ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, August 17, 2021

ሱዳን ልቧ አብጧል።የሚያስተነፍሳት ትፈልጋለች። በኢትዮጵያ ላይ ዳግም ወረራ በመፈፀም ተጨማሪ መሬት ለመውረር እንደምታስብ አዲስ ምልክት ሰጥታለች።ኢትዮጵያውያን ለሀገራችን ዘብ የምንቆምበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ነን።



ጉዳያችን ዜና / Gudayachn News 

ሱዳን በአሜሪካ አይዞህ ባይነት ከአቅሟ በላይ እየተንጠራራች ነው። የውስጥ ውጥንቅጥ ፖለቲካዋን ሳታጠራ ኢትዮጵያ በውጥረት ላይ መሆኗን የገመተችው ሱዳን ከእዚህ በፊት ከወረረችው መሬት በተጨማሪ አዲስ መሬት ልትወር እንደምትችል በአደባባይ ትናንት ተናግራለች።ይህንን የተናገረችው ትናንትየሱዳን  የሽግግር ምክርቤቱ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክ 67ኛ ዓመት የጦር ሰራዊቱን በዓል በአልፋሻቅ የኢትዮጵያ ድንበር አቅራብያ ባከበሩበት ጊዜ ነው። ባለስልጣናቱ እንደተናገሩት የሰራዊቱን በዓል በአልፋሻቅ ያቀበሩበት ምክንያት ቦታው የሱዳን መሆኑን ለማስረገጥ እና ወደፊትም የሱዳን ሰራዊት በቦታው እንደሚቆይ ለማረጋገጥ ስለፈለግን ነው ብለዋል።

''ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም እንፈልጋለን።ነገር ግን የመሬታችን ኢንች እንዲነካ አንፈልግም'' ያሉት የሱዳኑ ሽግግር ምክርቤት ፕሬዝዳንት  በአልፋሻቅ አሁንም በኢትዮጵያ የተያዙብን ስድስት ቦታዎች አሉ።አሁንም ኢትዮጵያ ድምፃችንን ትስማን ሲሉ ተናግረዋል። በመቀጠልምእንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2017 ዓም የሱዳን ጦር ሰራዊት ቦታዎቹን ለማስመለስ ጥረት አድርጎ ነበር ካሉ በኃላ ሆኖም ግን በኃላ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብን ፈርቶ እና በወቅቱ የነበረው ስርዓት ቸልተኝነት እንዲሁ ቀረ ሲሉ ተደምጠዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ ኢትዮጵያ በሁሉም የወታደራዊ ማሰልጠኛዋ ከፍተኛ ቁጥር ያለው አዲስ እና ወጣት ሰራዊት ሌት ከቀን እያሰለተነች ነው።በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት አዲስ ምልምሎች በጣም ወጣት፣ እጅግ ንቃት እና ቅልጥፍና የሚታይባቸው ናቸው። የኢትዮጵያ ይቅርብም ሆነ የሩቅ ጠላቶች ኢትዮጵያ በእዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ይህንን ያህል ሰራዊት ታዘጋጃለች ብለው ፈፅመው አልገመቱም።ምክንያቱም በእነርሱ ግምት ዘረኛው ህወሓት በኢትዮጵያ ለ27 አመታት የዘራው የጎሳ ፖለቲካ ሀገሪቱን ለመከላከል በኢትዮጵያዊነት የሚነሳ ትውልድ አሳጥቷታል ብለው ያስቡ ነበር።የሆነው ግን በተቃራኒው ነው።ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪክዋ ውስጥ በእዚህ ደረጃ ልጆቿን ለውትድርና ለማሰልጠን የከተተችበት ጊዜ የለውም።

በመጨረሻም አሁን ባለው የሱዳን የፀብ ጫሪነት አካሄድ በተለይ የሽብርተኛው ህወሓት ጀሌ የሆነው እና በማይካድራ ጭፍጨፋ የተሳተፈው ሳምሪ በመባል የሚታወቀውን ቡድን ሱዳን በማሰልጠን ለኢትዮጵያ ቀጥተኛ የፀጥታ ስጋት መሆኗ ኢትዮጵያ ይህንን ቡድን ሱዳን ውስጥ ገብታ በአየርም ሆነ በልዩ ኃይል የመደምሰስ ሙሉ መብት አላት። ኢትዮጵያ ህወሓት ጁንታ በልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ከመመከቱ አንፃር ዋናው የውግያ ግንባሯ ሱዳን ሊሆን ይችላል። አንድ ወቅት የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች አታማዥር ሹም ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ የምንዘጋጀው ለህወሓት ጁንታ እንዳይመስላችሁ እኛ የምንዘጋጀው ለዋና አዝማቾቻቸው ነው።ማለታቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ሁሉም ዘብ ሊቆምላት የሚገባበት ጊዜ ነው።ለነፃነቷ ደግሞ ከልጅ እስከ አዋቂ ተሰልፏል።በሰሞኑ የኢትዮጵያ ጦር ኃይልን ለመደገፍ በአዲስ አበባ ሊስትሮዎች ገንዘብ አተራቅመው ገቢ ሲያደርጉ፣በትናንትናው ዕለት ደግሞ መንግስትን ይህንን አድርግ እያልን እንደምናስቸግረው ሁሉ ዛሬ እኛም ለሀገራችን እና ለመንግስት ይህንን እናድርግ ብለን ገንዘብ አሰባሰብን ያሉ የአካል ጉዳተኞች ማኅበር ፌዴሬሽን ከአካል ጉዳተኞች  በፈቃዳቸው ከ100 ሺህ ብር በላይ ማዋጣታቸው የተሰማው በእዚህ ሳምንት ነው። 

ኢትዮጵያ  በፈጣሪዋ እና በልጆቿ ተጋድሎ ፈፅማ  ተሸንፋ አታውቅም! አሁንም አትሸነፍም!


No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...