ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, August 11, 2021

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጦርነቱ ምክንያት ለደረሰው ሰብዓዊ ቀውስ ዕርዳት የሚውል ገንዘብ ማሰባሰብ ጀምረዋል።በሳምንቱ መጨረሻ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጋብዘው በሰብዓዊ ቀውሱ ዙርያ ማብራርያ ለማግኘት ቀጠሮ ይዘዋል።


በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊ ቀውስ እንደተፈጠረ ይታወቃል።በመቶ ሺዎች የሚሆኑ ተፈናቅለዋል።ጦርነት ከመፈናቀል በላይ ይዞ የሚመጣው ተያያዥ ችግሮች አሉ።ሕፃናት ካለወላጅ ይቀራሉ፣የአካል ጉዳተኞች ይኖራሉ።አሁን ግን በዋናነት የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን የዕለት ጉርስ እና ልብስ ያስፈልጋቸዋል። ይህንን ሰብዓዊ ቀውስ ለመቀነስና ለወገኖቻችን አለን! በማለት ተፈናቃዮችን ለማገዝ እንዲቻል በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የሰብዓዊ እርዳታ ማሰባሰብ ሥራ ጀምረዋል።በማስተባበር ሥራ ላይ የተሰማሩት በኖርዌይ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰቦች፣የሃይማኖት ድርጅቶች እና የሲቪክ ማኅበራት በአንድነት በመሆን ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሳምንቱ መጨረሻ በደረሰው የሰብዓዊ ቀውስ ዙርያ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሚና ዙርያ ለመወያየት እና ማብራርያ ለማግኘት በኖርዲክ ሀገሮች የኢትዮጵያ አምባሳደር ድሪባ ኩማ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲያስፖራ ጉዳይ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት እና የብሔራዊ አደጋ እና ዝግጁነት ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በዙም ተገኝተው በኖርዌይ ለሚኖሩ ለኢትዮጵያውያን ማብራርያ ይሰጣሉ (ዝርዝሩን ከላይ ፖስተሩ ላይ ይመልከቱ)።

ድጋፍ የሚያደርጉበት ሁለት አማራጭ መንገዶች

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የዕርዳታ ማሰባሰብያ የሚገባበት የባንክ አካውንት ቁጥር 1503 43 13420 (የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ኢመርጅንሲ አካውንት)
ወይም በቪብስ ቁጥር 647675 በመጠቀም ድጋፍዎን ለወገንዎ ማድረግ ይቻላሉ።






No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...