ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, August 6, 2021

ልዩ ጥንቃቄ - በምዕራብ ኢትዮጵያ አዲስ ስጋት አለ።
  • በማይካድራ የዘር ጭፍጨፋ የፈፀመው የህወሓት ኃይል ሲሰለጥን ቆይቶ ኢትዮጵያ ላይ ለመዝመት  አሁን ሱዳን ብሉናይል ግዛት ገብቷል።

ጉዳያችን ዜና / Gudayachn News
========================== 
የማይ ካድራን ጭፍጨፋ ፈጽሞ ወደ ሱዳን የሸሸው ኃይል ተጨማሪ ስደተኞችን አክሎ ወታደራዊ ሥልጠና በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አታሼ በነበረ ሰው ስልጠና እየወሰደ እንደነበር ከእዚህ በፊት መገለጡ ይታወቃል። ይህ ኃ ኃይል በአሁኑ ጊዜ ወደ ብሉ ናይል ግዛት የገባ ሲሆን በቋራ እና በቤኒሻንጉል በኩል ለመምጣት ዝግጅት ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። በተለይም በቋራ ከቅማንት ታጣቂ፣ በቤኒሻንጉል ከጉምዝ ታጣቂ ጋር በመሆን ትንኮሳ ለመፈጸም ማሰቡን የመረጃ ምንጮች ገልጠዋል።  ጉዳዩን የሱዳን መንግሥት  ቢክድም የሳተላይት ፎቶዎች ግን እንቅስቃሴውን አጋልጠዋል።

በሌላ በኩል ይህንን ስራዋን የምታውቀው ሱዳን በአብዬ ግዛት የሚገኘው በተባበሩት መንግሥታት ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ከተለያዩ ሀገሮች በተውጣጣ ኃይል እንዲቀየርላት ከእዚህ በፊት የጠየቀችው ሱዳን ዛሬ እንደ አዲስ ጥያቄዋን አንስታለች።ሚድል ኢስት ሞኒተር ዛሬ እንደገለጠው ሱዳን ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ የጠየቀችውን ጥያቄ መልሳ አሁን ማንሳቷን ገልጧል።በሱዳን 4ሺህ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል የሚገኝ ሲሆን ሰራዊቱ የደቡብ እና ሰሜን ሱዳን መገናኛ በሆነችው እና በነዳጅ ሀብት በበለፀገው የአብዬ ግዛት ላይ የሚገኙ ሲሆን በቦታው የሚገኙ ሲቪሎች እና የእርዳታ ሰራተኞች ጥበቃ እና ቁጥጥር ላይ ተሰማርተዋል።ሱዳን ይህንን ጥያቄ ያነሳቸው አንዱ ምክንያት በኢትዮጵያ ላይ የሚዘምቱ በማይካድራ ጭፍጨፋ የተሳተፉ ወንጀለኞችን እያሰለተነች እና ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት እየሞከረች ከመሆኑ አንፃር ከኢትዮጵያ ጋር የበለጠ ፍጥጫ ውስጥ እንደምትገባ በመረዳት እንደሆነ መገመት ይቻላል።

No comments:

ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ታላቅ ተልዕኮ የሚኖረው ሀገራዊ የምምክር ኮሚሽን በተመለከተ ምን ያህል እናውቃለን?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ባካተተ መልኩ አዋቅሯል። በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉት ነጥቦች ምላሽ ያገኛሉ፡  ኮሚሽኑ እንዴት ተመሰረተ?  የኮሚሽኑ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት ተመ...