ ውስጥ እርስዎን ወይንም ሁሉንም ቤተሰብ ኢላማ ለማድረግ ያቀደ የሽብር ወሬ ነው።

2) የሚወዱት ወዳጅ ወይንም ጥሩ ሰው የሚሉት ሰው በዓላማ ግን የሽብርተኛው ህወሓት ደጋፊ በመሆኑ የሚነዛቸው ወሬዎች።ሽብርተኛው ቡድን አፈቀላጤዎች ከሰማይ አይወርዱም እዛው አጠግብዎ ከሚወዱት ሰው ላይ የተሰራባቸው ሊሆኑ ይችላል።

3) ሼህ ወይንም ካህን ናቸው አይዋሹም በምትሏቸው ሰዎች የውሸት ዜና ይነዛል።ሽብርተኛው ህወሓት ከእነኝህ አካላት ስውር አባላት ነበሩት።አሁንም በገንዘብ በመደለል የውሸት ዜና እንዲያሰራጩ የሚያሰራቸው አሉ።

4) የህዝብ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች።ከተማ በሕዝብ ትራንስፖርት የሚመላለሱ ነገር ግን አንዳንድ ጥርጥር የሚፈጥሩ መንግስትን በማይገባ ጉዳይ በማጥላላት ሕዝብ ጥላቻ እንዲያድርበት ለማድረግ ቀኑን ሙሉ ከታክሲ ታክሲ እየቀያየሩ ሲሄዱ የሚውሉ አሉ።

5) የመንግስት ሰራተኞች እና ኃላፊዎች። እነኝህ በሚሰሩት ሥራ ሕዝብ እንዲመረር በማድረግ ሕዝቡን የማስመረር ሥራ ከመስራት ባለፈ ከሌላው የተሻለ የሚያውቁ በመምሰል ሕዝብ የማያውቀው እኛ በሃላፊነታችን የምናውቀው በማለት ሆን ብለው ወሬ ይነዛሉ።

6) የመንግስት ሚድያ ላይ የሚሰሩ ጋዜጠኞች፣ቪድዮ አቀናባሪዎች እና ድምፅ ኤድተሮች። እነኝህ ለሕዝብ የሚተላለፉ ዜናዎች ላይ ደካማ ዜናዎች በመምረጥ፣በሚያቀናብሩት ቪድዮ ላይ መንግስትን የሚያሳጣ ጉዳይ ላይ በማትኮር እና ጠቃሚውን በመቁረጥ እና ትኩረት እንዳያገኙ በማድረግ 

7) የህዝቡን ማኅበራዊ ግንኙነት የበለጠ እንዲዳከም እና ተስፋ እንዲቆርጥ የሚያደርጉ።የህዝብ ማህበራዊ ግንኙነት ሲጠነክር ይመካከራል፣ በሽብርተኛው ቡድን ላይ የጋራ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ያግዘዋል።ስለሆነም ጎረቤት ከጎረቤት፣ሰፈር ከሰፈር፣ እንዲጣሉ በማድረግ።በባህር ማዶ ደግሞ ማኅበርሰብ ከማኅበረሰብ እንዲለያይ በማድረግ ሕዝብ በጋራ እንዳይዋጋ ለማድረግ ይጠቀሙበታል።

የሽብር መንዣ ስምንቱ የመጀመርያ ዓረፍተ ነገሮች።
  • ''ወያኔዎች አይቻሉም----'' እነርሱ እኮ '' የፈለገ ቢሆን እነርሱ ----'' 
  • ''ይሄ ሰውዬ (ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን) እኔ አላመንኩትም ----''
  • ''ይሄ ተረኝነት ----''
  • '' ያው ነው ያም መጣ ያም መጣ ለሕዝብ ጠብ የሚል እንደሆነ የለም ''
  • '' አይምሰልህ/ሽ ፖለቲካ ማለት -----''
  • '' እኔ ምን አገባኝ ----ምን አገባን''
  • ''ዛሬ በህልሜ ----'' ለጁንታው የሚጠቅም ሕልም ያዩ መስለው ያወሩልዎታል።
  • '' ሰራዊቱ ለምን ይህን አያደርግም፣ያንን አይሰራም-----አውቀው ነው እንጂ ''
ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች እና አነጋገሮች ሲገጥማችሁ ሳያውቅ በሌላ ሰለባ ሆኖ የመጣ ወይንም የራሱ የሽብርተኛው ህወሓት የሴል አባል ሆኖ በሽብር ሥራ ላይ ተሰማርቶ እንደሚገኝ ቀድማችሁ ንቁ! ሽብር ነዥዎቹ የሚመጡት በአካል፣በስልክ ወይንም በማኅበራዊ ሚድያ ሊሆን ይችላል። ቀድመው ይንቁ! ይጠርጥሩ! እነኝህ የሽብር መንዛት ስራዎች የሚሰሩት በተደራጀ ነገር ግን አንዳንዴ ነዥዎቹም በማያውቁት መንገድ እንዲሰራባቸው ተደርጎ ነው።

==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...